A boy and his sister drowned in a water filled hole in Hawasa’s - TopicsExpress



          

A boy and his sister drowned in a water filled hole in Hawasa’s main street - በሐዋሳ የአምስት ዓመት ሕፃንና እህቱ ተከፍቶ በተተወ የመንገድ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ በሐዋሳ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ክፍት ተደርጐ በተተወ የመንገድ ዳር ጉድጓድ ውስጥ ሚያዝያ 27 ቀን 2006 ዓ.ም. የገቡ የአምስት ዓመት ሕፃንና የሀያ ዓመት እህቱ ሕይወታቸው ማለፉን የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ በዕለቱ ኃይለኛ ዝናብ ዘንቦ ስለነበረ መጀመርያ ጉድጓዱ ውስጥ የገባውን ትንሽ ወንድሟን ለማዳን የሞከረችው እህቱ ጉድጓዱ ውስጥ በመግባቷ፣ በመጨረሻም አደሬ ሆስፒታል ከሚባለው አካባቢ አስክሬናቸው መገኘቱን ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የልጆቻቸው አስክሬን በዕለቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ በክሬን መውጣቱንና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ሚያዝያ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. መፈጸሙን አባታቸው አቶ ደስታ አበው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ዘገባው የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንዳስነበበው የከተማው ማዘጋጃ ቤት ቱቦውን በማግሥቱ በሲሚንቶ ደፍኗል፡፡ በሌላ በኩል ማዘጋጃ ቤቱ የደረሰውን ችግር ተመልክቶ በአፋጣኝ የወሰደው ዕርምጃ መልካም የሚባል ቢሆንም፣ ክፍት ተደርጐ በተተወ ጉድጓድ ምክንያት ሁለት ልጆቻቸውን አጥተው ሳለ ምንም ዓይነት የሐዘን መግለጫ መልዕክት አለመላኩ ቅር እንዳሰኛቸው አቶ ደስታ መግለጻቸውም ተጠቁሟል፡፡ ተጨማሪ...diretu.be/883534
Posted on: Sun, 11 May 2014 18:30:00 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015