ስም፡- ዳግማዊ ምኒልክ Name: Menelik - TopicsExpress



          

ስም፡- ዳግማዊ ምኒልክ Name: Menelik II የአባት ስም፡-ኃይለ መለኮት Father’s Name:Haile Melekot ሥራ፡- ንጉሥ ነገሥት Occupation: Emperor የትውልድ ቀን፡- ነሃሴ 9፣0%6 ዓ.ም፣ Date of Birth: August 17,1844 የሞቱበት ቀን፡- ታህሣሥ 3፣09)6ዓ.ም. Date of Death:December 12,1913 የትውልድ ቦታ፡- አንጎለላ ማርያም Place of Birth: Angolala Mariam,Shoa,Ethiopia የሞቱበት ቦታ፡- አዲስ አበባ Place of Death: Addis Ababa የቀድሞ መጠሪያ ስማቸው፡- ሣህለ ማርያም Originally: Sahile Mariam ዳግማዊ አፄ (እምዬ) ምኒልክን የምወድባቸው ምክንያቶች፡- Reasons for being passionate about Emperor(Emye)Menelik II ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ወደ ንግሥና መምጣታቸው፤ Enthroned to unify Ethiopia; የኢትዮጵያ የአዲሱ ሥልጣኔ መሥራች መሆናቸው፤ Founder of Ethiopia’s New Civilization; ለምሣሌ፡-የመጀመሪያው ትምህርት ቤት(ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት)፣ የመጀመሪያው ባንክ(አቢሲንያ ባንክ)፣የመጀመሪያው ሆስፒታል(ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል)፣የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት(ሠይጣን ቤት ቀደም ሲል ሜጋ አምፊ ቴአትር ተብሎ ይጠራ የነበረው የአሁኑ ዋፋ ሲኒማ ያለበት ሲሆን፣ይህ ቦታ ቀደም ሲል ሠይጣን ቤት የተባለው መኳንንቶቹ እኛ አናይም ይህ የሠይጣን ሥራ ነው በማለታቸው እምዬ ምኒልክ ሲኒማ ለማየት ብቻቸውን ሲገቡ ሠይጣን ቤት ገቡ ከሚለው በመውሰድ ነው)፣የመጀመሪያው የአስፓልት መንገድ(ከአዲስ አበባ እስከ አዲስ ዓለም 55 ኪሎ ሜትር፣የመጀመሪያው የውሃ መሥመር፣የመጀመሪያው ስልክ፣የመጀመሪያው የባቡር ሃዲድ(ከጅቡቲ-ድሬዳዋ-አዲስ አበባ፤ምንም እንኳን ከባቡር ሃዲዱ መጠናቀቅ በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም)፣ For instance,The first School(Menelik II School);The first bank(Bank of Abyssinia);The first Hospital(Menelik II Hospital);The first Cinema(Satan Beth the then Mega Amphi Theatre lately Wafa Cinema);The first Asphalt road(Addis Ababa through Addis Alem 55 Kms);The first tap water line;The first telephone,The first railway line(Addis Ababa via Djibouti though he died prior to its completion); የመጀመሪያው አውቶሞቢል መኪና (በአሁኑ ሰዓት መኪናዋ በብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ ትገኛለች፡፡)፣ The first Automobile Car(now displayed at the National Museum of Ethiopia) በአዲስ አበባ የመጀመሪያው ውቴል (ጣይቱ ሆቴል) እጅግ ለሚወዷት ሃገራቸው ማስገንባታቸው፤ Built the first modern hotel in Addis Ababa(Taitu Hotel); ለህዝባቸው ታማኝ ንጉሥ መሆናቸው፤ Loyalty to the people; የህትመት መሣሪያን ማስመጣታቸው፤ Imported printing machine; የጥይት ፋብሪካ ማቋቋማቸው፤ Established bullet plant; የማዕድን ፍለጋ ፕሮጀክት ማስጀመራቸው፤ Launched mining project; ዘመናዊ ገንዘቦችን አስቀርፆ ማውጣት እና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጋቸው፤ Minting and employing modern currency notes; የገንዘብ መቅረጫ አስመጥተው ሥራ ላይ እንዲውል ማድረጋቸው፤ Importing and implementing Money minting machine; የቴሌፎን፣ቴሌግራም እና የፖስታ አገልግሎትን በሥራ ላይ ማዋላቸው፤ Implementing telephone, telegram and postal services; የክትባት መድኃኒት አስመጥተው የሚወዱት ህዝባቸው እንዲጠቀምበት ማድረጋቸው፤ Imported vaccination medicines so as benefiting the people; የኤሌክትሪክ መብራት አገልግሎት ማስጀመራቸው፤ Launching Electricity Power; የእህል ወፍጮ እንዲቋቋም ማድረጋቸው እና በወቅቱ የነበሩት መኳንንቶችም ሆኑ ህዝባቸው በነገሩ ግራ በመጋባታቸው እና ቴክኖሎጂውን ላለመቀበል ሲያንገራግሩ እምዬ ምኒልክ የመጀመሪያው የወፍጮ ቤቱ አስፈጪ በመሆን አገልግሎቱን ዱቄት እየቦነነባቸው ለሚወዱት ህዝባቸው ማሣየታቸው እና ማስተዋወቃቸው፤ Establishing grind Mill though opposition from the nobility to accepting the technology and Emye Menelik, provided the dust sprinkle, was the first person make the gringing; የመንገድ፣ድልድይ እና የህንፃ ሥራዎች ግንባታን ማስጀመራቸው፤ Road, bridge and building constructions; የሸክላ ፋብሪካን ማቋቋማቸው፤ Establishing clay factory; ቶሎ የሚደርስ ልዩ የዛፍ ዘር አስመጥተው ማስተከላቸው፤ Planting a special tree; በሕክምና ተቋማት ባህላዊውን እና ዘመናዊውን መድኃኒት አቀነባብሮ መጠቀምን ማስጀመራቸው፤ Starting an integrated use of modern medicines with traditional herbs; የመጠጥ ውሃ ቧንቧ ዝርጋታን እና የውሃ ጉድጓዶችን ማደራጀታቸው፤ Organizing the installation of tap water and well water; የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ጋዜጣ ማውጣታቸው(የህትመት ማሽኑን ከማስመጣታቸው በፊት በእጅ ተፅፎ ለመኳንንቶቹ የሚታደል አነስተኛ ጋዜጣ ነበራቸው)፤ Printing the first Ethiopian Newspaper; ዘመናዊ ሆቴል ማቋቋማቸው፤ Establishing modern hotel; የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በአቻነት ደረጃ አጠናክረው መቀጠላቸው፤ Continuing diplomatic relations in an equivalent manner; የንግድ ግንኙነት ከውጪ ሃገራት ጋር መጀመራቸው፤ Starting trade relations with foreign countries; የሃገር ወሰን ክልል ስምምነት መፈራረማቸው፤ Signing territorial boundary agreements; በቂ ሕክምና ባልተገኘበት አጋጣሚ ማንም ሰው ታሞ ሲዳከም 48 ሰዓት ሳይሆነው ሞተ ተብሎ በችኮላ እንዳይገነዝ የሚያደርግ ደንብ አውጥተው በሥራ ላይ ማዋላቸው፤ Enacted and implemented a law that prevents an ill person not to be furnished for coffin before 48 hours dubbing as dead in situations where sufficient medication is absent. ባርነትን ማውገዝ እና በህግ መከልከላቸው፤ Reprimanding slavery by virtue of Law; በኢየሩሣሌም ገዳም የኢትዮጵያ ይዞታ የነበረውን አርመን፣ፅርአውያን እና ግብፃውያን ስለአጣበቡት፤ከቱርኩ ንጉሥ ከሡልጣን አብዱል ሂሚድሃን ጋር ተላልከው የአባቶችን ይዞታ ማስከበራቸው እና ማስፋፋታቸው፤ Expediting with the Turkish king Sultan Abdul Himidhan, he secured Ethiopian possession at monastery of Jerusalem for Armen, Egyptians, and Tsarinas populated and congested it; ለአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያውን የሥፍራ ማስተር ፕላን እና የቦታ አስተዳደር ደንብ ማውጣታቸው፤ Proclaimed the first areal administration regulation and spatial Master Plan for Addis Ababa; የድንጋይ ከሰል ማዕድን እንዲገኝ ማስደረጋቸው፤ Finding charcoal and coal mining; ለሚገዙት ህዝብ ታላቅ ክብር የነበራቸው በመሆኑ፤ Had a due respect for the people he ruled; ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠሏ በፊት የነበራትን ቅርፅ እ.ኢ.አ በ 1900 እንድትይዝ ማስቻላቸው፤ Gave Ethiopia its shape prior to the secession of Eritrea in 1892; የኢጣያልንን ወራሪ ኃይል በአድዋ ጦርነት ላይ በከፍተኛ ጀግንነት አሸንፈው የአፍሪካውያን ብሎም የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሣሌት መሆናቸው እና ሉዓላዊነቷን የጠበቀች ሃገር ለትውልድ ማስተላለፋቸው፤ An icon for freedom of African even Black people of the world having won and expelled the Italian expedition courageously at the battle of Adwa; ለሃገራቸው እና ለህዝባቸው ቃልኪዳን መግባታቸው ለዚህም ማሳያ ይሆናቸው ዘንድ ራሣቸው ላይ ነጭ ጨርቅ ማሠራቸው፤ Vowed for his country and his people and he put a white amulet across his head; በቤተ መንግሥት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሣይክል የነዱ የመጀመሪያው ደፋር ኢትዮጵያዊ ንጉሥ መሆናቸው፤ The first brave Ethiopian king to have ridden a bicycle within the premises of the Grand palace; የመጀመሪያ በሆነችው አውቶሞቢል መኪና ላይ የተሣፈሩ የመጀመሪያው ንጉሥ መሆናቸው፤ The first king to embark on the first Automobile Car; በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የስልክ ጥሪ ያደረጉ ንጉሥ መሆናቸው፤ The first Ethiopian King to have made phone call; የሚወዷትን ሃገራቸውን በወቅቱ ከነበረው የእድገት ሁኔታ ጋር አብራ እንድትሄድ የነበራቸው ቁርጠኛ አቋም፤ Savvy ness manifested through the then technological advancement and conditions of modernization; አዲስ አበባን መቆርቆራቸው፤ Established Addis Ababa; በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ልዩ ልዩ ቦታዎች ላይ እጅግ በጣም አስገራሚ የሆኑ አብያተ - መንግሥታትን ማስገንባታቸው(አንኮበር ላይ የተሠራው ቤተ መንግሥት የሚገኘው ከፍታው ከባህር ወለል በላይ 2870 ሜትር በሆነ ተራራ ላይ ነው፤አዲስ አበባ የሚገኘው ቤተ መንግሥት የተገነባው በእንጦጦ ተራራ ሲሆን ከፍታውም ከባህር ወለል በለይ አስከ 3100 ሜትር ይደርሳል፤ሆለታ ገነት ላይ በአነስተኛ ኮረብታማ ቦታ ላይ ያስገነቡት ቤተ መንግሥት ከአዲስ አበባ በ ከ 30 - 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲገኝ አዲስ ዓለም ላይ ያለው ቤተ መንግሥት ደግሞ ከአዲስ አበባ በ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡) Had built astounding palaces throughout the country(Ankober’s Palace 2870 metres above sea level; Entoto’s Palace – Addis Ababa at about 3200 metres above sea level;Holeta Guenet’s palace built on a hill 30 -40 kilo metres away from Addis Ababa; and the Addis Alems Palace some 55 kilometres away from Addis Ababa.) በመላ ሃገሪቱ እጅግ በጣም በርካታ ቁጥር ያላቸውን አብያተ ክርስቲያናት ማሣነፃቸው፤ Had built a number of Orthodox Christian Churches through out Ethiopia; መስጅዶችን በተለይም በአዲስ አበባ ያለውን ታላቁን የአንዋር መስጅድ ማሰራታቸው፤ Built mosques especially the Grand Anwar mosque of Addis Ababa; ከደሃው ህዝባቸው ላለመለየት በድንክ እልጋ ላይ መተኛታቸው፤ He used to sleep on a bunk – small bed so as to be consonant with the laity; ከውጭ ሃገራት የመጡ እንግዶችን ለመቀበል ካልሆን በስተቀር ጫማ አለመጫማታቸው እና እንደ ተራው የሃገሬው ሰው በባዶ እግራቸው መሄዳቸው ይህም የሃገሬ ህዝብ በባዶ እግሩ እየሄደ እኔ በጫማ መሄድ የለብኝም ከሚል ቅን አስተሳሰብ የመነጨ በመሆኑ፤ Bare footed except when receiving foreign diplomats to equating himself with the ordinary people; በሃይማኖታቸው ጠንካራ እና ፍፁም የፀኑ መሆናቸው፤ Had been very strong and firm in his faith; ሥልጣኔ እጅግም ያልገባውን ህዝብ አቻችለው በፍቅር መምራት መቻላቸው፤ Had ruled the urbane and partly modernized people with harmony and love; እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን በ18 79 ዓ.ም. ሲመረቅ 5393 ሠንጋ በሬ ታርዶ ከ 60፣000 በላይ የሚሆን ህዝብ ተጋብዞ ነበር የምረቃ ሥነ ሥርዓቱም ከመስከረም 21 እስከ ህዳር 25 መቀጠሉ፤ Up on the inaugural ceremony of Entoto Mariam Church,some 5393 oxen had been slaughtered for over 60,000 invitee who had attended at; And the ceremony lasted till October 1 through December 3,1890; በአጠቃላይ ለሃገር አነንድነት እና ሥልጣኔ የተፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት፡፡ Born for the solidarity and modernization of Ethiopia – in general. ማስታወሻ፡- ከላይ የተጠቀሱት የሃገር ወዳዱ ኢትዮያዊ ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ዋና ዋና ክንዋኔዎች ሲሆኑ ሌሎች ብዙ ያልተጠቀሱ ተግባሮቻቸው እንዳሉ በትህትና እገልጣለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ Ps. The above mentioned activities of the savvy and patriotic King were not the only deeds, but of little out of the many – I would politely say. And I thank you. ዘላለማዊ ክብር ለእምዬ ምኒልክ! Everlasting honour to Emye Menelik!
Posted on: Fri, 28 Feb 2014 16:08:36 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015