አንድ ነገር ልንገርህ ??? "ንገረኝ" - TopicsExpress



          

አንድ ነገር ልንገርህ ??? "ንገረኝ" በለኛ...ሀገርህን የጎዳት ወደኋላም ያስቀራት ሙስና ይመስልሀል...ግን አይደለም....ሀገርህን ወደኋላ ያስቀራት ስራ አለመውደድ ይመስልሀል እርሱ እንዳለ ሆኖ...ሀገርህን ከድህነት ወለል በታች(የደሀ ደሀ ያረጋት) ህዝቡ አለመማሩ ይመስልሀል ልክ ነህ ግን እሱ ብቻ አይደለም.... ሀገርህን ወደኋላ ያስቀራት ጽንፈኝነት ነው...ፖለቲካችንን ወደኋላ ያስቀረው ጽንፈኝነት ነው....ምእመኑን ከአማኒነት ወደሀይማኖተኛነት እየለወጠው ያለው እኔ ሙሉ ለሙሉ ልክ ነኝ አንተ ግን ሙሉ ለሙሉ ተሳስተሀል የሚል እንጭጭ አስተሳሰብ ነው::...አትናደድ ታገሰኝ.... ወደፖለቲካችን እንምጣ... የኛ ሀገር ፖለቲካም ፖለቲከኛም ኮሚክ ነው ፖለቲከኞቻችን ገና ለአቅመ ፑልትክና ሳይበቁ ፑልትክናቸውን ይፖለትካሉ...ከዚያ በምህጻረ ቃል በታጀበ ስም እነሱን ከመሳሰሉ ፖልታኪዎች ጋር ሆነው የፖለቲካ መፖልተኪያ ድርጅት ይመሰርታሉ... ከዚያም እንደምንም ተጋፍተው ፓርላማ ይገቡና "ይተኛሉ"(አዎ እንቅልፋቸውን ይለጥጡታል) ወር ጠብቀው ደሞዛቸውን ይበላሉ...ከዚያም ከረጅም እንቅልፋቸውና ኢህአዴግ ተሳስቷል ከምትል ጠባብ አስተሳሰባቸው ጋር ይኖራሉ...እነሱን ከኢህአዴግ የሚለያቸው የኢህአዴግን ስህተት ብቻ እየነቀሱ ማውጣታቸው የተደረገውንም ያልተደረገውንም ጥላሸት እየቀቡ ማውገዛቸው....በቃ ይሄ ነው ፖለቲከኛ ያስባላቸው.(ድንቄም ፖለቲከኛ)... እነሱ የተሻለ ፖሊሲ የላቸውም ቢኖራቸው እንኳ እንደፍታብሄር ህጋችን ቀጥታ ከአንዱ ሀገር የተቀዳ እንጂ ከኛ ሀገር context ጋር ያልተስማማና በራሳቸው ያልተነደፈ ነው::በነሱ አይን መንግስት ተሳስቶ እንኳ የሚሰራው መልካም ነገር ሁሉ ስህተት ነው ምክኛቱም መንግስትን ተሳስተሀል ካላሉ ተቃዋሚነታቸው ሚታወቅ አይመስላቸውማ ቂቂቂ... ትዝ ይለኛል ኮንዶሚኒየም ቤቶችን እድሜ ይስጠውና አርከበ ልሰራ ነው ተመዝገቡ ሲለን ምድረ ተቃዋሚ ሆዬ ብለው ሀገሬውን ሁሉ አዘናጉ (ነቄዎች ብቻ ተመዘገብን) ሃሃሃ...ታዲያ ያኔ እንደዛ ያለ ጶለቲከኛ ዘንድሮ 20/80 ሲመዘገብ ሰልፍ ላይ ተገናኘን ቂቂቂ... እንዲሁ ነን... አንድን ነገር ስንደግፍ ሌላውን ከመጥላት ወይም ከመቃወም ላይ ተደግፈን ነው ስለዚህ ሁሌም ኑሮአችን የንፉቅቅ... ህዝባችንስ ቢሆን እስኪ እዩት ተቃዋሚ ነኝ ባዩን...ሰው ኢህአዴግን ከደገፈ ሀገር እንደካደና ለሆዱ እንዳደረ አድርጎ ጥምብ እርኩሱን ያወጣዋል (ይሄ የኔም ችግር ነው) እኛ የመቃወም መብት ይሰጠን ብለን እንጮሀለን ግን የሌላውን ያለመቃወም መብት እንዳፈራለን... እኛ ኢህአዴግ ሆይ ስንተችህ አትርገጠን ብለን ሁሌም እንጮሀለን የሌላውን ያለመተቸት መብት ግን አናከብርም.... እንዲሁ ነን ...ሁሌም ሰዉ እኛን እንዲሆን እንፈልጋለን ለኛ ይሄ መንግስት ላይመቸን ይችላል ግን የተመቸው ካለ የመደገፍ መብቱን እንረዳለት...ኢህአዴግን ያልሰደበ ጋዜጠኛን ለምን እንደካድሬ እንቆጥረዋለን???የሰውን መብት ሳናከብር የኛ መብት እንዲከበርልን መሞከር ጽንፈኝነትና ጠባብ አስተሳሰብ ነው:: አዎ ፍሬንድካዎቼ ጽንፈኞች ነን መንግስት ጥሩ ሲሰራ እግዚሀር ይስጥህ ከማለት ይልቅ ስራውን ለማጣጣልና ለማንቋሸሽ እንሯሯጣለን....በጎውን በጎ ክፉውን ክፉ የምንልበትን ህሊና ጽንፈኝነት ቀምቶናል.... *** መስቀል ፍላወር አካባቢ አንድ የትግሬ ሙዚቃ ብቻ የምታጫውት ቤት አለች ሚዘፈነው ትግረኛ ብቻ ነው ደንበኞቹም በአብዛኛው ትግሬዎች ብቻ ናቸው...እናም ጓደኞቼ እዚያች ቤት ሲገቡ በጣም ይናደዳሉ ይላል አንደኛው... ይላል ሌላኛው.... ከዚያች ቤት ቀጥላ ደግሞ አንድ የባህል ሙዚቃ (በማሲንቆ) ሚጫወቱባት ቤት አለች እዚያ ስንገባ ማንም ሰው ስለሰዎቹ ዘረኝነት አያወራም በሙዚቃው ተዝናንቶ ከመውጣት ውጪ,,,,ግን እኮ እዚህች ቤት ያለአማርኛ ዘፈን ሌላ አይከፈትም...ኦሮሚኛም የለም ጉራገኛም የለም ግን ማንም ስለዘረኝነታቸው complain አያቀርብም ትግሬዎቹ ዘረኛ ከሆኑ እነዚህኞቹም ዘረኛ ናቸው ማለት ነው እነዚህ ካልሆኑ ደግሞ እነዚያም አይደሉም ማለት ነው..... እንዲሁ ነን በጥላቻና እኔ ብቻ ትክክል ነኝ በሚል ምልኪ ላይ ተደግፈን ነው የኖርነው:: *** የሀይማኖት አባቶችም አንድ ከሚያደርገን ነገር ይልቅ የሚያለያየንን ነገር እየቆጠሩ ነው ሲያስተምሩን የኖሩት... የሌላውን እንከንና ጉድፍ እያነሱ ነው ሚሰብኩን:: ለምሳሌ--ፕሮቴስታንቱ ኦርቶዶክስን ኦርቶዶክሱ ፕሮቴስታትን ሲያጠለሽና አንዱ የአንዱን እንከን እንደስብከቱ ማጣፈጫ ሲጠቀምበት እንጂ አብሮ መኖርንና ፍቅርን ሲሰብክ አይታይም.... እርሱ ስብከቱ ይጣፍጥለት እንጂ የሚናገረው ንግግር ምን ያክል አንድነታችንንና አብሮ የመኖር ባህላችንን እንደሚያበላሽ አይረዳውም...እርሱ የአንዱን ቤተእምነት ጥላሸት አብዝቶ እራሱን ከፍ ከፍ ያድርግ እንጂ የሚናገረው ንግግር ምን ያክል የማህበረሰቡን ሰላም እንደሚያውክ አያስተውልም....ሰውን በማቆሸሽ ንጽህናን ያገኝ ይመስል ጽንፈኛና ጠባብ አመለካከቱን እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ ዘርቶት ይወርዳል (በመሰረቱ የሌላው መሳሳት በምንም ሁኔታ እኛን ልክ አያደርገንም) :: እንዲሁ ነን... *** እኛ ትክክል ነን ስንል ሌላውን ተሳስተሀል ካላልን አንደሰትም...እኛም አንተም ትክክል ነን ማለት አንችልበትም... ለዚያ ነው መከፋፈላችን የበዛው ለዚያ ነው ጎጠኝነታችንና ጎሰኝነታችን የበዛው ለዚያ ነው ተቃዋሚዎችና ገዢው ፓርቲ ልንስማማ ያልቻልነው:: ጸሀዩ መንግስታችንም ይሉኝታ አያውቅም ሁል ጊዜ የርሱ ፖሊሲ ብቻ ነው ልክ...ሁል ጊዜ እርሱ ትክክል ተቃዋሚዎች ደግሞ ስህተት ናቸው....ሁል ጊዜ እርሱን የተቃወመውንና የተቃየመውን ሁሉ "ውጉዝ ከመአሪዮስ" ብሎ መቀመቅ ያወርደዋል እንጂ ሀሳቡ ልክ ይሆንን ብሎ ራሱን አይፈትሽም:: እንዲሁ ነን... በመንግስት ማሊያ ቋሚ ተሰላፊዎች የሆኑት ገዢዎቻችን ተቃዋሚያቸውን እንጂ ራሳቸውን እንዳያዩ ሆነው "በጽንፈኝነት" ታውረዋል:: ጽንፈኝነት ነው ሀገር ያፈረሰው ጽንፈኝነት ነው ሀገር ያጠፋው ጽንፈኝነት ነው ወደኋላ የጎተተን..... እንዲሁ ነን.....
Posted on: Fri, 28 Jun 2013 22:54:02 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015