ወላሂ ታላቁ የእዝነተና የራህመት ወር - TopicsExpress



          

ወላሂ ታላቁ የእዝነተና የራህመት ወር ረመዷን መጥቷል ድልን ከፈለግን ሰላምን ከፈለግን የጌታችንን በእዝነት አይን መታየትን ከፈለገን ወንጀላችን ተምሮ አላህ ከአይን ቅንድባችን ይበልጥ እንዲቀርበን ከፈለግን የፈተናችን ጊዜ እንዲቋጭ ከፈለግን ነገ ጀነትን ለመውረስ ከፈለግን ዐፉ እንባባል አንድ ሰው የተበደለውን ነገር ለአላህ ብሎ ዐፉ ካለ አላህ በእጥፍ ወንጀሉ ይቅር ይለዋል በቅርቡ መስጂድ ውስጥ ኡስታዝ ዳዕዋ ሲያደርጉ የሰማሁትን ድንቅ ሀዲስ እየቆራረጥኩም እየቀጣጠልኩም ቢሆን ልንገራቹ አንድ ቀን ረሱል ሰ ዐ ወ ቁጭ ብለው ደዕዋ ለሰሀቦች በሚያደርጉበት ጊዜ እንዲህ አሉ አንድ የጀነት የሆነ ሰው ወደኛ እየመጣ ነው አሉ ሰሀቦች ምን ይሆን እያሉ ዑመር ነው አቡበክር እያሉ በውስጣቸው ሲወዛገቡ ከቆይታ በኃላ አንድ ብዙም የማይጠበቅ እንደማንኛም ተራ ሰው (የሰው ተራ የለውም የውስጣችንና መጨረሻትችንን የሚያውቀው አንድ አላህ ነው እንዲሁ ለቋንቋ አረዳድ ነው) ለዳዕዋ በተቀመጡበት ይገባና ቁጭ ይላል በሚቀጥለው ቀንም ረሱል ተመሳስይ ንግ ግር ተናግረው የጀነት የሆነ ሰው እየመጣ ነው ብለው ከአፍታ ቆይታ በኃላ የትላንቱ ሰው ይመጣል ታዲያ በሰሀቦች ጊዜ የነበረው ለኸይር ስራ መሽቀዳደም የሚወዳደረው ነገር የለም እና አሊይ ረዐ ምን ቢሰራ ነው ይህ ሰው የጀነት የተባለው ብለው ሰውየውን በድብቅ መከታተል ጀመሩ ለሁለት ቀናት ያህል ሰውየውን ሲከታተል ለሊትም ቀንም ከማንም የተለየ ኢባዳ የሚያደርግ አልነበረም ይበላል ይጠጣል ይሰግዳል በሰዐቱ ይተኛል ታዲያ አሊይ ረዐ መከታተሉን ትተው ለምን አልጠይቀውም አሉና እንዲህ ይሉታል ረሱል ሰዐወ ሁለት ቀን የጀነት መሆንህን መሰከሩልህ እኔም ከሌላው በተለየ ምን ቢያደርግ ነው እንዲህ አይነት ደረጃ ያገኘው ብዬ ለሁለት ቀናት ተከታተልኩህ ነገር ግን ምን አይነት የተለየ ነገር አለየሁብህም እስቲ ሚስጥሩን ንገረኝ ይሉታል ሰውየውም አዎ ልክ ነህ ከማንም የተለየ ስራ የለኝም ነገር ግን እኔና አላህ ብቻ የምናውቃት ስራ አለች የማደርጋት እሷም ማታ ማታ ሰተኛ የበደሉኝ ሰዎች ለአላህ ብዬ ይቅር ብዬቸው ነው የምተኛው ይላቸዋል ያ ጀማዐ ሰዎች ሲበድሉን አላህ ፊት እፋረደሀለው ብለን የምናተርፈው ትርፍ በጣም በጣም ጥቂት ናት በዕርግጥ ተበዳይ ቢካስም ነገር ግን አላህ ይቅር ባዮችን ከሚያጎናፅፋቸው ጀነትን ከመሰሉ ገፀ በረከቶች በምንም በልኩ አይወዳደርም ሰለሆንም ሁላችንም ዐፉ እንባባል በምንም አይነት መልኩ የበደልኩት ያስቀየምኩት ትንሽም ቢሆን ቅር ያስባልኩት ሰው ካለ አይደለም ስላለ ለአላህ ብላቹ ዐፉ በሉኝ እንግዳችንን እንቀበለው ሸህሩ ረመዷን የኢባዳን የትግል ወር
Posted on: Sun, 07 Jul 2013 13:37:00 +0000

Trending Topics




© 2015