1.ቅድስት ሉሲ ከ283-304 እ.አ.አ የኖረች - TopicsExpress



          

1.ቅድስት ሉሲ ከ283-304 እ.አ.አ የኖረች ወጣት ሰማዕት ስትሆን Lucia of Syracuse; Lucia de Syracuse(Lucy of Syracuse), Lucia, Lucy,Santa Lucia(Saint Lucia), or Saint Lukia እየተባለች ትጠራለች ሉሲ ወይም ሉሲያ የሚለው ቃል (luc-lux) ምንጩ ላቲን ሲሆን ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው ...Syracuse(ሲሪያከስ=ሰራኩስም) ደግሞ በዶቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነትን የተቀበለችበት የጣልያን ከተማ ናት ( she was a martyr in Syracuse during the Diocletian persecutions of 304 AD) በቅዱስ መጽፋችን ውስጥ ሰራኩስም ተብሎ ቦታው ተዘግቧል …..በሐዋርያት ሥራ ም.28 ቁ.12 ላይ "ወደ ሰራኩስም በገባን ጊዜ ሦስት ቀን ተቀመጥን፤"( Acts 28:12 And landing at Syracuse, we tarried there three days.) ልዩ መለያዋ ከመከራዋ ጽናት የተነሳ ዓይኗን እንኳ ጎልጉለው ቢያወጡት ብርሃናዊ ዓይን ተሰጥቷት ታይ ነበርና በወርቅ ዝርግ ሳህን ላይ ሁለት ዓይኖቿን እንደያዘች መታየቷ ነው:: (As final torture, her eyes were gouged out. She was miraculously still able to see without her eyes. To this day we see pictures of Saint Lucy holding her eyes on a golden plate. ) ታዲያ ግን ይህ እኛ በብዛት ቅድስት አርሴማ እያልን የምንጠቀምበት ሥዕለ አድኅኖ (Iconography) ነው:: 2. ቅድስት ባርባራ በቤተ ክርስቲያናችን ታህሳስ ስምንት የምትዘከረው የኒቆሚዲያዋ ኮከብ ሰማዕቷ ቅድስት ባርባራ ደግሞ ሌላዋ በገዛ አባቷ እጅ ሰማዕትነትን የተቀበለች እንደነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያሉ ደጋጎች በአርጋኖን ምስጋናቸውላይ የተማጸኑባት(አርጋኖን ዘሰንበት የመጨረሻውን ክፍል ይመልከቱ) በዚሁ ታላቅ ጻድቅ(ዳግማዊ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ = አባ ጊዮርጊስ) ገድል ላይ ከቅዱሳን አንስት ጋር ስሟ የተጠቀሰ የበረከትና የቃል ኪዳን እናት ስትሆን በሥ ዕሏ ላይ ብዙውን ጊዜ ስሟ በግሪክ H AGIA BAPBPA (ኢ አጊያ ባርባራ= ቅድስት ባርባራ) ተብሎ ተጽፎ ይገኛል:: ጽዋና መስቀል ከዘንባባ ጋር ይዛ በመታየቷ እኛ ቅድስት አርሴማ ናት በማለት በብዛት እየተጠበምንበት ያለው ሥዕል ነው:: 3.ቅድስት አርሴማ ዲዮቅልጢያኖስ መልከመልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ቀድሞ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኛላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በየሃገሩ ሰደደ:: በዚህ ጊዜ ይህች አርሴማ ሰባ ሁለት ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣ ነበር:: ሃያ አራቱ ደናግል የቀሩት አርባ ስምንቱ መዓስባን(ያገቡ) ነበሩ:: በወቅቱ የነበረች እመ ምኔቲቱ አጋታ ትባላለች:: የዲዮቅልጢያኖስ ሠራዊት የተባለችውን ብላቴና እየፈለጉ አርሴማ ካለችበት ደረሱ:: ባይዋት ጊዜ በውበጥው ተደንቀው ሥዕሏን ሥለው ወስደው ለንጉሱ ሰጡት:: ዲዮቅልጢያኖስም መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል በሉ ሄዳችሁ እርሷን አምጡልኝ አላቸው:: እርሷም እንዳስፈለጋት አውቃ ተነስታ አርማንያ ወረደች:: እርሱም ከዚያ እንደወረደች አውቆ በወቅቱ የነበረው የአርማንያ ንጉስ ድርጣድስ ይባላል:: እንዲህ ያለች ብላቴና ወደ ሃገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ መልእክት ላከበት:: ድርጣድስ ምልክት ይዞ ቢያስፈልግ የተባለችውን ብላቴና አገኛት::ከመልኳ ማማር የተነሳ እንደ ፀሐይ ስታበራ አያትና ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ እንደምን ለእርሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን ይኽችን ብላቴና ለ እኔ ለምኚልኝ አላት:: እመ ምኔቲቱም አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ በጀ ይሁን አለችው:: ኋላ ግን አርሴማን ለሰማያዊው መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቼሻለሁና ይህ ርኩስ እንዳያረክስሽ እወቂ አለቻትና አስጠነቀቀቻት:: በፈቃዱ የተስማማች የመሰለው ድርጣድስ ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው:: ንጉስ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት:: ከዚያ አያይዞ መላውን ደናግልና ተከታዮቿን አስፈጅቷቸዋል:: ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ሥራ ማሰራት ኋላም ማስጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውኃ የማይቀምስ ሆነ:: ብላቴኖቹ እንግዲህ እንዲህ ሲሞት እንዴት እናየዋለን ብለው ኃዘኑን አደን ያስረሳዋልና አደን ይዘነው እንሂድ እያሉ ይዘውት ሄዱ:: በዚያው ባለበት ለአደን እንደወጣ እሪያ(አሳማ) ሆኖ ቀርቷ:: ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መላከ እግዚአብሔር ለእህቱ ተገልጾ ከጎርጎርዮስ ዘአርማንያ በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት:: ነገር ግን ድርጣድስ ጎርጎርዮስን በሃይማኖት ምክንያት ተጣልቶት ከአዘቅተ ኹስሕ አስጥሎት ነበርና ከዚያው የሞተ መስሏቸው ደነገጡ:: እርሱን ግን መልአኩ ለአንዲት መበለት ነግሮለት እርሷ አንድ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት አስራ አምስት ዓመት በዚያው ጉድጓድ ኑሯል:: ሠራዊቱም የኒህ የክርስቲያኖች አምላካቸው ጽኑ ነውና ምናልባት በህይወት ይኖር ይሆናል ብለው ከተጣለበት ጉድጓድ ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው:: የገመዱን ሃብል ቢስቡለት ጎርጎርዮስ ከሰል መስሎ ወጥቷል:: የድርጣድስም እህት እባክህ ወንድሜን አድንልኝ ብላ ለመነችው:: እርሱም ወንድምሽ ያለበትን ታውቂዋለሽን አላት አዎን አለችው::አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን አሳዪኝ ብሏት አሳየችውና አጽመ ሰማዕታትን ሰብስቦ በክብር አስቀብሮ ካበቃ በኋላ በዪ ውሰጂኝ ብሏት ይዛው ሄደች:: ወደ እርያነት ከተለወተው ድርጣድስ ፊት ቆሞ አሁን አንተን ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው:: ወአድነነ ርእሶ ወአንገስገሰ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል (እሺ እንደማለት ራሱን ነቀነቀ) ግዕዛኑን(ሰብዓዊ ተፈጥሮውን) ኣልነሳውም ነበርና ይሁን አለውና አዳነው እንዳይታበይ ከእጅ ከእግሩ የእርያ (የአሳማ) ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል:: ከዚያ አስተምሮ ቢያሳምነው አጥምቀኝ አለው መጠመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ ለእኔ ሥልጣን የለኝም ቢለው የአንጾክያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል:: እርሱንም (ጎርጎርያስ ዘአርማንያን ) ተካሶ በሀረሩ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆን አስሹሞታል:: Photo: "ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በማስተዋልም ይጸናል።"ምሳ. 24:3 ፍጥረቱን ሁሉ በድንቅ ችሎታው የፈጠረ እግዚአብሔር የፈጠረውን እያየ የራሱን ሥራ መልካምነት ይመሰክር ነበር ደጋግሞም በኦሪት ዘልደት "እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ" (ዘፍ 1:4,10,12,18,21,25)እያለ ሊቀ ነቢያት ሙሴ መሰከረ :: ነገር ግን የእጁን ሥራ ውጤት ሰውን ከፈጠረ በኋላ የቀድሞውን አገባብ ቀይሮ እጅግ በሚል ቅጽል አሳምሮ የሥራውን መልካምነት እንዲህ ገለጸው "እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። "(ዘፍ 1:31) ታዲያ ግን እኮ ይህን ህንጻ ሥላሴ ለመፍጠር አምላክ አንዳች አልደከመም ሠለስቱ ምዕት በቅዳሴያቸው "ወአመ ፈጠሮ ለአቡነ አዳም አኮ ዘአንሶሰወ ከመ ያምጽእ መሬት ወማየ ነፋሰ ወእሳተ አላ እም መንበሩ ኢተሐውሰ ወኢያንቀልቀለ ፍጹመ ነስአ ዓርባዕተ ጠባይዓ ክልኤተ እምዘይትገሰስ ወክልኤተ እምዘኢይትገሰስ ሠለስተ እምዘይትረአይ ወአሐደ እምዘኢይትረአይ ቦቱ ለሐኮ ወአሰነዮ በእደዊሁ ቅድሳት ሰአሞ ወአፍቀሮ!!!" እንዳሉ ዳሩ ግን በፈጣሪ እጅ የታነጸውና ጽኑ ፍቅሩን ለመግለጽ አፈቀረው ሳመው ተብሎ የተገለጸው ቤት በጥበብ ቢሰራም ማስተዋል ስላጣ አልጸናም ፈረሰ ...... አዎ ፈቃዱን ስሜቱን የማይቆጣጠር ከማስተዋል የሚከለከል ሰው ዛሬም እንዲሁ ይፈርሳል (ምሳ. 25:28 "ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው።"):: ማስተዋል ቤትን ያጸናል! የዋህነትና ቅንነት በማስተዋል ካልተቃኘ ያለዋጋ መትጋት ያለአላማ መጋደል እንዲሁም ተልዕኮ ራዕይና ግብ በሌለው መርኅ በስሜት መነዳት ነው:: አለማስተዋል ምናልባት ከምክር እጦት ሊሆን ይችላል "ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም።" እንደተባለ::(ዘዳ. 32:28 ) ቅዱስ ዳዊት በተሰጠው እድሜ ዘመን ከራሱ ስሜት እና ፈቃድ ይልቅ ያስቀደመው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ማገልገል ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል እንደመሰከረለት "ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥"(ሐዋ.13:36) ብዙዋቻችን ግን በተሰጠን የማለዳ ጤዛ እድሜአችን አለም በፈቃዷ ከተገለገለችብን በኋላ እንሞታለን:: ለምን?......እንጃ! ንጉስ ዳዊት እኮ በራሱ ዘመን እንኳን የዓለምን ፈቃድ ሊያጸና የራሱን ፈቃድ ታግሎ የረታና ከውድቀቱ በጽኑ እንባና ንሰሃ የተነሳ ነገሩን ሁሉ በማስተዋል የሚያከናውን "እንደ እግዚአብሔር ልብ" የተሰኘ ታላቅ ሰው ነው:: በመጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 18 ቁጥር 14 ላይ "ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።" ይለናል:: ለልማዱ እኛም በብሂል "አስተውሎ የሚራመድ ብዙ ርቀት......" እንላለን መጽሐፉም ቢሆን ቀድሞ "የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል።"(ሆሴ. 4:14 )ሲል አስቀምጦታል:: ለምን ያሉ እንደሆነ እንዲጸና ራሱን የሚጠብቅበት ነጻ ፈቃድና የሚያገናዝብበት አመዛዛኝ ህሊና ተሰጥቶት በጥበብ የተሰራው ህዝብ ካላስተዋለ አምላኩ ስለማይራራለት ነው " የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።" (ኢሳ.27:11):: በጊዜ ቅዳሴ ዲያቆኑም "ንኔጽር" እናስተውል የሚለው ለዚህ ነው:: ቀድሞ የተቀመጣችሁ ተነሱ ብሎ "ከአራተ ዝንጋኤው የተቀመጠ በተዘክሮ" ...... "ከአራተ ሐኬት የተቀመጠ በአንክሮ" እንዲነሳና በማስተዋል ወደ ምስራቅ ተመልክቶ ማኅደረ እግዚአብሔርን ህገ ወንጌልን ምዕራፈ ቅዱሳንን መጻዒት መንግስትን እንዲዘክር ያዝዋል:: ታዲያ በማስተዋል ምስራቅን ያላየ ከማኅደረ ዲያቢሎስ ከሙታን ጉባዔ ይጨመራል "ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል።"....... ምሳ 21:16 እንግዲህ ይህን ሁሉ እንድል መነሻ የሆነኝ ዛሬ ዛሬ ብዙዋቻችን ነገሮችን በማስተዋል ከማጤን ይልቅ በየዋህነትና በግዴለሽነት በመመልከት ቀደምት አበው እና እመው ዋጋ ከፍለው ያጸኗትን ነቅ አልባና ፍጽምት የሆነችውን ተዋህዶ ሃይማኖት እንደ እንግዳ ደራሽ..... እንደ ውኃ ፈሳሽ..... እንደወፍ ዘራሽ..... ድንገት ዛሬ ደርሶ ማንም እንደገዛ ፈቃዱ በስሜት በመመራት ያለማስተዋል ለሚያደርጋቸው ስህተቶች መገዛታችን ከምክር እጦት ሊሆን ይችላል ብዬ በማሰብ መረጃው ቢኖረን ምክር ቢለገሰን እናርማለን በሚል ተስፋ ቀጣዩን ሃሳብ በማጤን እንድትከታተሉ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ:: ለዛሬው ቀደም ባሉ ጊዜያት ለመጠቆም ሞክሬ ትችትና ነቀፌታን ካተረፍኩባቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ብቻ በማስረጃ በመደገፍ ላብራራ ::ይሕም ስለ ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ትክክለኛ ሥዕለ አድኅኖ (Iconography) ይሆናል:: በሃገራችን ዛሬ ዛሬ ከነፍሳቸው ይልቅ ለኪሳቸው ያደሩ ነጋዴዎች በዝተው በየመደብሩ ማንኛውም ዘንባባ ጽዋ መስቀል ዓይን..... ይዛ የተሳለችና ከውጪ የመጣች የሴት ሥዕል ከተገኘች በቃ እርሷ ቅድስት አርሴማ ናት! የዋህ የማያስተውል ያልነውም ህዝባችንም ያምናል ይገዛል ይማጸናል..... ታዲያ በልቡ ቅንነት የውስጡ መሻት ሲከናወንለት እናያለን በመጽሐፈ ስንክሳር ይህን የመሰለ የየዋሃን ታሪክ ተቀምጧል አንድ አስከናፍር የተባለ እንደ አርከ እግዚአብሔር አብርሃም እንግዳ ተቀባይ ሰው ነበር 13 ሽፍቶች ሊዘርፉት ወደቤቱ ገብተው ጌታዬን ከነደቀመዛሙርቱ አገኘሁ ብሎ የሽፍቶቹን አለቃ እግር አጥቦ ለዘመናት ከአልካ=ጋ የቀረ ልጁ ላይ የክርስቶስ እግር እጣቢ እንደሆነ በማመን ቢያፈስበት ድኖ ተነስቷል:: ይህ ተአምር በዚያ ዘመን ሊሰርቁ የመጡትን ሽፍቶች ህዝቡ ሁሉ ያለውን እየሰጠ እንዲከተላቸው ምክንያት የፈጠረ እነሱንም "በሃሰት እንዲህ የተደረገልን አምነን ብንጋደልማ ከዚህ በላይ እንዴት ይሳነናል..." ብለው በበረሃ ወድቀው በተጋድሎ ጸንተው በሰማዕትነት ክብር አርፈዋል:: የአስከናፍር እምነቱ ለሽፍቶቹ ተረፈ ...... የኛ እምነትስ? እውነትን እየተፋ ክህደት እያሰፋ የሚዋለደ ውን ነጋዴ ደገፍንበት ....... በተለይ በሥዕላቱ ላይ ባለቤቱ በሌላ ፊደል(ምናልባትም ትርጉሙን በማናውቀው ቋንቋ) ተገልጾ እያለ እኛ ግን ይኼ ምንድነው ? ምን ማለት ነው? ለምን ተጻፈ? መቼ ማን እንዴት ሳለው? ሳንል "ለሰማዕቷ" ካለን ጽኑ ፍቅር የተነሳ ገዝተን እንጠቀምበታለም:: እስኪ አሁን የሚሻለውን ነገር ፈትነን ያለ ነውር እየተመራን ለቅድስቲቱ "ለሰማዕቷ" ያለንን ፍቅር በማስተዋልና በእውቀት እየገለጽን እምነታችንን እናብዛ እናሳድገውም:: ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎኦ እንደ መከረን "ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።"ፊል. 1:9-11 በቅድሚያ ስለ ዘንባባ ጥቂት እንበል ..... ዘንባባ እንደ ቤተክርስቲያናችን ፍቺ የጽኑ እምነት መገለጫ ነው (አቤቱ....እንደሰሌን ስር በልቡና ጽናትና በፍቅር ዝምታ ትከለኝ እንዲል ውዳሴ አምላክ) ዳዊትም በመዝ. 91:12 ላይ "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።" ይለዋል:: ሰሎሞን በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንዲስል የታዘዘው ይህን የጥብዓትና የጽናት ምልክት ዘንባባ ነበር (በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ6 ቁጥር 29 ላይ "በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ።" ዳግመኛም በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5 ላይ "ታላቁንም ቤት በጥድ እንጨት ከደነው፥ በጥሩም ወርቅ ለበጠው የዘንባባና የሰንሰለት አምሳል ቀረጸበት።" ይላል) ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊውም ድል የነሱ ከታላቁ መከራ የመጡ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም ያነጹ ያላቸውን ሲገልጻቸው "ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤"(ራእ. 7:9) ልብ አድርጉ እነዚህ የዘንባባ ዝንጣፊ የያዙት በጣም ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ አንድስ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ይላቸዋል:: በምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ሰፊ ቦታ የሚሰጣቸው አኃትና እመው (አንስት ቅዱሳት) በተለይም ሰማዕታት መስቀልና ዘንባባ ይዘው ይሳላሉ:: ለምሳሌ 1.ቅድስት ማሪና ዘአንጾክያ (በቀጣይ የምናያት በእኛ ሃገር ግን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ እያልን በስህተት የምንጠራት) 2.ቅድስትባርባራ ዘኒቆሚዲያ 3. ቅድስት ሉሲ(ሉሲያ) ዘሰራኩስም 4. ቅድስት አርሴማ ዘአርማንያ 5.ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድሪያ 6. ቅድስት አንስታስያ, ቅድስት ኪርያክ, ቅድስት ማርሴላ(ማርኬላ), ቅድስት ሶፍያ ወዘተ..... ወደፈት ለህዝቡ ከሚደርሱ ሰፊ ሥራዎች ውስጥ በተለይ አንኳር የሆኑ የቅድስት ሉሲንና የቅድስት ባርባራን ሥዕለ አኅህኖ እንድንለይ ቀታዮቸል ነጥቦች እናክልና ለዛሬ ያልኩትን ልቋጭ (በዚህ አጋጣሚ የቅድስት አርሴማን ታሪክ የተጠቀምኩት ከመጽሐፈ ቅዳሴ ትርጓሜ ነው) 1.ቅድስት ሉሲ ከ283-304 እ.አ.አ የኖረች ወጣት ሰማዕት ስትሆን Lucia of Syracuse; Lucia de Syracuse(Lucy of Syracuse), Lucia, Lucy,Santa Lucia(Saint Lucia), or Saint Lukia እየተባለች ትጠራለች ሉሲ ወይም ሉሲያ የሚለው ቃል (luc-lux) ምንጩ ላቲን ሲሆን ትርጉሙም ብርሃን ማለት ነው ...Syracuse(ሲሪያከስ=ሰራኩስም) ደግሞ በዶቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነትን የተቀበለችበት የጣልያን ከተማ ናት ( she was a martyr in Syracuse during the Diocletian persecutions of 304 AD) በቅዱስ መጽፋችን ውስጥ ሰራኩስም ተብሎ ቦታው ተዘግቧል …..በሐዋርያት ሥራ ም.28 ቁ.12 ላይ "ወደ ሰራኩስም በገባን ጊዜ ሦስት ቀን ተቀመጥን፤"( Acts 28:12 And landing at Syracuse, we tarried there three days.) ልዩ መለያዋ ከመከራዋ ጽናት የተነሳ ዓይኗን እንኳ ጎልጉለው ቢያወጡት ብርሃናዊ ዓይን ተሰጥቷት ታይ ነበርና በወርቅ ዝርግ ሳህን ላይ ሁለት ዓይኖቿን እንደያዘች መታየቷ ነው:: (As final torture, her eyes were gouged out. She was miraculously still able to see without her eyes. To this day we see pictures of Saint Lucy holding her eyes on a golden plate. ) ታዲያ ግን ይህ እኛ በብዛት ቅድስት አርሴማ እያልን የምንጠቀምበት ሥዕለ አድኅኖ (Iconography) ነው:: 2. ቅድስት ባርባራ በቤተ ክርስቲያናችን ታህሳስ ስምንት የምትዘከረው የኒቆሚዲያዋ ኮከብ ሰማዕቷ ቅድስት ባርባራ ደግሞ ሌላዋ በገዛ አባቷ እጅ ሰማዕትነትን የተቀበለች እንደነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያሉ ደጋጎች በአርጋኖን ምስጋናቸውላይ የተማጸኑባት(አርጋኖን ዘሰንበት የመጨረሻውን ክፍል ይመልከቱ) በዚሁ ታላቅ ጻድቅ(ዳግማዊ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ = አባ ጊዮርጊስ) ገድል ላይ ከቅዱሳን አንስት ጋር ስሟ የተጠቀሰ የበረከትና የቃል ኪዳን እናት ስትሆን በሥ ዕሏ ላይ ብዙውን ጊዜ ስሟ በግሪክ H AGIA BAPBPA (ኢ አጊያ ባርባራ= ቅድስት ባርባራ) ተብሎ ተጽፎ ይገኛል:: ጽዋና መስቀል ከዘንባባ ጋር ይዛ በመታየቷ እኛ ቅድስት አርሴማ ናት በማለት በብዛት እየተጠበምንበት ያለው ሥዕል ነው:: 3.ቅድስት አርሴማ ዲዮቅልጢያኖስ መልከመልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ቀድሞ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኛላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በየሃገሩ ሰደደ:: በዚህ ጊዜ ይህች አርሴማ ሰባ ሁለት ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣ ነበር:: ሃያ አራቱ ደናግል የቀሩት አርባ ስምንቱ መዓስባን(ያገቡ) ነበሩ:: በወቅቱ የነበረች እመ ምኔቲቱ አጋታ ትባላለች:: የዲዮቅልጢያኖስ ሠራዊት የተባለችውን ብላቴና እየፈለጉ አርሴማ ካለችበት ደረሱ:: ባይዋት ጊዜ በውበጥው ተደንቀው ሥዕሏን ሥለው ወስደው ለንጉሱ ሰጡት:: ዲዮቅልጢያኖስም መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል በሉ ሄዳችሁ እርሷን አምጡልኝ አላቸው:: እርሷም እንዳስፈለጋት አውቃ ተነስታ አርማንያ ወረደች:: እርሱም ከዚያ እንደወረደች አውቆ በወቅቱ የነበረው የአርማንያ ንጉስ ድርጣድስ ይባላል:: እንዲህ ያለች ብላቴና ወደ ሃገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ መልእክት ላከበት:: ድርጣድስ ምልክት ይዞ ቢያስፈልግ የተባለችውን ብላቴና አገኛት::ከመልኳ ማማር የተነሳ እንደ ፀሐይ ስታበራ አያትና ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ እንደምን ለእርሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን ይኽችን ብላቴና ለ እኔ ለምኚልኝ አላት:: እመ ምኔቲቱም አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ በጀ ይሁን አለችው:: ኋላ ግን አርሴማን ለሰማያዊው መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቼሻለሁና ይህ ርኩስ እንዳያረክስሽ እወቂ አለቻትና አስጠነቀቀቻት:: በፈቃዱ የተስማማች የመሰለው ድርጣድስ ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው:: ንጉስ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት:: ከዚያ አያይዞ መላውን ደናግልና ተከታዮቿን አስፈጅቷቸዋል:: ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ሥራ ማሰራት ኋላም ማስጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውኃ የማይቀምስ ሆነ:: ብላቴኖቹ እንግዲህ እንዲህ ሲሞት እንዴት እናየዋለን ብለው ኃዘኑን አደን ያስረሳዋልና አደን ይዘነው እንሂድ እያሉ ይዘውት ሄዱ:: በዚያው ባለበት ለአደን እንደወጣ እሪያ(አሳማ) ሆኖ ቀርቷ:: ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መላከ እግዚአብሔር ለእህቱ ተገልጾ ከጎርጎርዮስ ዘአርማንያ በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት:: ነገር ግን ድርጣድስ ጎርጎርዮስን በሃይማኖት ምክንያት ተጣልቶት ከአዘቅተ ኹስሕ አስጥሎት ነበርና ከዚያው የሞተ መስሏቸው ደነገጡ:: እርሱን ግን መልአኩ ለአንዲት መበለት ነግሮለት እርሷ አንድ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት አስራ አምስት ዓመት በዚያው ጉድጓድ ኑሯል:: ሠራዊቱም የኒህ የክርስቲያኖች አምላካቸው ጽኑ ነውና ምናልባት በህይወት ይኖር ይሆናል ብለው ከተጣለበት ጉድጓድ ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው:: የገመዱን ሃብል ቢስቡለት ጎርጎርዮስ ከሰል መስሎ ወጥቷል:: የድርጣድስም እህት እባክህ ወንድሜን አድንልኝ ብላ ለመነችው:: እርሱም ወንድምሽ ያለበትን ታውቂዋለሽን አላት አዎን አለችው::አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን አሳዪኝ ብሏት አሳየችውና አጽመ ሰማዕታትን ሰብስቦ በክብር አስቀብሮ ካበቃ በኋላ በዪ ውሰጂኝ ብሏት ይዛው ሄደች:: ወደ እርያነት ከተለወተው ድርጣድስ ፊት ቆሞ አሁን አንተን ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው:: ወአድነነ ርእሶ ወአንገስገሰ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል (እሺ እንደማለት ራሱን ነቀነቀ) ግዕዛኑን(ሰብዓዊ ተፈጥሮውን) ኣልነሳውም ነበርና ይሁን አለውና አዳነው እንዳይታበይ ከእጅ ከእግሩ የእርያ (የአሳማ) ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል:: ከዚያ አስተምሮ ቢያሳምነው አጥምቀኝ አለው መጠመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ ለእኔ ሥልጣን የለኝም ቢለው የአንጾክያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል:: እርሱንም (ጎርጎርያስ ዘአርማንያን ) ተካሶ በሀረሩ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆን አስሹሞታል::
Posted on: Wed, 09 Oct 2013 02:11:35 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015