40/60 ቤቶች ምዝገባ ትክክለኛ መረጃ - TopicsExpress



          

40/60 ቤቶች ምዝገባ ትክክለኛ መረጃ ‹‹አንድ ተመዝጋቢ አጭበርብሮ ከተመዘገበ ሲደረስበት በህግ ይጠየቃል›› Featured Written by Web administrator dereje yiemeru font size Print Email Media Rate this item1 2 3 4 5 (0 votes) ኢትዮ-ቻናል፡- ነባር ተመዝጋቢዎች በምን ይረጋገጣሉ? አቶ መስፍን፡- በሁሉም ወረዳዎች ሙሉ መረጃ አለ፡፡ ሌላው፤ በተለያየ መገናኛ ብዙሃንና በእኛ ድረገፅ ከግንቦት 25 ጀምሮ ስለሚለቀቅ ሁሉም ሰው መረጃዎቹን ማግኘት ይችላል፡፡ ኢትዮቻናል፡- በባንክ ቁጠባ ሂሳብ ደብተር ከሌለ መመዝገብ አይቻልም፤ በባንክ በኩል ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል? አቶ መስፍን፡- ከባንክ ጋር ተያይዞ ተደጋግሞ የሚነሳ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ ከንግድ ባንክ ጋር ሁለት አማራጮችን ተነጋግረናል፡፡ አንደኛው፤ የተለመደውን የቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ወደ ድጎማ ፕሮግራም ማዞር ይቻላል የሚል ነው፡፡ ስለዚህ፤ የዝግ ሂሳብ አገልግሎት እስኪጀመር ድረስ በኖርማል ቁጠባ መደበኛና የዕለት ተዕለት ስራው ስለሆነ ባንክ አትቆጥቡ አይልም፡ ፡ ቁጠባው ይደረጋል፤ ፕሮግራሙ ሲጀመር ወደ ዝግ ሂሳብ ማዞር ስለሚቻል ማንኛውም ሰው ለቤት ልማት ፕሮግራም ነው ለሌላም ነው ሳይል መቆጠብ ይችላል፡፡ ዝቅተኛውን የቁጠባ መጠን በአካውንቱ ይዞ ከመጣ ግን ወደ መዝገባው ይሄዳል፡፡ የአካውንት ቁጥሩ ከባህር መዝገቡ ጋር ስለሚተሳሰር ወደ ዝግ ሂሳብ ማዞር ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ በኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስትር አማካይነት ለሁሉም ባንኮች ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይሄ በአጭር ጊዜ የሚፈታ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ማንኛውም ሰው በመደበኛ ቁጠባ ቆጥቦ መመዝገብ የሚቻልበት እድል ክፍት ነው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- 40/60 እና የማህበራት ምዝገባ አፈፃፀም ልዩነት ይኖረዋል? አቶ መስፍን፡- ቀድሞ እየሄደ ያለው የኮንዶሚኒየም ቤት ምዝገባ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ የበሰለ መረጃ ማግኘት ይጠቅማል፡፡ ነገር ግን ከአጠቃላይ ስራው አንፃር 40/60 ወይም ማህበራት ምንድነው? የሚለውን ዜጎች ፍላጎታቸውን ወስነው እንዲዘጋጁ ለማድረግ አሁን መረጃ እየሰጠን ነው ያለነው እንጂ እያንዳንዱ ባለቤት አለው፡፡ 40/60 የሚመዘገበውና መመሪያ የሚያዘጋጀው ንግድ ባንክ ነው፡፡ ለዚህ ዝርዝር ነገር ባንክ በየጊዜው መግለጫ እየሰጠበት ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከእኛ ስራ ጋር የሚያስተሳስራቸው ዋና ዋና መረጃዎችን ነው፡፡ ይህንንም፤ ለህብረተሰቡ እያቀረብን ነው፡፡ 40/60 ወይም በማህበራት ምን ማሟላት አለበት? የሚሉት፤ ተመሳሳይ ግዴታዎች ስላሉት፤ እነዚያን ግዴታዎችን የማሳወቅ ጉዳይ ነው በዋናነት እየሰራን ያለነው፡፡ ይሄ በተከታታይ ስራ መዳበር እንዳለበት ለመናገር ነው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ቁጠባ ያላቸው ሰዎች በምን ሁኔታ ይስተናገዳሉ? አቶ መስፍን፡- ቁጠባ ማካሄድ የሚቻለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ነው፡፡ መመሪያው ሲወጣ የነበረው ሃሳብ በንግድ ባንክ በኩል ይሄን ያህል ኃይል ለማስተናገድ እቸገራለሁ የሚል ነበር፡፡ ስለዚህ፤ አንድ አማራጭ ያቀረብነው የአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋምን የዚህ የቁጠባ አካል እንዲሆን ነበር፡፡ በመጨረሻ ላይ ከአስተዳደር አንፃር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ታሳቢ ተደርገው በንግድ ባንክ ብቻ ቁጠባ እንዲደረግ የሚል ስምምነት ተደርሷል፡፡ ስለዚህ፤ በንግድ ባንክ ባሉት በሁሉም ቅርንጫፎች መቆጠብ ይቻላል፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- የአዲስና የነባር ተመዝጋቢዎች የቁጠባ ብር መጠን ለምን ተለያዩ? አቶ መስፍን፡- ልዩነት የፈጠረው የዓመታት ልዩነት ነው፡፡ ነባሩ የሚቆጥበው እስከ አምስት ዓመት ነው፡ ፡ አዲሱ የሚቆጥበው ሰባት ዓመት ነው፡፡ ስለዚህ፤ ተመሳሳይ ብር በሰባትና በአምስት ዓመት መቆጠብ ስለሌለበት የማስተላለፊያ ዋጋዎች ላይ ልዩነት ቢኖረውም መነሻው የቁጠባ መጠን በዝርዝር ተሰልቶ የተቀመጠ ነው፡፡ ሰባት ዓመት የሚቆጥብ ሰው መጠኑ ቀለል ይላል፡፡ አምስት ዓመት የሚቆጥብ ሰው በተመሳሳይ ለአምስት ዓመት የተሰራውን ስሌት ይከፍላል፤ ትንሽም ይጨምራል፡፡ ይሄን የቁጠባ ዓመቱ የሚፈጥረው ውጤት ነው እንጂ ከቤቶቹ ዋጋ፣ ጥራትና ከካሬ ሜትር ስፋትና መጥበብ ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- የሚቋቋሙ የመመዝገቢያ ጣቢያዎች በመንግስት ተቋማት ዝርዝር ውስጥ የሌሉ አሉ፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? አቶ መስፍን፡- መመሪያዎቹ ሲዘጋጁ ያልተካተቱ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ፤ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የለም፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ ደግሞ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የለም፡፡ ስለዚህ ይሄንን በልዩ መመሪያ እያስተካከልን፤ የተጓደሉትን ለማሟላት ጥረት አድርገናል፡፡ ከየተቋማቶቹ የምዝገባ አስተባባሪዎች ሁለት ዙር ኦሬንቴሽን ተሰጥቷቸዋል፡ ፡ የምዝገባ ጣቢያዎች የምናደራጅበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ማዘጋጃ ቤት ራሱን ችሎ እንዲሄድ አድርገናል፡፡ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንም በጣም በርካታ የሰው ኃይል ስላለው በተመሳሳይ ራሱን ችሎ ምዝገባ እንዲያደርግ ነው እያሰብን ያለነው፡፡ ስለዚህ ችግሩ የሚፈታበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- በመንግስት የልማት ተቋማትና የግል ድርጅቶች ያሉ ሠራተኞች እንዴት ይስተናገዳሉ? አቶ መስፍን፡- የመንግስት ልማት ድርጅቶችና የግል ተቋማት በወረዳ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ በርካታ የመንግስት የልማት ተቋማት ድርጅቶች አሉ፡፡ በተመሳሳይ፤ በዚህ ከተማ ስፍር ቁጥር የሌለው የግል ድርጅቶች አሉ፡፡ ለሁሉም ይሄን ዕድል መስጠት ማለት ለማስተዳደርም አይመችም፡፡ በእያንዳንዱ ተቋም ኔትወርክ ለመዘርጋት በጣም ውድ ነው፡፡ ከአቅም በላይ ነው የሚሆነው፡፡ እኛ የምንጠቀመው የወረዳ ኔት ፕሮግራም ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከዚህ ፕሮግራም ውጭ የራሱ ተቋማት ጭምር አሉ፡፡ ስለዚህ፤ ይሄ ለአስተዳደርም ሆነ ለሌሎች የመረጃ መረብ ዝርጋታዎች አስቸጋሪ ስለሆነ በዚህ ፕሮግራም ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ነገር ግን እንደ ዜጋ የመመዝገብና ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ የቆዩት ጭምር መስተናገድ የሚችሉበት ሰፊ ዕድል የተፈጠረበት ሁኔታ አለ፡፡ በተቋምም ሆነ በወረዳ የተመዘገበ በየትኛውም መንገድ ልዩነት የለውም፡፡ የመንግስት ሰራተኛውን የሚያጣራው (filter) የሚያደርገው ራሱ ሶፍትዌር ነው፡፡ ለምሳሌ፤ 30 በመቶ ዕጣ በማውጣት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ እስከ አሁን ዕጣ ከወጣው ውስጥ 56 በመቶ ተጠቃሚ የሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ ይሄ ሶፍትዌር፤ ፕሮግራሙ ራሱ እዚያ ሲወጣ ሴቶችን filter ያደርጋል፡፡ የመንግስት ሰራተኛውም በባህር መዝገቡም ላይ ሆነ ቅፁም ላይ ሲሞላ የመንግስት ሰራተኛ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ፤ ዕጣ የማውጣት ሂደት 20 በመቶ ተግባራዊ የሚሆንበት ሂደት በቀጥታ ከዳታ ቤዝ ውስጥ ማውጣት ስለሚቻል ወረዳም ሆነ ተቋምም የተመዘገበ ወደ አንድ ማዕከል ዳታ ቤዝ ስለሚመጣ ክፍተት የለውም፡ ፡ ማኔጅ ማድረግ እንችላለን፡፡ ለዚያም ነው እነዚህን አማራጮች እየፈጠርን ያለነው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- በመንግስት ተቋማት ምዝገባ ማካሄድ የሚቻለው 10/90 እና 20/80 ብቻ ነው ይባላልና እውነት ነው? አቶ መስፍን፡- በተቋማት ምዝገባ ላይ ሁለት መንገድ ነው፡፡ አንዱ ማህበራት መመዝገብ ይችላሉ፡ ፡ ማህበራት ተመዝግበው ወደዚህኛው መምጣት ይቻላል፡፡ ከምንም በላይ ግን ሰፊ ትኩረት የተሰጠው የኮንዶሚኒየም በተናጠል የሚደረጉ ምዝገባዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ በተናጠል የሚደረጉ ምዝገባዎች፤ ነባር የመንግስት ሰራተኛም ቢሆን የሚመዘገበው ወረዳ ነው፡፡ ነባር የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ መረጃዎቹና ሌሎቹ የምዝገባ ስርዓቶቹ የሚፈፀሙት በወረዳ ነው፡፡ በተቋማት አዲስ ተመዝጋቢ ብቻ ነው የሚመዘገበው፡ ፡ ይሄ በግልፅ መታወቅ አለበት፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- የተመዘገበ ሰው መረጃ ስለትክክለኛነቱ እንዴት ይረጋገጣል? አቶ መስፍን፡- በየምዝገባ ጣቢያዎች መረጃዎች ይኖራሉ፡፡ በተለያዩ ድረ-ገፆች መረጃዎች እንለቃለን፡፡ ይሄ ትልቅ አማራጭ ነው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- የመንግስት ሠራተኞች አማራጭ ካላጣ በስተቀር በየወረዳው መመዝገብ የለባቸውም እየተባለ ነው፤ ከሚፈጠረው መጨናነቅ ለመቀነስ የመንግስት ሰራተኞች ምዝገባ በሚሰሩበት ተቋማት ብቻ ነው ማለት ነው? አቶ መስፍን፡- ሁለቱም ጋር መመዝገብ ለፕሮግራሙ ምንም ልዩነት እና እስከሌለው ድረስ እግር መንገዱን ቅዳሜ እሁድ ቤቱ ሲውል መመዝገብ ይችላል፡ ፡ ቅዳሜም፤ እሁድም ምዝገባ አለ፡፡ ‹‹በመንግሥት ተቋም ብቻ መመዝገብ አለብኝ›› የሚል ካለም ምርጫው እናስፋለት ነው፡፡ አማራጮችን ከማስቀመጥ በስተቀር ሌላ ልዩነት የለውም፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- በአዲስ አበባ ከሁለት ዓመት በላይ ኖረው መታወቂያ የሌላቸው እንዴት ይስተናገዳሉ? አቶ መስፍን፡- ትክክል ነው! አምስትም፣ ስድስት ዓመትም ኖረው ግን መታወቂያ የሌላቸው አሉ፡ ፡ በምዝገባው ብቸኛው መንገድ መታወቂያ ብቻ ነው አላልንም፡፡ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አለ፡፡ ይሄ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መታወቂያ የሌላቸው ነገር ግን በነዋሪነት የሚታወቁ፣ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ያላቸው ሌሎች ማረጋገጫዎችን እየተጠቀመ የሚያስተናግድባቸው አሠራሮች በጋራ እየተፈጠረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከመታወቂያ ጋር ተያይዞ ሰዎች መልቀቂያ ይዘው ሲመጡ በቤተሰብ ቅፅ በማህደር ውስጥ ይኖራሉ፤ መታወቂያ ባይኖራቸውም እነዚህንና ሌሎች አማራጮች የማጣራት ሥርዓት በየወረዳው የሚሰራበት ስለሆነ እነዚህ በከተማው ውስጥ እየኖሩ ያሉ ዜጐች ተጠቃሚነታቸውን የሚያሳጣ አይደለም፡፡ ሌላውና ወሳኙ ጉዳይ የመዝጋቢው አካል የማጣራት ብቃት አይደለም፡፡ በዋናነት ተመዝጋቢው አካል የሞላቸው እያንዳንዱ ነገሮች ስለትክክለኛነታቸው አምኖ፤ ፈርሞ ነው የሚያስገባው፡፡ ሁለት ወር ሆኖት፤ ሁለት ዓመት ነኝ ብሎ በተጭበረበረ መንገድ ይዞ የሚመጣው ነገር ካለ በማጥራት ሂደት ሲደረስበት በህግ ይጠይቃል፡፡ ሌሎች ጥቅሞችንም ያጣል፡፡ ይህንን በደንብ አውቆ፤ አምኖ ነው የሚገባው፡፡ ዋነኛው ተጠያቂነት፣ ያለው ተመዝጋቢው ላይ ነው፡፡ መዝጋቢው ላይ አይደለም፡ ፡ መዝጋቢው በመመዝገብ ሂደት እያወቀ የፈፀማቸው ጥፋቶች ካለ ይጠየቃል፡፡ ስለዚህ፤ ትልቁ ተመዝጋቢው ሲመጣ መዝጋቢውን አካል፣ ላታልለው፣ ልሸውደው፣ ላጭበርብረው እችላለሁ ብሎ ሳይሆን ማሰብ ያለበት ከራሱ ጋር የተገናኘ ትልቅ ኃላፊነት በላዩ ላይ ተጭኖበታል፡፡ የሌለው እንዳለ አድርጐ፤ የተመዘገበ ሰው በቀጥታ ከምዘገባ በኋላ፤ በምዝገባ ሂደትም እየተጣራ ሲደረስበት ወንጀሉ የእሱ ነው፡፡ ስለዚህ፤ ይሄንን አምኖ ነው የሚመዘገበውና ትልቁ ነገር በዚህ ሂደት መታሰብ አለበት፡፡ ከዚህ ውጭ ቤት እና መሬት እያላቸው የተመዘገቡ ሰዎች ካሉ አሁን በከተማ ደረጃ የReal property Registration ሥራ በዘመናዊ መረጃ፤ በውጭ ኮንስልታት እየተሠራ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ፤ እያንዳንዱ ቤት፤ መሬት የማነው? የሚለውን ልቅም ያለ መረጃ ከ170 በላይ ከተሞች እየተሠራ ነው፡፡ ሀቁን ሀብቱን ሊክድ የሚችልበት ዕድል አይኖረውም፡ ፡ ስለዚህ፤ ያን ያህል የተወሳሰበ ነገር ውስጥ ወንጀል ለመሥራት የሚጥር ሰው አይኖርም አይባልም፡ ፡ በማጣራት ሂደት ግን ይሄ ወንጀል ኃላፊነቱ የተመዝጋቢው ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ በሌላው አካል በሚደረጉ ቁጥጥርና ፖሊሲ ብቻ መከታተልም ስለማይቻል ነው፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- ሁለት እጮኛሞች በየራሳቸው ተመዝግበው ቆይተው ትዳር ቢመሰረቱና ቤት ቢደርሳቸው እንዴት ይስተናግዳሉ? አቶ መስፍን፡- ሁለት እጮኛሞች ከተመዘገቡ በኋላ ቢጋቡ የሚለው መልካም ነገር ነው፡፡ ከተጋቡ በኋላ ግን ቤት የማግኘት ዕድላቸው አንድ ነው፡፡ ምዝገባው ላይ ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ከሁለት አንዱ ከደረሳቸው ሁለተኛው ሰው ድጋሚ ሲደርሰው ሲጣራ ሌላ ዕድል ስላገኙ ይሰረዛል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ፤ምዝገባውን መመዝገብ የጋብቻው ሁኔታ፣ አስተማማኝ ካልሆነ የሚከለክል ነገር የለም፡፡ ስለዚህ በማጣራት ሂደት ይሄ ሊስተካከል ይችላል፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- ህዝቡ እንዴት ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይቻላል? አቶ መስፍን፡- ያገኘናቸውን አማራጮች ሁሉ መጠቀም አለብን፡፡ በተለያዩ መድረኮች ከህብረተሰቡ ጋር መወያየት አለብን፡፡ የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር ተወያይተን ኃላፊነቱን ወስደው መስራት አለባቸው፡፡ በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ህብረተሰቡን ግንዛቤ መፍጠር አለብን፡፡ ይሄ በቂ ስለማይሆን በምዝገባ ጣቢያ ሲመጡ ገለፃ የሚሰጥ ሰው በበቂ ሁኔታ አዘጋጅተናል፡፡ በበቂ ሁኔታ ለመሥራት ጥረት እናደርጋለን፡፡ ኢትዮ-ቻናል፡- የቤቶች ጠቅላላ ክፍያ ካሬ ሜትር ስፋት አልተገለፀም? አቶ መስፍን፡- ለህዝብ የተገለፀው ዝርዝር የያዘ ሰንጠረዥ፤ ከመመሪያው ጋር የተለያዩ የሚመስሉ ነገሮች አሉ፡፡ ይሄ የምዝገባ መመሪያ ከፀደቀ በኋላ የወጡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያወጣቸው cost build up ነው የወጣው፡፡ ስለዚህ፤ ያለው ልዩነት 10/90 በመመሪያው ሁለት ዓመት ይኖርበታል፡፡ 24.2. ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነ በህግ ችሎታ ያለው ተመዝጋቢ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ የነዋሪነት ወቅታዊ መታወቂያ በመያዝ መዝጋቢው አካል ዘንድ በግንባር ቀርቦ አግባብ ባለው የምዝገባ ቅፅ መሠረት መመዝገብ አለበት፡፡ 24.3 ማንኛውም ተመዝጋቢ በምዝገባ ሂደት ሕገ- ወጥ ድርጊቶችና ከመመሪያው ውጭ እየተፈጸሙ ያሉ ተግባራቶች ካጋጠሙት ጉዳዩን ለመዝጋቢው አካል የመጠቆም ኃላፊነት አለበት፡፡ 24.4 ማንኛውም ተመዘጋቢ በቤት ልማት ፕሮግራሙ ላይ መመዝገብ የሚችለው ካሉት ፕሮግራሞች በአንዱ ብቻ ነው፡፡ ተደጋጋሚ ምዝገባ ከተገኘበት ከሁሉም ይሠረዛል፡፡ 24.5. ተመዝጋቢው የቤት ልማት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆን የቅድሚያ የቁጠባ ሒሳብ ደብተር ከመክፈት ባሻገር በተከታታይ በየወሩ በመመሪያው በተቀመጠው መሠረት መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ 24.6 ማንኛውም ተመዝጋቢ በኤጀንሲው ወይም ኤጀንሲው በሚወክለው አካል ቀርቦ የጣት አሻራ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ 26. አቤቱታ የማቅረብ መብት ማንኛውም ተመዝጋቢ ከምዝገባ ሂደቱ ጋር ተያይዞ እንዳልመዘገብ ተከልክያለሁ ወይም ከምዝገባ ያለአግባብ ተሰርዣለሁ ወይም በአዋጁና በመመሪያው የተሰጠኝን መብት እንዳጣ ተደርጌአለሁ የሚል ከሆነ አቤቱታውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በወቅቱ የማቅረብ መብት አለው፡፡ 27. ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ 27.1. በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚደራጀው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሰየሙ ሦስት አባላት ይኖሩታል፣ 27.2. የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት አወቃቀር፡- ሀ. በክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሰየም..... ሰብሳቢ ለ. በክፍለ ከተማው የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት የሚወከል... አባል ሐ. ከክፍለ ከተማው ቤቶች ልማት አስተዳደር የሥራ ሂደት የሚወክል... አባልና ፀሐፊ 27.3. መዝጋቢው አካል በሚሰጣቸው የምዝገባ ውሳኔዎች ቅሬታ ያደረበት ማንኛውም ተመዝጋቢ እንዳልመዘገብ ተከልክያለሁ ወይም ከምዝገባ ያለአግባብ ተሰርዣለሁ ካለ ቅሬታውን በቃል ወይም በጽሑፍ በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚደራጀው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፣ 27.4. የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔዎችን የሚሰጠው ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ብቻ መመሪያውን ተከትሎ ይሆናል፡፡ 27.5. ቅሬታውን የማጣራት ሥራ በሚከተለው አግባብ መከናወን ይኖርበታል፡- ሀ. እንደ አስፈላጊነቱ ከባለጉዳዩ ጋር በመወያየት፣ ለ. ቅሬታውን ፈጥረዋል ተብሎ ቅሬታ ከቀረበበት መዝጋቢ አካል ጋር ወይም ቅሬታ በተፈጠረበት አካባቢ በግንባር በመቅረብ፣ ሐ. አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ በማዘዝ ወይም በመመርመር ሊያጣራ ይችላል፤ 27.6. የኮሚቴው ውሳኔ የአብላጫ ድምጽ ስርዓት የሚከተል ይሆናል፤ 27.7. ኮሚቴው ለቀረበለት አቤቱታ መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጣራት ቅሬታው በቀረበለት በ5 ቀን ውስጥ ውሳኔውን በፅሁፍ ለቅሬታ አቅራቢው ይሰጣል፡፡ ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል፡፡ 27.8. የኮሚቴው የቆይታ ጊዜ የምዝገባ ሂደቱ በይፋ መዘጋቱ ከተገለፀበት ከአምስት የሥራ ቀናት በኋላ ለኤጀንሲውና ለአስተዳደሩ ሪፖርት በማቅረብ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ 27.9. ኮሚቴው ያለአግባብ በሚሰጠው ውሳኔ በጋራም ሆነ በተናጠል በህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 27.10. ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችና ወጪዎች በኤጀንሲው በኩል የሚሸፈን ይሆናል፡፡ 27.11. ከምዝገባው መጠናቀቅ በኋላ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በመደበኛው የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ክፍሎች የሚታይ ይሆናል፡፡ ክፍል ሰባት ልዩ-ልዩ ድንጋጌዎች 28. የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ይህን መመሪያ ከማስፈጸም አኳያ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡ 29. ቅጣት 29.1. ማንኛውም ተመዝጋቢ በአዋጁና በዚህ መመሪያ የተዘረዘሩትን አንቀፆች በመተላለፍ የተመዘገበ፣ ለመመዝገብ የሞከረ፣ ያሳሳተ፣ የምዝገባውን ሒደት ያወከ እንደሆነ በአዋጁ ቁጥር 19/1997 አንቀጽ 20 ላይ በተቀመጠው መሰረት በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነታቸው ወይም ይበልጥ ማስቀጣቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፤ 29.1.1. ሐሰተኛ ሰነዶችን መፍጠር፣ ሰነዶችን ወደ ሐሰተኛነት መለወጥና በማጥፋት ወይም መታወቂያ ወይም እውነተኛ በሆነው ማህተም ያለአግባብ የሰራበት ወይም በመጠቀም የመዘገበ ከሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 364፣ 375 (ለ) (ሐ) (መ)፣ 376፣ 378 እና 379/1 (ሀ) (ለ)፣ 29.1.2. በዚህ መመሪያ ከተደነገገው ውጭ በቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ውስጥ ለመመዝገብ ለራሱ ወይም ለትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ መስሪያ ቦታ እያለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በሰጦታ ለሶስተኛ ወገን መብቱን ያስተላለፈ ወይም ከዚህ ቀደም የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ተጠቃሚ የሆነ እና ካሉት የቤት ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ የተመዘገበ እንደሆነ እንዲሁም በዚህ መመሪያ በአንቀጽ 12 የተከለከሉ ድርጊቶችን በመተላለፍ ጥቅምን ወይም ያለአግባብ መበልፀግን ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ወይም በማጭበርበርና በማታለል ማስረጃ የሰጠ ማንኛውም አካል ወይም የመዘገበ እና የተመዘገበ ከሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 386፣ 389፣ 663፣ 692 እና 699፣ 29.1.3. በወንጀል ሕጉ መሰረት ከመንግስት ሥራ ጋር በተያያዘ ጉቦ በመስጠት፣ የማስመዝገብ ግዴታን የሚመለከቱ ድንጋጌ በመጣስ እና የመንግስት ሥራን ማሰናከልና የመተባበር ግዴታን የጣሰ ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 427፣ 434 (1)(2) እና 438፤ 29.1.4. ተመዝጋቢው የፈጸማቸው ጥፋቶች ቀላል ጥፋቶች ከሆኑ በመንግስት መስሪያ ቤት ላይ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ላይ በተገለጹት የደንብ መተላለፍ ወንጀሎች አንቀጽ 803 እና 804 መሠረት ተከሶ እንዲቀጣ ይደረጋል፡፡ 29.2. በዚህ መመሪያ የተጣለውን ግዴታ ያልተወጣና ክልከላዎችን የጣሰ ማንኛውም አስፈጻሚና ፈጻሚ ሠራተኛ ወይም የሥራ ኃላፊ ከሆነ በአዋጁ ቁጥር 19/1997 አንቀጽ 20 ላይ በተቀመጠው መሰረት በሀገሪቱ የወንጀለኛ ህግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነታቸው እንደጠበቁ ሆኖ 29.2.1. በዚህ መመሪያ የተጣለውን ክልከላ፣ ግዴታ እና ኃላፊነት ያልተወጣ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ወይም ኃላፊ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር መንግስት ሠራተኞች አዋጅ እና በአቤቱታ ቅሬታ አፈታት ሥርዓት እና ተጠያቂነት ደንብ ቁጥር 48/2004 መሠረት በዲሲፕሊን ቅጣት ይቀጣል፣ 29.2.2. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 411-419 መሠረት ከሚያስቀጡት ሁኔታዎች ውጭ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት ለመፈጸም ሲል በተሰጠው ስልጣን ያለአግባብ የተገለገለ እንደሆነ በወንጀል ሕጉ ደንብ መተላለፍ አንቀጽ 798 መሠረት ክስ ይመሰረትበታል፣ 29.2.3. የመንግስት ሠራተኞች በመንግስት ሥራ ላይ ለሚፈጽሙአቸው ጥፋቶች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 407፣ 409፣ 411 እና 416 በተለይ በአንቀጽ 418 አለአግባብ የመዘገበ እንደሆነ እንዲሁም ከኤጀንሲው የኮምፒዩተር ዳታና የመረጃ ደህንነትን በመጣስ የሚፈፀም ጥፋት በወንጀል ሕጉ 706 እና 707 መሠረት ክስ ተመስርቶ እንዲቀጣ ይደረጋል፡፡ 30. አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የቤት ፈላጊዎች ገቢ አጣሪ ኮሚቴ 30.1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ (8.1) የ10/90 ወይም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የቤት ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ገቢ እየመረመረ ውሳኔ የሚሰጥ ጊዜያዊ ኮሚቴ በወረዳ ምዝገባ ጣቢያ በወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሰየሙ አራት አባላት ያሉት ኮሚቴ ይደራጃል፤ 30.2. የገቢ አጣሪ ኮሚቴ አባላት አወቃቀር ሀ. በወረዳ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሰየም....................... ሰብሳቢ ለ. ከወረዳው ወጣት ፎረም የሚወክል....................... አባል ሐ. ከወረዳው ሴት ፎረም የሚወክል....................... አባል መ. ከወረዳው ነዋሪዎች ፎረም የሚወክል....................... አባል ሠ. ከወረዳው የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ ቤት....................... አባልና ፀሐፊ 30.3. ከኮሚቴው አባላት አብዛኞቹ በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፣ 30.4. የኮሚቴው ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው፤ ሆኖም ድምጽ እኩል ለእኩል ከተከፈለ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፤ 30.5. ኮሚቴው አነስተኛ ገቢ ያለውን ቤት ፈላጊ ማስረጃ በመቀበልና በመመርመር በመመሪያው አንቀጽ 8 (8.1.2) አግባብ አጣርቶና ለይቶ አነስተኛ ገቢ ያለው መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ውሳኔውን በቃለ- ጉባኤ አስፍሮ አነስተኛ ገቢ ያለውን ቤት ፈላጊ በኮሚቴው ሰብሳቢ አማካኝነት በጽሑፍ አረጋግጦ ለመዝጋቢው አካል ይልካል፣ በውሳኔው ላይ የሃሳብ ልዩነት ያለው የኮሚቴ አባል የልዩነቱን ምክንያት በማብራራት ቃለ-ጉባኤ ላይ እንዲሰፍር ይደረጋል፣ 30.6. የኮሚቴው ስልጣን በመስፈርቱ መሠረት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የቤት ፈላጊዎች ገቢ በማረጋገጥ ለመዝጋቢው አካል ማስተላለፈ ብቻ ነው፣ 30.7. ኮሚቴው ያለአግባብ በሚሰጠው ውሳኔ በጋራም ሆነ በተናጠል በህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ 30.8. የኮሚቴው የቆይታ ጊዜ በከተማው የስትሪም ኮሚቴ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 31. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡ 32. መመሪያ የማሻሻል ስልጣን ይህን መመሪያ ማሻሻል ሲያስፈልግ በከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወይም ከንቲባው ሊሻሻል ይችላል፡፡ 33. መመሪያ የሚፀናበት ጊዜ ይህ መመሪያ በከንቲባው ተፈርሞ ከወጣበት ህዳር 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡ ኩ ማ ደመቅሳ የአ ዲ ስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲba 7. ለምዝገባ ብቁ ስለመሆን ማንኛውም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ 7.1 ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ 7.2 በከተማዋ ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የኖረና እየኖረ ያለ፣ 7.3 የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በሥራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ማስረጃው ቦታውን ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ማስረጃ ካቀረበ ለምዝገባ ብቁ ይሆናል፡፡ 8. የምዝገባ መስፈርት በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 7 ሥር የተዘረዘሩት እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ተመዝጋቢ፤ 8.1. የ10/90 ወይም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የቤት ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች 8.1.1. በራሱም ሆነ በሚያስተዳድረው ቤተሰብ ከሚገኝ ገቢ በየወሩ ብር 187 መቆጠብ እንደሚችል የግዴታ ውል መግባት ይኖርበታል፡፡ 8.1.2. በንዑስ አንቀጽ 8.1.1 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ አነስተኛ ገቢ ያለው ስለመሆኑ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ተቀጣሪ ከሆነ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የገቢ መጠኑና የገቢ ግብር ስለመክፈሉ የሚያሳይ ማስረጃ የሚያቀርብ፣ ተቀጣሪ ካልሆነ ከሚኖርበት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በየወሩ 187 ብር የመቆጠብ አቅም እንዳለው የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርብ፤ በህዝብ መድረክና በተለያዩ አደረጃጀቶች በኮሚቴው እንዲጠራ ይደረጋል፡፡ ስሙ በህዝብ ማስታወቂያ ተለጥፎና አስተያየት ተሰጥቶበት ገቢው ዝቅተኛ ስለመሆኑ በአንቀጽ 30 መሠረት የገቢ በአጣሪ ኮሚቴው ተጨማሪ ማጣራት ይደረጋል፡፡ 8.1.3. ለተመዘገበበት መኖሪያ ቤት በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.3 በተገለጸው መሰረት በቅድሚያ የባንክ ቁጠባ የጀመረና ለዚህም የባንክ የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ያለው መሆን ይኖርበታል፤ 8.1.4. በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሌለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን መብቱን ያላስተላለፈ ወይም ከዚህ ቀደም የኮንዶኒየም ቤት ዕጣ ተጠቃሚ ያልሆነ መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ መግባት አለበት፡ ፡ 8.1.5. በቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ከአንድ ጊዜ በላይ ያልተመዘገበ መሆን ይጠበቅበታል፤ 8.1.6. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ወቅታዊ የነዋሪነት መታወቂያ በአካል ይዞ መቅረብ አለበት፤ 8.1.7. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 7.3 የተገለጸው እንደጠበቀ ሆኖ ምዝገባው በሚካሄድበት ወቅት በአካል መቅረብ ካልቻለ ህጋዊ ውክልና በማቅረብ በህጋዊ ወኪሉ አማካኝነት መመዝገብ ይችላል፡፡ 8.1.8. ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ፍላጐቱንና ግዴታዎችን በዚህ መመሪያ በአባሪ በተያያዘው ቅጽ 003 መሰረት ግዴታ ሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡ 8.2. ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት የቤት ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች 8.2.1. ቀደም ሲል በተካሄደው ምዝገባ ተመዝግቦ ስሙ በመረጃ ቋት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፤ 8.2.2. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8.2.1 ቢኖርም በተጠባባቂነት ዕጣ ወጥቶላቸው ነገር ግን ቤቱ ሳይደርሳቸው ስማቸው ከመረጃ ቋት ውስጥ የወጡ ተመዝጋቢዎች ስማቸውን ከተጠባባቂዎች ስም ዝርዝር ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ 8.2.3. ለተመዘገበበት መኖሪያ ቤት በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.1 በተዘረዘረው መሰረት በቅድሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጠባ መጀመሩን የሚያሳይ የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 8.2.4. በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሌለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን መብቱን ያላስተላለፈ ወይም ከዚህ ቀደም የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ተጠቃሚ ያለመሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ መግባት አለበት፡፡ 8.2.5. በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛውና በሚያስተዳድረው ቤተሰብ የሚያገኘውን ጠቅላላ ወርሃዊ ገቢ በትክክል መግለጽ ይኖርበታል፤ 8.2.6. በቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ከአንድ ጊዜ በላይ ያልተዘመገበ መሆኑን ማረጋጥና ግዴታ መግባት ይጠበቅበታል፤ 8.2.7. የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ የነዋሪነት ወቅታዊ መታወቂያ በአካል ይዞ መቅረብ አለበት፤ 8.2.8. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 7.3 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ምዝገባው በሚካሄድበት ወቅት በአካል መቅረብ ካልቻለ ህጋዊ ውክልና በማቅረብ በህጋዊ ወኪሉ አማካኝነት መመዝገብ ይችላል፡፡ 8.2.9. ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ፍላጐቱንና ግዴታዎችን በዚህ መመሪያ በአባሪ በተያያዘው ቅጽ 001 መሰረት ሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡ 8.3 አዲስ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች 8.3.1. ለሚመዘገብበት መኖሪያ ቤት በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.2 በተዘረዘረው መሰረት በቅድሚያ የባንክ ቁጠባ መጀመር ይኖርበታል፤ 8.3.2. በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም በከተማው ውስጥ የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሌለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን መብቱን ያላስተላለፈ ወይም ከዚህ ቀደም የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ተጠቃሚ ያለመሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ መግባት አለበት፡፡ 8.3.3. በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛውና በሚያስተዳድረው ቤተሰብ የሚያገኘውን ጠቅላላ ወርሃዊ ገቢ በትክክል መግለጽ ይኖርበታል፤ 8.3.4. በቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ከአንድ ጊዜ በላይ ያልተዘመገበ መሆን ይጠበቅበታል፤ 8.3.5. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ወቅታዊ የነዋሪነት መታወቂያ በአካል ይዞ መቅረብ አለበት፤ 8.4.5. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 7.3 የተገለጸው እንደጠበቀ ሆኖ ምዝገባው በሚካሄድበት ወቅት በአካል መቅረብ ካልቻለ ህጋዊ ውክልና በማቅረብ በህጋዊ ወኪሉ አማካኝነት መመዝገብ ይችላል፡፡ 8.4.6. ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ፍላጐቱንና ግዴታዎችን በዚህ መመሪያ በአባሪ በተያያዘው ቅጽ 002 መሰረት ሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡ 9. ለምዝገባ የሚያስፈልግ የቁጠባ መጠን 9.1. በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በነባር ለሚመዘገብ ተመዝጋቢ የመጀመሪያውን ዝቅተኛ የቁጠባ መጠን፣ 9.1.1. ለባለ ሦስት መኝታ ቤት ብር 685.00 /ስድስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር/ 9.1.2. ለባለ ሁለት መኝታ ቤት ብር 561.00 / አምስት መቶ ስልሳ አንድ ብር/ 9.1.3. ለባለ አንድ መኝታ ቤት ብር 274.00 /ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር/ 9.1.4. ለስቱዲዮ ብር 151.00 /አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም መቆጠብ አለበት፡፡ 9.2. በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በአዲስ ለሚመዘገብ ተመዝጋቢ የመጀመሪያውን ዝቅተኛ የቁጠባ መጠን፣ 9.2.1. ለባለ ሦስት መኝታ ቤት ብር 489.00 /አራት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር/ 9.2.2. ለባለ ሁለት መኝታ ቤት ብር 401.00 /አራት መቶ አንድ ብር/ 9.2.3. ለባለ አንድ መኝታ ቤት ብር 196.00 /አንድ መቶ ዘጠና ስድስት ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም መቆጠብ አለበት፡ ፡ 9.3. በ10/90 ወይም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤት ልማት ፕሮግራም ላይ ለሚመዘገብ ተመዝጋቢ የመጀመሪያውን የቁጠባ መጠን ብር 187.00 /አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም መቆጠብ አለበት፡ ፡ 9.4. ማንኛውም የ10/90 ወይም የአነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.3 በተቀመጠው የቁጠባ መጠን ልክ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በየወሩ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ሳያቋርጥ መቆጠብ ይኖርበታል፤ 9.5. ማንኛውም ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የቅድሚያ ቁጠባውን ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀፅ 9.1 በተቀመጠው የቁጠባ መጠን ልክ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በየወሩ ለተከታታይ አምስት ዓመታት መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ 9.6. ማንኛውም አዲስ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የቅድሚያ ቁጠባውን ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀፅ 9.2 በተቀመጠው የቁጠባ መጠን ልክ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በየወሩ ለተከታታይ ሰባት ዓመታት መቆጠብ የሚጠበቅበት ሲሆን፤ በማንኛውም ሰዓት ተመዝጋቢው የቆጠበውን ገንዘብ እንዲለቀቅለት ከፈለገ ባለው አሠራር መሠረት መልሶ ከምዝገባው ይሠረዛል፡፡ 9.7. በዚህ አንቀፅ አንቀ 9.1.፣ 9.2. እና 9.3. የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም ተመዝጋቢ የሚጠበቅበትን የቅድሚያ ክፍያ መጠን ሙሉውን ወይም ከተቀመጠው ዝቅተኛ የቁጠባ መጠን በላይ ቆጥቦ የመመዝገብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 9.8. የማንኛውም ተመዝጋቢ የቁጠባ መጠን ቤቱን በሚረከብበት ወቅት በወቅቱ ለዕጣ ለሚቀርቡ ቤቶች ወቅታዊ ማስተላለፊያ ዋጋ መሰረት የቅድሚያ ክፍያውን ያሟላ መሆን አለበት፡፡ 10. ስለ ቅፆች ይዘት፤ 10.1. ለቤት ተጠቃሚነት እንደፍላጐት መግለጫና ማረጋገጫ ሆነው የሚያገለግሉት ቅፆች ቅርፅ፣ ይዘትና አይነት ከዚህ መመሪያ ጋር አባሪ ሆነው የሚወጡ ሲሆን በዋናነትም፤ 10.1.1. የአመልካቹን ሙሉ ስም እስከ አያት እንዲሁም የአመልካቹን ፆታ፤ 10.1.2. የእናት ሙሉ ሥም፤ 10.1.3. ያገባ ከሆነ የትዳር ጓደኛውን ሙሉ ስም ከነአያት፤ 10.1.4. የመኖሪያና የሥራ አድራሻ እንዲሁም የሥራ ሁኔታ፤ 10.1.5. ማመልከቻ እስካቀረበበት ቀን ድረስ በተከታታይ በከተማው ውስጥ ቢያንስ ሁለት ዓመት የኖረ እና እየኖረ ያለ መሆኑን የሚገልፅ፤ 10.1.6. የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በሥራ ወይም በትምህርት ምክንያት በከተማዋ ውጭ የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ፤ 10.1.7. በቤት ልማት ፕሮግራሙ ከአንድ ንዑስ ፕሮግራም በላይ ያልተመዘገበ መሆኑንና በአይቲ ኦዲት ሲረጋገጥ ከሁሉም ፕሮግራም ተሰርዞ በህግ ሊጠየቅ እንደሚችል፤ 10.1.8. ለመግዛት የሚፈልገውን የቤት ዓይነት ወይም የክፍል ብዛት፤ 10.1.9. በራሱና በትዳር ጓደኛው እንዲሁም በስሩ ያሉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የገቢ መጠንና ምንጭ፤ 10.1.10. የአመልካቹ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፤ 10.1.11. በራሱ ወይም በትዳር ጓደኛው ስም የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሌለው ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን ያላስተላለፈና በቤት ልማት ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ተጠቃሚ ያልሆነ፤ 10.1.12. ዝቅተኛውን የቁጠባ መጠን መቆጠብ የጀመረ፤ በተከታታይ በየወሩ በመመሪያው መሰረት የሚቆጥብና ለተከታታይ 6 ወራት ቁጠባ ካቋረጠ ያስቀመጠው ገንዘብ ተመላሽ ተደርጎ ከምዝገባው እንደሚሰረዝ እንዲሁም በአዋጁ መሰረት የቅድሚያ ክፍያ ከፍሎ ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ የሆነ መሆኑን፤ 10.1.13. የገዛውን የመኖሪያ ቤት ከገዛበት ቀን ጀምሮ ለነባርም ሆነ አዲስ 20/80 ፕሮግራም ተጠቃሚ በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመታት፣ ለ10/90 ፕሮግራም ተጠቃሚ በመጀመሪያዎቹ 5 ዓመታት ውስጥ በሽያጭ፣ በወለድ አገድ ወይም በስጦታ ለሦስተኛ ወገን የሚያስተላልፍ መሆኑንና በጋራ ህንፃ ህግ ለመተዳደር ፈቃደኛ መሆኑ፤ 10.1.14. የሚኖረው በመንግስት ቤት ከሆነ ለሚያስተዳድረው አካል የገዛውን ቤት በተረከበ በሰላሳ ቀን ውስጥ ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኑ፤ 10.1.15. የሞላው ቅጽ ሐሰተኛ ሆኖ ቢገኝ አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቤቱን በመልቀቅ ለኤጀንሲው ለማስረከብና ኤጀንሲው በሚወስነው መሰረት የኪራይ ተመንና ቅጣት እንዲሁም መሰል አስተዳደራዊ ወጪዎች ከነወለዱ ታስቦ ቀሪው እንዲመለስለት የሚፈቅድ መሆኑን፤ 10.1.16. ቤት ፈላጊው በአዋጁና በመመሪያው መሰረት ለመተዳደር ፈቃደኛ መሆኑንና በማመልከቻ ቅጽ ላይ የሞላው ዝርዝር እውነተኛና ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦ መፈረሙን የሚያሳይና አስፈላጊ የሆኑ መጠይቆችን የሚይዝ ይሆናል፡፡ 11. የምዝገባ ሂደት 11.1. የምዝገባ ሂደቱ የሚጀመርበት ጊዜ በይፋ ለህዝብ ይገለፃል፤ 11.2. በምዝገባው ወቅት ለተመዝጋቢው ስለ አመዘጋገቡና ስለ ቤት ልማት ፕሮግራሞች ይዘት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች የሚሰጡ ሲሆን ነባር የ20/80 ተመዝጋቢን በተመለከተ ራሱን በሦስት አማራጮች ለይቶ እንዲያስቀምጥ በማድረግ፣ በዚህም፡- መሠረት 11.2.1. በነባር 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም መቀጠል የሚችል መሆኑን፣ 11.2.2. በቤቱ አይነት ላይ የፍላጐት ለውጥ ካለው በአዲስ 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ምዝገባ የመመዝገብ መብት እንዳለው፤ 11.2.3. አነስተኛ ገቢ ካለው ከሚኖርበት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ወይም ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ማስረጃ በማቅረብ በ10/90 የቤት ልማት ፕሮግራም ላይ መመዝገብ የሚችል መሆኑን ወይም 11.2.4. መካከለኛ ገቢ ካለው በ40/60 ቁጠባ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ላይ መመዝገብ እንደሚችል ይገለጽለታል፡፡ 11.3. ማንኛውም ተመዝጋቢ ቅፁን በሚሞላበት ወቅት ሊነበብ በሚችል የእጅ ፅሁፍ፤ ስርዝ ድልዝ በሌለው ሁኔታና በአማርኛ ፊደል በአግባቡ ቅፁን ሞልቶ በግንባር ሲቀርብ እንዲመዘገብ ይደረጋል፤ 11.4. ማንኛውም ተመዝጋቢ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ባወጣበት ወረዳ ወይም ምዝገባ ጣቢያ መስፈርቱን አሟልቶ ለምዝገባ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 11.5. መዝጋቢው አካል በዚህ መመሪያ ላይ የተዘጋጁት ቅፆች በትክክል መሞላታቸውና መፈረማቸውን አረጋግጦ ይቀበላል፣ 11.6. በመዝጋቢው አካል ተረጋግጠው የቀረቡትን ቅፆች በባህር መዝገብና በኮምፒውተር እንዲመዘገቡ ይደረጋል፣ 11.7. መዝጋቢው አካል የምዝገባው ሂደት በትክክል መካሄዱን በማረጋገጥ ለተመዝጋቢው ስለመመዝገቡ ማረጋገጫ ይሰጣል፣ 11.8. የምዝገባ ሂደቱን በተመለከተ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው መረጃው ይፋ ይደረጋል፡፡ 12. ለተመዝጋቢ ስለሚሰጥ ማረጋገጫ 12.1. ማንኛውም ሰው ለምዝገባ ብቁ እስከሆነና የምዝገባ መስፈርቱን አሟልቶ እስከተመዘገበ ድረስ ለተመዘገበበት ፕሮግራም የምዝገባ ማረጋገጫ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ 12.2. ለተመዝጋቢው በተሰጠው ማረጋገጫና በመረጃ ቋት ውስጥ ባለው መረጃ መካከል ልዩነት ቢፈጠር ተቀባይነት የሚኖረው በመረጃ ቋት ውስጥ የሚኖረው መረጃ ይሆናል፡፡ 12.3. ለተመዝጋቢው የሚሰጠው የምዝገባ ማረጋገጫ አይነትና ይዘት በኤጀንሲው የሚወሰን ይሆናል፡፡ 13. የምዝገባው መረጃ ለህዝብ ክፍት ስለመሆን፤ የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ መረጃ በተለያዩ የምዝገባ ጣቢያዎች ለ5 ተከታታይ ቀናት ክፍት ይሆናል፤ 14. የቅድሚያ ተጠቃሚነት አወሳሰን፤ 14.1. ቀደም ሲል በነበረው ምዝገባ ተመዝግበው በዕጣ ዕድላቸውን ሲጠባበቁ የነበሩ ተመዝጋቢዎች አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው በ20/80 በሚሰሩ ቤቶች ላይ ዳግም ምዝገባ ካከናወኑ ቅድሚያ የዕጣው ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ 14.2. ነባሩ 20/80 ተመዝጋቢዎች የዕጣው ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ቅድሚያ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የአዲስ 20/80 ተመዝጋቢዎች የዕጣው ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡ ክፍል አራት ምዝገባን ስለማጣራት እና በምዝገባ ላይ የሚደረጉ ለውጦችን ስለማስተካከል 15. ምዝገባን ስለማጣራት 15.1. መዝጋቢው አካል በራሱ ተነሳሽነት የከተማ አስተዳደሩን መረጃ በመጠቀም ወይም በተለየ መንገድ የተመዝጋቢዎችን መረጃ ትክክለኛነት የማረጋገጥና ስህተት ባለባቸው ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ መብት አለው፤ 15.2. በአንቅፅ 5 ላይ የተገለፀው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም የምዝገባ ሂደት መጠናቀቁ በይፋ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የምዝገባው መረጃ ህዝብ እንዲያውቀውና አስፈላጊውን ጥቆማ እንዲሰጥ በመረጃ መረብ፣ በጋዜጣ በሌሎችም የመገናኛ ዘዴዎች እና በየወረዳውና ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ እንዲለጠፍ ይደረጋል፤ 15.3. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 15/2 መሠረት በሚቀርቡ ጥቆማዎች መሰረትም መዝጋቢው አካል ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ስህተት ባለባቸው ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የመውሰድ ወይም እንዲወሰድ የማድረግ መብት አለው፤ 16. በምዝገባ ላይ የሚደረጉ ለውጦችን ስለማስተካከል 16.1. በነባርም ሆነ በአዲስ ተመዝጋቢነት የሚቀርብ የተመዝጋቢም ሆነ የትዳር ጓደኛ ፍች፣ የስም ለውጥ ጥያቄ የሚስተናገደው በመደበኛ ፍርድ ቤት አማካኝነት በሚሰጥ ውሳኔ ነው፣ 16.2. በነባር ምዝገባ በኮምፒዩተርና በነዋሪዎች መታወቂያ መካከል የስም፣ የአባት ስም፣ የእናት ስም እና የትዳር ጓደኛ ስም ፊደላት ግድፈት ወይም የዕድሜ ማስተካከል ጥያቄ ሲቀርብ ማስተካከያው በነዋሪነት መታወቂያ ላይ ያለው መረጃ ትክክለኛ ተደርጐ ይወስዳል፣ 16.3 በምዝገባ ወቅት የተፈጠረው የስም ፊደላት ግድፈት ወይም የዕድሜ መጠን በአገልግሎት ሰጪው ተቋም ባለሙያ ስህተት ከሆኑ እርማቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲስተካከሉ ይደረጋሉ፤ 16.4. ቀደም ሲል በተካሄደው ምዝገባ ተመዝግቦ ስሙ በመረጃ ቋት ውስጥ የሚገኝ ተመዝጋቢ የኮምፒዩተር ምዝገባ ሶፍት ዌሩ በሚይዘው ፎርማት መሰረት መረጃው ካልተሟላ አዲስ በሚሞላው ቅፅ ላይ ያለውን መረጃ እንደትክክለኛ በመቁጠር መረጃውን ማስተካከል ይችላል፡፡ 16.5. በነባሩ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዳግም ምዝገባ ላይ የሚመዘገብ ሰው ቀደም ሲል ተመዝግቦ ከነበረበት የመኖሪያ ቤት አይነት ወይም የክፍል ብዛት ላይ አሁን ያለው የቤተሰብ ቁጥር በማደጉ እና የገቢ ለውጥ ካለው በአዲስ 20/80 እና በሌሎች አማራጭ የቤት ልማት ፕሮግራሞች የመመዝገብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 17. ምዝገባ የማይወረስ መሆኑ 17.1. ማንኛውም ሰው በምዝገባ ሂደቱ ውጤት ተጠቃሚ መሆን የሚችለው በህይወት እስካለ ድረስ ብቻ ነው፤ 17.2. ምዝገባው በባል ወይም በሚስት ስም ሲሆንና ተመዝጋቢው በሞት ቢለይ ወይም ቢጠፋ በህይወት ያለው ባል ወይም ሚስት በምዝገባ ቅፁ አማካኝነት ወይም ከፍርድ ቤት በሚያቀርበው ማረጋገጫ መነሻነት ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው፡፡ 17.3. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ አንድ ቢኖርም ዕድሜያቸው 18 ዓመት ያልሞላቸው የሟች ልጆች ወራሽነታቸውን በመደበኛ ፍ/ቤት አረጋግጠው ሲመጡ የምዝገባው ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡ ፡ ሆኖም ወራሽ ስለመሆናቸው ከፍ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 17.4. በፍ/ቤት የወራሽነት መብት የተረጋገጠላቸው ግለሰቦች ተጠቃሚ የሚሆኑት በንዑስ አንቀጽ 8.1.4 የሚያሟሉ መሆን አለበት፡፡ 18. መረጃን ወቅታዊ ስለማድረግ 18.1. የተመዝጋቢዎች መረጃ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወቅታዊ ሊደረግ ይችላል፤ 18.2. ማንኛውም የአዲስና የነባር ተመዝጋቢ የመረጃ ለውጥ መስተናገድ የሚችለው መዝጋቢው አካል መረጃን ወቅታዊ ለማድረግ በሚያወጣው የህዝብ ማስታወቂያ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይሆናል፤ 18.3. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ አንድ ቢኖርም መዝጋቢው አካል በሚቀርብለት ጥቆማ ወይም በራሱ ተነሳሽነት የተመዝጋቢው መረጃ ስህተት ሆኖ ሲያገኘው የመሰረዝና የማስተካከል ሥልጣኑ የተጠበቀ ነው፡፡ ክፍል አምስት የምዝገባ ጊዜ ገደብ፣ የመረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅና ደህንነት ስርዓት 19. የምዝገባ ጊዜ ገደብ 19.1. ማንኛውም የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ የሚቆይበት ጊዜ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡ 19.2. የምዝገባው ጊዜ የሚቆይበትን ቀነ- ገደብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በሆኑ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት ቢያንስ ለ5 ቀናት ያህል በተከታታይ መገለፅ አለበት፤ 19.3. የምዝገባ ሂደቱ በተወሰነው ጊዜ ገደብ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት፤ በይፋ ከተገለፀው የምዝገባ ቀን ውጪ የሚመጣ ተመዝጋቢ በማንኛውም አይነት ሁኔታ ሊስተናገዱ አይቻልም፡፡ 19.4. የዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 19/3 ቢኖርም መዝጋቢው አካል የምዝገባውን ጊዜ ገደብ እንዳስፈላጊነቱ ሊያሳጥርም፣ ሊያራዝም ይችላል፡፡ 20. የምዝገባ መረጃ አያያዝ፣ አጠባበቅና ደህንነት፣ 20.1. ምዝገባው በሃርድና በሶፍት ቅጂ የሚከናወን ሲሆን ለሃርድ ኮፒው ምዝገባ የሚያገለግለው ባህር መዝገብ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያ ወይም ወረዳ አንድ ወጥና በቅፁ ላይ ያሉትን አስፈላጊ ዝርዝሮች በመያዝ በቁጥር ቅደም ተከተል ተመዘግቦ የሚያዝ ይሆናል፡፡ 20.2. የምዝገባ ጣቢያ ወይም ወረዳ መዝግቦ የያዘውን የተመዘጋቢዎችን የምዝገባ መረጃ በሃርድና በሶፍት ኮፒ ለክፍለ ከተማና ለማዕከል መዝጋቢ አካል ያስተላልፋል፤ መረጃውም በየደረጃው ተደራጅቶ ይያዛል፡፡ 20.3. የመረጃውን ደህንነት ለመጠበቅና እያንዳንዱ ምዝገባ መጠባበቂያ መረጃ ወይም ባክ አፕ እንዲኖረው ማድረግ፡፡ ሃርድ ኮፒውን በተመለከተ ባህር መዝገቡ በምዝገባ ጣቢያ ወይም በወረዳ የኮምፒውተር ማጠቃለያ በክፍለ ከተማ፤ በተመዝጋቢው የተሞላው ቅፅ በማዕከል እንዲቀመጥ ተደርጎ በየደረጃው ደህንነቱ ይጠበቃል፡፡ 20.4. የሶፍት ቅጂ መረጃውን በተመለከተ በዋናነት በማዕከል ባለው ሰርቨር አማካኝነት መረጃው የሚቀመጥ ሲሆን፤ እንደ መጠባበቂያ መረጃ ወይም ባክ አፕ አስፈላጊ በሆኑ የአስተዳደሩ አካላት ወይም ቦታዎች ላይ የተጠናቀቀው መረጃ እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ 20.5. የከተማ አስተዳደሩ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደአስፈላጊነቱ የአይቲ ኦዲት ያደርጋል፤ 20.6. በሃርድ ቅጅውና በሶፍት ቅጅው መረጃ መካከል ልዩነት ቢፈጠር የሃርድ ቅጅው መረጃ እንደ ትክክለኛ መረጃ የሚቆጠር ይሆናል፡፡ 20.7. ከመረጃዎች አያያዝ አንፃር ቀዳሚ መረጃ ሆኖ የሚወሰደው በማዕከል የሚደራጀው የሃርድ ቅጅ መረጃ ሲሆን በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ የሚኖሩት መረጃዎች ለማመሳከሪያነት ያገለግላሉ፡፡ 21. መዝጋቢ አካል 21.1. የቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ሂደት በኤጀንሲው ወይም ኤጀንሲው በሥሩ በሚወክለው መዝጋቢ አካል አማካኝነት በዋናነት በወረዳ ምዝገባ ጣቢያ አማካኝነት የሚከናወን ይሆናል፤ 21.2. በወረዳ ምዝገባ ጣቢያ የተመዘገቡ የተመዝጋቢዎች መረጃ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማና በማዕከል ተደራጅተው ይያዛሉ፤ 21.3. መዝጋቢው አካል ለመዘገባቸው መረጃዎች አያያዝ አስተዳደርና ደህንነት ኃላፊነት አለበት፤ 21.4. የምዝገባ ሂደቱ አፈፃፀምና የመረጃው ልውውጥ በዋናነት የሚወሰነው መዝጋቢውን አካል ለማደራጀት ተዘጋጅቶ በሚፀድቀው የአደረጃጀት ማዕቀፍና በሲስተም ደህንነት መመሪያው አማካኝነት ይሆናል፡፡ ክፍል ስድስት ኃላፊነት፤ ክልከላና ቅሬታ ሰሚ 22. የተከለከሉ ድርጊቶች 22.1. አንድ ተመዝጋቢ ካሉት የቤት ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ አይችልም፤ 22.2. ባልና ሚስት በቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በባል ወይም በሚስት ስም ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ ክልክል ነው፤ 22.3. ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ በራሱም ሆነ በሞግዚቱ አማካኝነት ሊመዘገብ አይችልም፣ እንዲሁም ከአንድ ጊዜ በላይ ከተመዘገበ ከሁሉም ፕሮግራሞች እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ 22.4. በራሱ ወይም በትዳር አጋሩ ስም የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ያለው ወይም ከዚህ ቀደም በቤት ልማት ፕሮግራም ግንባታ ተጠቃሚ የሆነ ሰው በቤት ፈላጊዎች ምዝገባ ላይ መመዝገብ አይችልም፤ 22.5. በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 7 ለምዝገባ ብቁ ስለመሆን እና በአንቀፅ 8 የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ቤት ፈላጊ ሊመዘገብ አይችልም፡፡ 22.6. በነባር 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምዝገባ ላይ ስሙ በመረጃ ቋት ውስጥ የሌለን ተመዝጋቢ በነባሩ የ20/80 ዳግም ምዝገባ ላይ መመዝገብ ክልክል ነው፡፡ 22.7. በምዝገባ ሂደቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ውጪ የሆነ ማንኛውም ሰው መመዝገብ አይችልም፡፡ 22.8. በእያንዳንዱ ፕሮግራም ተመዝጋቢ ከዚህ የምዝገባ መመሪያ ጋር አባሪ ሆነው ከቀረቡት የምዝገባ ቅጾች ውጪ በሌላ ቅፅ ወይም ፎርም መረጃን ሞልቶ ማቅረብ ክልክል ነው፤ 22.9. በነባር 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝግቦ ከዚህ በፊት ዕጣ ወጥቶለት በተለያዩ ምክንያቶች ቤቱን ቀርቦ ያልተረከበ ተመዝጋቢ በነባሩ 20/80 ዳግም ምዝገባ ሊመዘገብ አይችልም፡፡ ነገር ግን እንደ አዲስ ለመመዝገብ አይከለከልም፡፡ 23. ከምዝገባ ስለመሰረዝ 23.1. ማንኛውም ተመዝጋቢ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ያቀረበው ማስረጃ ወይም የሞላው ቅፅ የተሳሳተ ወይም ሐሰተኛ መሆኑ በመዝጋቢው አካል ወይም በህዝብ ጥቆማ ከተረጋገጠ የወንጀል ኃላፊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበው ምዝገባ ይሰረዛል፡፡ 23.2. ማንኛውም ተመዝጋቢ በየወሩ ሊቆጥብ የሚገባውን የገንዘብ መጠን ለተከታታይ ስድስት ወራት መቆጠቡን ካቋረጠ የቆጠበው ገንዘብ እንዲመለስ ተደርጎ ከምዝገባው እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ሆኖም ተመዝጋቢው በየወሩ ከሚጠበቅበት አነስተኛ የቁጠባ መጠን በላይ በአንድ ጊዜ ወይም ከስድስት ወር ባነሰ ጊዜ የቆጠበ ከሆነ ቁጠባውን እንደሸፈነ ይቆጠራል፡፡ ተመዝጋቢው በማንኛውም ሰዓት ከምዝገባው ተሠርዞ የቆጠበው ገንዘብ እንዲመለስለት ከጠየቀ ባለው የባንክ አሰራር መሠረት ተመልሶለት ከምዝገባ ይሰረዛል፡፡ 23.3. ማንኛውም ተመዝጋቢ በራሱ ፈቃድ ከምዝገባው ለመሰረዝ ጥያቄ ሲያቀርብ የቆጠበው ገንዘብ እንዲመለስ ተደርጎ ከምዝገባው እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ 23.4. በነባር 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ላይ በ1997 ዓ.ም. ተመዝግቦ የነበረና ይህ መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት ድጋሜ ቀርቦ ያልተመዘገበ ከሆነ በፍላጐቱ ከምዝገባ እንደተሰረዘ ይቆጠራል፡፡ 23.5. በ10/90 ፕሮግራም ከ187 ብር በላይ በወር የመቆጠብ አቅም እያለው በዚሁ ፕሮግራም የተመዘገበ መረጃው በተገኘበት ጊዜ ይሠረዛል፡፡ 24. የተመዝጋቢው ኃላፊነት 24.1 ተመዝጋቢው ምዝገባውን ለማከናወን በቅድሚያ በዚህ መመሪያ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቶ በግንባር መቅረብና ትክክለኛ መረጃ መስጠት
Posted on: Fri, 07 Jun 2013 09:25:40 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015