5 Young Ethiopian Filmmakers Selected For Emerging Talent - TopicsExpress



          

5 Young Ethiopian Filmmakers Selected For Emerging Talent Initiatives At Cannes & Monaco ... See at ... diretu.be/754828 |አምስት ወጣት ኢትዮጵያውያን ፊልም ሰሪዎች በኬንስ እና ሞናኮ ለሚካሄደው ተስፋ የተጣለባቸው የወጣት ፊልም ሰሪዎች ኢኒሼቲቭ ተመረጡ፡፡ ለሳምንት ያህል በሚቆየው በዚህ የ2014ቱ ፕሮግራም ላይ የተመረጡት ወጣቶቹ ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች ከዓለማቀፉ የፊልም ኢንደስትሪ አከፋፋዮች፣ ፕሮድዩሰሮች፣ ዳይሬክተሮችና ወኪሎች ጋር ቆይታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡ የተመረጡት አምስት ኢትዮጵያውያን ፊልም ሰሪዎች አዳነች አድማሱ፣ ሕይወት አድማሱ ጌታነህ፣ ሄርሞን ሐይላይ፣ ያምሮት ንጉሴ እና ዳንኤል ንጋቱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ዓለማቀፉ ‘International Emerging Film Talent Association’ ከኢትዮጵያ ፊልም ኢንሼቲቭ እና Better World Film Festival (BWFF) ጋር በመሆን ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት የተመረጡት ኢትዮጵያውያን ፊልም ሰሪዎች ዓለማቀፍ ግንኙነት በመፍጠር ሙያቸውን እንዲያጎለብቱ ተብሎ የተፈጠር ዕድል ነው ብለዋል፡፡ From Addis to Cannes በተባለው በዚሁ የልምድ መቅሰም መሰናዶ ላይ የኢትዮጵያውያኑ ፊልም ሰሪዎች ፊልሞች በሞንቴካርሎ ለሕዝብና ለፊልም ታዳሚያን እንደሚታይ ተገልጿል፡፡ ለዝርዝሩ.... diretu.be/754828
Posted on: Wed, 07 May 2014 18:30:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015