ABU DAWD OSMAN በባህርዳር ከተማ በሙስሊሞች - TopicsExpress



          

ABU DAWD OSMAN በባህርዳር ከተማ በሙስሊሞች መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኝ ቦታን ለአንድ ድርጅት መንግስት በመስጠቱ በሙስሊሞች እና በፖሊስ መካከል ግጭት መፈጠሩ ተሰማ:: በአማራ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በባህር ዳር ከተማ የህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር የሆነው የደባርቅ መካነ መቃብር አስፋልት አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግሰት ሞይንኮ ለተሰኘ ድርጅት አሳልፎ በመስጠቱ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት ቦታው በመንግስት የተሰጠው ድርጅት ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ ማስታወቁን ምንጮች አስታውቀዋል፡፤ ሆኖም ይህን ከደባርቅ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ በትላትናው ዕለት ህዝበ ሙስሊሙ ለማጠር እና አታክልት ለመትከል በመሳባሰብ ወደ ቦታው በመሄድ አጥር ማጠር ሲጀምሩ በፍጥነት የፌደራል ፖሊስ በመምጣት በጉልበት ለማስቆም በመሞከራቸው በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በፌደራሎቹ መካከል ችግር መፈጠሩን ምንጮች ከቦታው ዘግበዋል፡፡ በተፈጠረው አለመግባበባትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሙስሊሞች የታሰሩ ሲሆን ህዝበ ሙስሙ ባሰማው ተቃውሞ እና ትግልም ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ከአፍጥር ቡሃላ መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፤ ሼህ ሙሃመድ ታከለ እና አንድ ስሙ ያልተተቀሰ ሹፌር ከነመኪናው መታሰራቸው የተሰማ ሲሆን ማምሻውንም አለመፈታታቸው ታውቋል፡፤ በመንግሰት ድርጊት ቁጣው የገነፈለው የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብም በዛሬው ዕለት ሰላም በር መስጂድ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ የተጠራሩ ሲሆን የታሰሩት የማይፈቱ ከሆነ ወደ አላስፈላጊ ነገር ውስጥ ሙስሊሙን ሊከቱት ይችላሉ ሲል ምንጫችን ስጋቱን ገልፆል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን በአላህ ፈቃድ ይዘን እንመለሳለን፡፡ አላህ ይርዳቸው!!! ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!! አላሁ አክበር!!! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ for more information like this page https://facebook/abudawdosman https://facebook/abudawdosman
Posted on: Mon, 22 Jul 2013 16:41:49 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015