Asif Asim "እጅግ ዘግናኝ እና አስከፊ ድራማ - TopicsExpress



          

Asif Asim "እጅግ ዘግናኝ እና አስከፊ ድራማ ሰርቷል" ድምጻችን ይሰማ በደሴ ሁሉም የደሴ ሙስሊሞች እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች በጥብቅ ሊያወግዙት የሚገባ ጉዳይ! መንግሰት ሸህ ኑሩ የተባለውን ግለሰብ ራሱ ባዘጋጃቸው ደህንነቶች እንዲገደል ካደረገ በኋላ በደሴ ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ጠንካራ ሙስሊም የሆኑትን እየመረጠ በግድያው ላይ ይጠረጠራሉ በማለት በርካታ ሙስሊሞችን በማሰር ላይ ይገኛል፡፡ ይባስ ብሎ ዛሬ ሀሙስ ጧት እጅግ ዘግናኝ እና አስከፊ ድራማ ሰርቷል፡፡ ሷሊህ ሙሀመድ የተባለውን ወጣት ማክሰኞ 9፡00 ሰዓት ላይ ከያዙት በኋላ ዛሬ ጧት ቤታቸው በፌደራል ፖሊስና ከክልል በመጡ ፖሊሶች ከተከበበ በኋላ እጅግ አስቀያሚ ድራማ ሰርተዋል፡፡ ቤታቸው ውስጥ ሽጉጥና የጦር መሳሪያ በማስቀመጥ በቪዲዮ ከቀረጹ በኋላ በመጨረሻም ይህን ንጹህ ወንድማችንን ሽጉጥና መሳሪያ እንዲይዝ በማስገደድ በቪዲዮ ቀርጸውታል፡፡ በዚህ ድራማ ላይ ከከፍተኛ ባለስልጣነት ጀምሮ እስከ ቀበሌ ሹመኞች ድረስ በቦታው የተገኙ ሲሆን ከ 7 ፓትሮሎች በላይ የሚሆኑ ፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን በመክበብ አሳዛኙን ድራማ ሰርተዋል፡፡ ይህን አስከፊ ድራማም የሰሩት የሸህ ኑሩ ገዳይ ተገኘ በማለት ለማቅረብ ሲሆን የወጣቱንን እናትም በግድያው ላይ ተባባሪ ነሽ በማለት እሷንም ጨምረው ወደ እስርቤት ወስደዋታል፡፡ ይህ አሳዛኝና አስከፊ ድራማ ሰሞኑን በኢቲቪ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን ይህን ሴራ በማጋለጥ መረጃው ላልሰሙት በማሰማት ሁሉም ሙስሊሙ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡ ያረብ ከአንተ ውጭ ረዳት የለንምና አንተው ድረስልን! ያረብ ተበድለናል! የግፍ ግዜ በቃችሁ በለን!
Posted on: Thu, 11 Jul 2013 22:49:40 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015