Author Sues Renowned Film Maker Over Storyline Theft | Read More - TopicsExpress



          

Author Sues Renowned Film Maker Over Storyline Theft | Read More at .... goo.gl/T8XomX | ታዋቂው የፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ በ‹‹ ሶስት መአዘን ›› ፊልሙ የቅጂ መብት ክስ ቀረበበት የሴባስቶፖል ኢንተርቴይመንት ባለቤት እና በተለያዩ የፊልም ስራዎቹ የምናውቀው ቴዎድሮስ ተሾመ ‹‹በፍቅር ሲበቀል ›› መጽሃፍ ደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ ነው ክሱ የቀረበበት፡፡ ከሳሹ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስሞታውን እንዳሰማው ቴዎድሮስ ተሾመ ሶስት ማእዘን በተሰኘው ፊልሙ የመጸሃፉን አጠቃላይ ሀሳብ ወስዷል፡፡ የመጸሃፉ ደራሲ ለደረሰበት ኢኮኖሚያዊ እና የሞራል ጉዳት 10 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካሳም ጠይቋል፡፡ ፍቅር ሲበቀል ከአምስት ዓመታት በፊት ለህትመት የበቃ የድርሰት ስራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የክስ ሂደቱ ከፍርድ ቤቶች የክረምት እረፍት በኋላ ይቀጥላልም ተብሏል -እንደ አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ዘገባ
Posted on: Fri, 29 Aug 2014 11:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015