Egypt softens stance on Ethiopian dam ... See at ... - TopicsExpress



          

Egypt softens stance on Ethiopian dam ... See at ... diretu.be/868729 | የግብጽ ሚዲያዎች ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ እየተለሳለሰች መምጣቷን እየዘገቡ ነው፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ላይ በሚያቀርባቸው ዘገባዎቹ የሚታወቀው አል ሞኒተር የግብጽ መንግሥት ባለስልጣናት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ እየተለሳለሱ መምጣታቸውን ዘግቧል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አል ሞኒተር የግብጽ ጠቅላይ ሚንስትር ኢብራሂም ሜህሌብ ኢትዮጵያ ከግድቡ ኤሌክትሪክ ታመንጭ ግብጽም የውሃ መብቷ ይጠበቅ ማለታቸውንና የውጭ ጉዳይ ሚንሰትሩ ናቢል ፋህሚም በበኩላቸው ለአል ሞኒተር ሀገራቸው በግድቡ ግንባታ ሰበብ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት እንደማትገባ መግለጻቸውን አንስቷል፡፡ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የግብጽ መንግሥት ባለስልጣን በበኩላቸው ካለፉት ጥቂት ሳምንታት አንስቶ እስከ መጪው የግብጽ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድረስ የሚቆይ ረዥም የምክክርና አቋምን የመከለሻ ስብሰባዎች በግብጽ መንግስት ባለስልጣናት ዘንድ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በስብሰባዎቹ ላይ በርካታ የቴክኒክ ባለሙያዎችና የግድብና ውሃ ጉዳይ ኤክስፐርቶች ቀርበው ሀሳብ መስጠታቸውን የሚገልጹት ባለሥልጣኑ አሁን በግብጽ መንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ያለው እሳቤ ገንቢ ውይይት ከኢትዮጵያ ጋር ማድረግ የሚያስችል ፖሊሲ ወደ መቅረጹ እንዳዘነበለ ተናግረዋል፡፡ ግብጽ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና በናይል ተፋሰስ ሀገራት በ52 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የጥናት ፣ የምርምር እና የልማት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መዘጋጀቷን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ....... diretu.be/868729
Posted on: Sat, 24 May 2014 20:00:01 +0000

© 2015