Ethiopia, China enjoy excellent relations: Ethiopian PM ... See at - TopicsExpress



          

Ethiopia, China enjoy excellent relations: Ethiopian PM ... See at ... diretu.be/664953 | ኢትዮጵያ እና ቻይና በምርጥ ወዳጅነታቸው ደስተኞች ናቸው - ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት ከሆነ ቻይና እና ኢትዮጵያ የፈጠሩት ጠንካራ ወዳጅነት አስደሳች ፣ ውጤታማ እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቻይና ጋዜጠኞች በጽ/ቤታቸው በሰጡት ቃለመጠይቅ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት የሃገራቱን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው እና የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ መጀመራቸው የሀገራቱን ጠንካራ ወዳጅነት የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የዓለም አቀፍ የአሰራር ለውጥ ፣ ሽርተኝነት ፣ የሁለቱ ሃገራት የጋራ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቻይናዊያኑ ጋዜጠኞች ነግረዋል፡፡ ቻይና በኢትዮጵያ ፈጣን እድገት ላይ የራሷ አሻራ ማሳረፏንም ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ‹‹ ቻይና የምንተማመንባት አጋራችን ናት›› ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በነገው እለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለተጨማሪ ... diretu.be/664953
Posted on: Sat, 03 May 2014 17:25:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015