Ethiopia Elected Deputy Member of ILO Governing Body | See at .... - TopicsExpress



          

Ethiopia Elected Deputy Member of ILO Governing Body | See at .... diretu.be/969785 | ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት የአመራር አካል ተባባሪ አባል ሆና ተመረጠች የኢትዮጵያ መንግስት እንዳለው ከሆነ በ103ተኛው የዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ 2014- 2017 ለሶስት ዓመታት የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር አካል ተባባሪ አባል ሆና ተመርጣለች፡፡ ኢትዮጵያ ለቦታው በመመረጧ ከሌሎች የተመረጡ የአፍሪካ ሀገራት ጋር በመሆን አፍሪካ በስደት ፣ በስራ አጥነት ፣በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የማስተባበር ሚና መወጣት ይጠበቅባታልም ተብሏል፡፡ የሰረተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አብዱል ፈታህ ሀሰን በጉባኤው የኢትዮጵያን የልኡካን ቡድን ወክለው የነበሩ ሲሆን የዓለም የሰራተኞች ድርጅት በወጭ ሀገራት ለስራ ወጥተው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቱ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው አጠናክሮ እንዲቀጥልበትም ጠይቀዋል፡፡ በአመራር አባልነቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሌሎች 8 የአፍሪካ ሀገራትም መመረጣቸውም ተጠቁሟል፡፡ ለተጨማሪ.....diretu.be/969785
Posted on: Wed, 11 Jun 2014 14:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015