Ethiopia: If the shoe fits, build zones .... See at - TopicsExpress



          

Ethiopia: If the shoe fits, build zones .... See at ....diretu.be/258475 | የውጭ ሐገር የጫማና የጨርቃጨርቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ነው፡፡ የውጭ የጨርቃጨርቅና የጫማ ፋብሪካዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ እየከተሙ ነው የሚለን ዘገባ፣ ለኩባንያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ዋንኛው ምክንያት በኢትዮጵያ ያለው አንጻራዊ ርካሽ የሰው ጉልበት መሆኑን ይገልጻል፡፡ የታይዋኑ የጫማ አምራች ጆርጅ የጫማ ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 15 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለው ቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ምርት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ የሆነው ሁዋጂያን በአዲስ አበባ ዙሪያ እ.አ.አ በ2023 አንድ መቶ ሺ ሰዎችን መቅጠር የሚችል ግዙፍ የቀላል ማምረቻ ማዕከል ለመክፈት እንዳቀደው ሁሉ፣ ይህ የታይዋኑ ኩባንያም በጥቂት ዓመታት ውስጥ 10 000 ሰዎችን መቅጠር የሚችል የኢንዱስትሪ ፓርክ በሞጆ ለመክፈት ተዘጋጅቷል፡፡ መንግስት በአዲስ አበባ የኢንዱስትሪ ዞን እየገነባ የሚገኝባቸው ቦታዎች ቦሌ ለሚና ቂሊንጦ ሲሆኑ ከነዚህም በተጨማሪ ግን በድሬዳዋ፣ ኮምቦልቻና አዋሳ ከተሞችም ለመገንባት አቅዷል፡፡ የሁዋጂያን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበረችው ሔለን ሄይ “በቻይና በአሁኑ ወቅት ለአንድ ቻይናዊ የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ የሚከፈለው 9 758 ብር ሲሆን በኢትዮጵያ ግን 975 ብር ብቻ ነው ይህ ኩባንያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሳቡ አድርጓል” ትላለች፡፡
Posted on: Tue, 20 May 2014 14:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015