Ethiopia Passes a Law that Permits Artificial Ways for Having a - TopicsExpress



          

Ethiopia Passes a Law that Permits Artificial Ways for Having a Child ... See at... diretu.be/452386 | ለመካንነት የተዳረጉ ሴቶች በሰው ሰራሽ መንገድ መውለድ እንዲችሉ የሚፈቅድ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ። አገሪቱ በሰው ሰራሽ መንገድ መሃን የሆኑ ሴቶች ልጅ እንዲያገኙና ስራው በህግ የተደገፈ እንዲሆን የተለያዩ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰሰ ደንብ ስታዘጋጅ መቆየቷን የዘገበው ኤፍቢሲ ሲሆን ደንቡም ከሳምንታት በፊት በሚኒስተሮች ምክር ቤት እንደጸደቀ ጠቁሟል። ይህን ደንበ ማጽደቅ ያስፈለገው ልጅ ማግኘት ተፈጥሮአዊ መብት በመሆኑና ልጅ የሌላቸው ዜጎች የሚደርስባቸው የማህበራዊ ችግሮች ከፍተኛ በመሆኑ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ረዳት ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ደስታን ጠቅሶ ዘገባው አመልክቷል። ይህን አገልግሎት አቅሙ ያለው የመንግስትም ይሁን የግል የጤና ተቋም መስጠት እንደሚችል ደንቡ የሚፈቅድ ሲሆን ከዚሀ በፊት ሀገሪቱ በግልጽ የከለከለችውን የማህጸን ኪራይ ይህ ደንብም በግልጽ ይከለክላል ብሏል ሚኒስቴሩ። እናም ለህክምና አገልግሎት ከተሰጠው ፈቃድ ባሻገር ይህ አገልግሎት አለም አቀፍ ደረጃን የሚጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም የጤና ተቋም ከተሰጠው ፈቃድ ባሻገር ልዩ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል ተብሏል። ለዚህም በመሳሪያም ይሁን በባለሙያ ዝግጁ መሆን የሚገባው ሲሆን፥ ባለሙያውም ይህን አገልገሎት ለመስጠት ልዩ ፈቃድ ያስፈልገዋል። በአሁኑ ጊዜ ደንቡን ማስፈጸም የሚያስችል መመሪያ እየወጣ መሆኑን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለፀው። የቤተል ቲቺንግ ጄኔራል ሆስፒታል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የማህፀን ደዌና የፅንሰ ስፔሻሊስት ዶክተር ይገረሙ አስፋው በማንኛውም መንገድ መውለድ የማይችሉ ኢትዮጵያውያን በህንድና ታይላንድ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት አገልግሎቱን ሲያገኙ መቆየታቸውን አንስተው ኢትዮጵያውያኑ ልጅ ለማግኘትም ከ200 ሺህ ብር እስከ 300 ሺህ ብር ያወጡ ነበር ጠቁመዋል። በሀገራችን በብቸኝነት አገልግሎቱን ጀምሮ ስራው በህግ የተደገፈ ባለመሆኑ አገልግሎቱን ያቋረጠው ቤተል ሆስፒታል ለሰባት አመታት ከጣልያንና ከእስራኤል ሀኪሞች ጋር በመተባበር አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል ። በዚህ መንገድም ለ700 ሰዎች አገልግሎቱን መስጠት ተችሏል ነው ያሉት። አገልግሎቱ ከፍተኛ መድሀኒቶችን ከውጭ በማምጣትና ከውጭ የህክምና ባለሙያዎች ጋር የሚከናወን በመሆኑ ሆስፒታሉ ከ60 እስከ 90 ሺ ብር ነው አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል። አሁን ደንቡ መውጣቱም ኢትዮጵያውያን አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ውጭ የሚያደርጉትን ጉዞ የሚያስቀር ይሆናል ተብሏል።
Posted on: Sat, 26 Apr 2014 09:04:17 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015