Ethiopia is ranked as Sub-Saharan Africas strongest military - - TopicsExpress



          

Ethiopia is ranked as Sub-Saharan Africas strongest military - ኢትዮጵያ በጦር ኃይሏ በጥቁር አፍሪካ ‘አንደኛ’ ነች የዓለምን የጦር አቋም የሃገሮች ደረጃ የሚያወጣው “ግሎባል ፋየርፓወር” ዌብሣይት የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ከሰሃራ በስተደቡብ ባለው አፍሪካ እጅግ ብርቱው መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር አቋም ከደቡብ አፍሪካ፤ ከናይጀሪያና ከኬንያም ኃይሎች እንደሚያይል ዌብ ሣይቱ አመልክቷል፡፡ “ግሎባል ፋየርፓወር” የስያሜው ቃል በቃል ትርጉም “የዓለም የተኩስ አቅም” ወይም “የዓለም የጦር አቋም” ሊሆን ይችላል - ኢትዮጵያ በጦር ኃይሏ ብርታት በዓለም አርባኛ መሆኗን አሣይቷል፡፡ ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያን ተከትላ በዓለም 41ኛ ነች፡፡ ናይጀሪያ 47ኛ፣ የኢትዮጵያዋ ጎረቤት ኬንያ ደግሞ 63ኛ ነች - በጦር ኃይሎቿ ጥንካሬ፡፡ በጥናቱ ውስጥ ከታቀፉት 106 የዓለም ሃገሮች መካከል ኤርትራ የለችም፡፡
Posted on: Thu, 24 Apr 2014 12:09:26 +0000

© 2015