Ethiopia: potato cultivation great potential ... Read More - TopicsExpress



          

Ethiopia: potato cultivation great potential ... Read More at...goo.gl/y7PeyD | በድንች ዙሪያ የሚሰራው ዓለማቀፉ ተቋም International Potato Center ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ለድንች ምርት እጅጉን የተመቸች ሀገር መሆኗን ይገልጻል፡፡ በዚሁ ላይ ተመርኩዞ በቅርቡ በጀርመኑ ድረገጽ inar.de ላይ የወጣው ሪፖርት፣ ድንች ኢትዮጵያ ራሷን ለመመገብ የምታደርገውን ትግል በቀላሉ ሊያሳካ የሚችል ነው ይላል፡፡ ቢሆንም ግን በኢትዮጵያ ካሉ የድንች አምራቾች የተሻሻለ የድንች ዘር ማግኘት የቻሉት ከ3 % እንደማይበልጡ ነው የሚነገረው፡፡ ይህንንም ለመለወጥ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከአየርላንድ ሳይንቲስቶች ጋር በጥምረት እየሰራ ነው ተብሏል፡፡ የትብብሩ ዓላማ ለኢትዮጵያ ተስማሚ የሆነ፣ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ እና በሽታ ተከላካይ የድንች ዘር ለማግኘት ነው፡፡ ከእህል ምርት ይልቅ ቶሎ የሚደርሰው፣ ለእድገቱ ብዙም ውሃ የማይፈጀው እንዲሁም ከቫይታሚን ሲ እና ፕሮቲን የበለጸገው ድንች ወደፊት በኢትዮጵያውያን አመጋገብ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚኖረው እንደሚሆን ተገምቷል፡፡
Posted on: Sat, 06 Dec 2014 11:55:30 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015