Ethiopias mobile assembling plant business thrives ... See at .... - TopicsExpress



          

Ethiopias mobile assembling plant business thrives ... See at .... diretu.be/439425 | የኢትዮጵያ የሞባይል መገጣጠሚያ ኢንደስትሪዎች ቢዝነስ ደርቶላቸዋል፡፡ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ የሞባይል መገጣጠሚያዎች ተመሳስለው በሚሰሩና ከቻይና በሚገቡ ርካሽ የሞባይል ስልኮች ሳቢያ ከስረው ፋብሪካዎቻቸውን ሲዘጉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የሞባይል መገጣጠሚያዎች በአንጻሩ ቢዝነስ ደርቶላቸዋል ሲል ፒሲ አድቫይዘር ጽፏል፡፡ በኢትዮጵያ የሞባይል መገጣጠሚያ ያለው ቴክኖ ሞባይል ምርቶቹን ከኢትዮጵያ ውጪ መላክ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ቴክኖ ከኢትዮጵያ ውጪም የተቀረውንም አፍሪካ ገበያም በመሻት በኬንያ እና ናይጄሪያም መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ለማቋቋም አቅዷል፡፡ ጂ-ታይድ የተሰኘው ሌላኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሞባይል ስልክ መገጣጠሚያም የመስፋፋት ዕቅዱን እያጠናቀቀ ምርቶቹን ወደ ውጭ ለመላክ መዘጋጀቱን ጠቅሷል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ላሉ የሞባይል ሰሪዎች እንቅፋት የሆነውና ብዙዎቹንም አክስሮ ከገበያ ያስወጣቸው ከቻይና የሚገቡ ተመሳስለው የሚሰሩ ርካሽ ሞባይሎች መሆናቸውን የሚጠቅሱት የጉዳዩ ተከታታዮች የኢትዮጵያ መንግስት በአንጻሩ እነዚህን የሞባይል ስልኮች ወደ ሀገሩ እንዳይገቡ ማገዱ ሀገር ውስጥ ላሉት የሞባይል መገጣጠሚያዎች ጥሩ ሁኔታ ፈጥሯል ይላሉ፡፡ በዛምቢያ የኮምፕዩተር ሶሳይቲ የቴሌኮም ተንታኝ የሆነው አሞስ ካሉንጋ፣ “የኢትዮጵያ የታክስ ስርዓት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንጻር የተሻለ ነው፣ ተመሳስለው የተሰሩ ሞባይሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከመከላከሉም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት የሞባይል አምራቾች የታክስ ነጻ የሆነ ጊዜ መሰጠቱ አምራቾቹ አትራፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል” ይላል፡፡
Posted on: Sun, 01 Jun 2014 09:05:00 +0000

Trending Topics



ned Vincente Padilla 8x10 Photo Philadelphia
Yesterday my plane was delayed 5 hours, nearly ran out of petrol
SHOP NOW! ACDelco 45G0255 Stabilizer Bar Link Price

Recently Viewed Topics




© 2015