Federal TVET Institute Officials Charged of Corruption .... See at - TopicsExpress



          

Federal TVET Institute Officials Charged of Corruption .... See at ... diretu.be/272579 | የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተከሰሱ በትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተርን ጨምሮ አስር የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል መከሰሳቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል። ተከሳሾቹ ሻምበል ከበደ አስረስ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የአስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር፣ ወይዘሮ የሺዓለም አምባው አለኸኝ የኢንስቲትዩቱ ገንዘብ ያዥ፣ የኔነሽ ሃይለማሪያም ገንዘብ ያዥ፣ አረጋኸኝ ኩማ ሃይሌ የዕቃ ግዥ ሰራተኛ፣ ጋሻው ዘውዴ ወርቁ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ሀላፊ፣ ብርሃኔ መለሰ ሰጤ የተሽከርካሪ ስምሪት ሀላፊ፣ ሀብተወልድ ሃይሉ የፋይናንስ አገልግሎት ሃላፊ፣ አዱኛ ሸኔ አካዳሚክ ምክትል ዳይሬክተር፣ ሀይሌ በላይነህ ወልደፃዲቅ የሰው ሀይል ልማት ዳይሬክተር፣ በየነ ማሞ ገበየሁ የዕቃ ግዥ ሰራተኛ ናቸው። የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ እንደሚያመለክተው ኢንስቲትዩቱ በ2005 ዓ.ም በውስጥ ጨረታ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ፣ የመረጃ ግኑኝነት ቴክኖሎጂ ዕቃዎች እና ለማምረቻ ክፍል የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በጥቅሉ 2 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ለመግዛት ጨረታ ያወጣል። በግዥ መመሪያው ከ100 ሺህ ብር በላይ ዕቃ ሲገዛ በግልፅ ጨረታ መከናወን ሲገባው ይሄ አልተካሄደም፤ እንዲሁም በግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ባይቀርብ እንኳ በግዥ አፅዳቂ ኮሚቴ ፀድቆ ጨረታው መከናወን ነበረበት ይላል። ነገር ግን ምክትል ዳይሬክተሩ አንደኛ ተከሳሽ ሻምበል ከበደ አስረስ ለግዥ አፅዳቂ ኮሚቴ ሳያቀርብ ግዥውን በራሱ ፈቃድ አፅድቆ ጨረታው ተፈፃሚ እንዲሆን አድርጓል። በፖስታ ያልታሸገ ጨረታ እንዲሁም ዝቅተኛ ዋጋ እያለ ከፍተኛ ዋጋ ተቀብለዋል፤ ይሄም ብቻ አይደለም ሀሰተኛ ቃለ ጉባኤም አዘጋጅተዋል ሲል ያስረዳል። አንደኛ ተከሳሽ የአስተዳደር ምክትል ዳይሬክተሩ ሻምበል ከበደ ሁለተኛው ተከሳሽ የሺዓለም አምባውን ለልዩ ልዩ ግዥ በሚል 10 ሺህ ብር ወጭ ብሎ በማዘዝ ፤ ሁለተኛው ተከሳሽ ለግል ጥቅሟ አውላዋለች ይላል ክሱ። በሌላ በኩል አሮጌ የመኪና ዕቃ እና ጥራት የጎደላቸው የሎከር እቃዎችን ገዝተው ገቢ አድርገዋልና ሌሎችም ይገኛሉ። ተከሳሾቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ የተነበበላቸው ሲሆን፥ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ከሳሽ አቃቤ ህግ በስምንተኛ እና አስረኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ አካዳሚክ ምክትል ዳይሬክተሩ አዱኛ ሽኔ የዕቃ ግዢው ከበየነ ማሞ በስተቀር ሁሉም የተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ዋስትና የሚከለክል ነው ብሎ ተከራክሯል። ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱም ከሁለቱ በስተቀር የሌሎቹን ዋስትና ከልክሎ የክስ መቃወሚያቸውን ለመስማት ለግንቦት 15 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ መያዙም ተጠቁሟል።
Posted on: Fri, 09 May 2014 07:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015