Israeli Foreign Minister To Visit Ethiopia In Five-nation African - TopicsExpress



          

Israeli Foreign Minister To Visit Ethiopia In Five-nation African Tour | See at ... diretu.be/399464 | የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሀገራትን ሊጎበኙ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቪጎር ሊበርማን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ5 የአፍሪካ ሀገራት 10 ቀናት የሚቆይ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ጉብኝትን ‹‹ስትራቴጂካዊ ጉብኝት›› ብሎታል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚጎበኟቸው የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ፣ ሩዋንዳ ፣ አይቮሪ ኮስት ፣ ጋና እና ኬንያ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የጉብኝቱ ዓላማም እስራኤል ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ወቅት በአምስቱም የአፍሪካ ሀገራት የጋራ የፋይናንስ እና የቢዝነስ ጉባኤዎች ይደረጋሉ የተባለ ሲሆን የእስራኤል የወጪ ንግድ ኢንስቲቲዩት ተወካዮችን ጨምሮ ከ50 የእስራኤል ካምፓኒዎች የተውጣጡ ባለሀብቶች እና ሌሎች አካላትን የያዘ የልኡካን ቡድን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚመጣም ተጠቁሟል፡፡ አቪጎር ሊበርማን በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል፡፡ እስራኤል እና ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ፣ በባህል እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጠነከረ ወዳጅነት እንዳላች የሚታወቅ ሲሆን እስራኤል የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ግንባታ ትደግፋለች በሚል በግብጽ ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲሰነዘርባት መቆየቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡
Posted on: Thu, 12 Jun 2014 18:00:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015