The Egyptian journalist is expelled for engaging other than his - TopicsExpress



          

The Egyptian journalist is expelled for engaging other than his journalistic tasks: Shimeles Kemal ... See ...at ... diretu.be/853764 | ግብፃዊ ጋዜጠኛ ሃመዲ አል-አናኒ በኢትዮጵያ ውስጥ ከጋዜጠኝት ሙያ ተግባሩ ውጪ ተሰማርቶ በመገኘቱ ሰሞኑን መባረሩን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ።የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመለስ ከማል በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ “ጋዜጠኛ ሃመዲ አል-አናኒ ፈቃድ ካገኘበት የጋዜጠኝነት ሙያ ስራ ጋር ፈጽሞ ተፃራሪ በሆነ ሕገ ወጥ ድርጊት ውስጥ በመገኘቱ በፍጥነት ከሀገር እንዲባረር ተደርጓል” ብለዋል። ግብፃዊ ጋዜጠኛው ከሙያው ውጪ የተሰማራባቸውን ሥራዎች ምን እንደነበሩ እንዲገልፁልን ጠይቀናቸው ሚኒስትሩ በዚህ ነጥብ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ባድር አበድላቲ በበኩላቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ይፋዊ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ብለዋል። ግብፃዊ ጋዜጠኛ ሃመዲ አል-አናኒ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ፈቃድ አግኝቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ስድስት ወራት ስራውን ሲያከናውን ነበር። ግብፃዊ ጋዜጠኛ ሃመዲ አል-አናኒ ለግብፅ መንግስታዊ የዜና ኤጀንሲ እና ለሚድል ኢስት ኒውስ ኤጀንሲ ተቀጥሮ ይስራ ነበር።
Posted on: Thu, 29 May 2014 09:48:17 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015