The US Archeology Professor at Axum University asked to handover - TopicsExpress



          

The US Archeology Professor at Axum University asked to handover Artifacts ....... See ... at .... diretu.be/574992 | አሜሪካዊው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር ያገኟቸውን ቅርሶች እንዲያስረክቡ ተጠየቁ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት የውጭ አገር ዜጋ በምርምር ወቅት ያገኟቸውን የዘመነ አክሱም የዕደ ጥበብ ውጤቶች የትግራይ ክልል እንዲያስረከቡ ማሳሰቡ ተሰምቷ፡፡ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአርኪዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና የድኅረ ምረቃ ክፍል አስተባባሪው አሜሪካዊው ፕሮፌሰር ሳሙኤል ዎከር፣ በግላቸው በሚያከናውኑት ምርምር በርካታ የዘመነ አክሱም የሰውና የእንስሳት፣ የሳባና የግእዝ ጽሑፍ የሰፈረባቸውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የዕደ ጥበብ የሸክላ ውጤቶች ማግኘታቸውና መሰብሰባቸው በእጃቸውም እንደሚገኝ ምንጮችን ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ በኢትዮጵያ የቅርስ ሕግ መሠረት ማንኛውም ሰው በማናቸውም አጋጣሚ ያገኛቸውን ቅርሶች ለባለሥልጣኑ [ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን] ሪፖርት ማድረግና ማስረከብ እና ያወቀም የመጠቆም የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት በዘገባው ተመልክቷል፡፡ ይሁን እንጂ አሜሪካዊው መምህር ያገኟቸውን የዕደ ጥበባት ቅርሶች በሕጉ እንደተቀመጠው ሳያስረክቡ እስካሁን ይዘው ይገኛሉ ብሏል ዘገባው፡፡ መረጃው የደረሰው የኢትዮጵያ አርኪዮሎጂና ፓሊዮቶሎጂ ማኅበር፣ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጉዳዩን አስመልክቶ በጻፈው ደብዳቤ በአክሱም አካባቢ የተለያዩ ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ ቅርሶች በግለሰብ አርኪዮሎጂስት ሳሙኤል ዎከር እጅ መከማቸታቸውን ማሳወቁን ሪፖርተር አገኘኋቸው ያላቸው ሰነዶች እንደሚያመላክቱም ተጠቅሷል፡፡ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስ ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም አማረ፣ ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑንና ክልሉ ቅርሱን እንዲረከብ ካለበለዚያ የፌዴራል መሥሪያ ቤቱ እንዲረከብ የሚያሳስብ ደብዳቤ መጻፉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ የአክሱም ክላስተር ኃላፊዎች ቅርሶቹን በተመለከተ ተጠይቀው፣ መምህሩ የግእዝና የሳባ ጽሑፎች የተጻፈባቸውን ጨምሮ የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆናቸውንና ክላስተሩም ከዩኒቨርሲቲው የአርኪዮሎጂ ዲፓርትመንት ጋር በመነጋገር ለመረካከብ እየሠሩ መሆኑን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ አሜሪካዊው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር ..... diretu.be/574992
Posted on: Sun, 08 Jun 2014 10:00:00 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015