ለጥያቄያችን መልስ ***************** 1፡- - TopicsExpress



          

ለጥያቄያችን መልስ ***************** 1፡- ምስጢራተ ቤተ ክርስትያን የሚባሉት ስንት ናቸው ? ዝርዝራቸውን ጻፉ? ... ------>> ሰባት ናቸው . ምሥጢረ ጥምቀት . ምሥጢረ ሜሮን . ምሥጢረ ቁርባን . ምሥጢረ ንስሓ . ምሥጢረ ክህነት . ምሥጢረ ተክሊል . ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው ። 2፡-አዕማደ ሚስጥር የሚባሉት ስንት ናቸው ? ዝርዝራቸውን ጻፉ? ----->> አምስት ናቸው - ምሥጢረ ሥላሴ :-የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት የምንማርበት -ምሥጢረ ሥጋዌ:- የአምላክን ሰው መሆን… የምንማርበት - ምሥጢረ ጥምቀት :-ስለ ዳግም መወለድ.. የምንማርበት - ምሥጢረ ቁርባን ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም… የምንማርበት - ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን:- ስለ ዳግም ምጽዓት የምንማርበት 3፡- ምስጢር የተባሉት በምን ምክንያት ነው? -->> ምስጢር መባሉ ስለ ፫ ነገር ነው * ለአመነ እንጂ ላላመነ አይሰጥም። * በዓይን የሚታየው በእጅ የሚዳሰሰው ግዙፍ ነገር ሲለወጥ አይታይም። * ምዕመናን በዚህ በሚታየው የማይታየውን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ሲቀበሉ የሚፈጸመው በግብረ አምላካዊ ስለሆነ ሚስጥር ይባላል። ቤተክርስትያን የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ በእምነት ለሚቀርባት ሁሉ ታድላለች። ይህንንም ፀጋ የምታድልበት መሣሪያዎች ሚስጢራት ተብለው ይጠራሉ። እንዚህም ሚስጢራት ተብለው የሚጠሩበት ምክንያት አፈጻጸማቸው በዓይን የሚታይ ቢሆንም የሚያስገኝው ጥቅም ግን በስጋዊ ጥበብ ሊደረስበት የማይቻል የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለሆነ ነው። ይህም ከአእምሮ በላይ ነው።እንዲህም ሰለሆነ ቤ/ክ ምስጢር ብላ በመሰየም ለልጆቿ ታስተምራለች። 4:- አዕማድ የተባሉበት ምክንያትን ግለጹ? --->> አምድ ማለት ምሰሶ ማለት ሲሆን አእማድ ማለት ምሰሶዎች ማለት ነው ። ቤት በአምድ (በኮለም) እንደሚፀና ፤ ሃይማኖትም በነዚህ ምሥጢራት ተጠቃሎ ይገለጻል ፤ምዕመናንም እነዚህን ምሥጢራት በመማር ፀንተው ይኖራሉ ። የበለጠ ለማንበብ አነዚህን ይጫኑ :- tewahedo.nl/biblical_studymestir.html tewahedo.nl/biblical_study7mestir.htmlSee More— with Genet Abera and 7 others.
Posted on: Mon, 04 Nov 2013 07:37:20 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015