‹‹ሞደፊክ›. ድንግልና፤ አዲሱ - TopicsExpress



          

‹‹ሞደፊክ›. ድንግልና፤ አዲሱ የሳይንስ ስጦታ -------------------------------------- ‹‹እስቲ አምጡት የደሙን ሸማ እንዳንታማ፤ እስቲ አምጡት የደሙን ሻሽ፤ እንዳንሸሽ›› ድሮ፤ ልጆች ሆነን በሰርግ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በኩራት የሚዘፍኑት ዘፈን ነበር፡፡ በልጃቸው ‹‹ንፁህ›› ሆኖ ለወግ ማእረግ መብቃት ጎረቤትን ሁሉ ‹‹ስማችሁ? ልጃችን አኮራችን›› የሚሉበት ዘፈን፡፡ በዚያ ዘመን የሴት ልጅ ድንግልና የእሷ ብቻ አልነበረም፡፡ የቤተሰቧ ኩራትም ነው፡፡ ድንግል ሳትሆን ቀርታ ቤቶቿን ‹‹ያሸማቀቀች›› ሙሽራ እንደተውሶ እቃ ለቤተሰቦቿ የምትመለስበት ጊዜም ነበር፡፡ ዛሬም አለ፡፡ አሁን ግን በተለይ ከተማ ከተማውን ፤ ‹‹የጫጉላው ነገር መቼም ተረስቷል ለምስራቹ ጣት ይቆረጣል›› ተብሎ እስኪዘፈን ድንግልና ብርቅ ሆኗል፡፡ እነዚህን አሁን በውል የማላስታውሰው የነዋይ ደበበ ዘፈን ላይ ያሉ ስንኞች ስሰማ ሽማግሌውና ‹‹መሬው›› አጎቴ ትዝ ይለኛል፡፡ ዘፈኑ በመጣ ቁጥር የሚመለከተንንም የማይመለከተንንም አንድ ላይ ‹‹እያንዳንድሽ ይሄ ግጥም ላንቺ ነው›› በሚል ፊት እያየ ያስፈራራን ነበር፡፡ አንድ ሰሞን ውሃ እየጠፋ አስቸግሮ ቤት ውስጥ ያለነው ሴቶች በሙሉ ያለ አቅማችን በትልልቅ ጀሪካን ውሃ ተሸክመን ለመመላለስ ተገድደን ነበር፡፡ አመላልሰን ስንዳከም ፤የሁላችን ታላቅ የሆነችው የአክስቴ ልጅ ‹‹ አረ አጎቴ፤ እኔ በኃላ የለሁበትም፡፡ ያ ነገር እኮ በከባድ ሸክም ይሄዳል›› ብላው ሁላችንም ስንስቅ ‹‹አዎ የትም ስትንዘላዘሉ ትውሉና በኃላ የጀሪካን ውሃ ነው እንዲህ ያረገኝ በሉ!›› ብሎ እየተበሳጨ ወደ ቤት ሲገባ አስታውሳለሁ፡፡ አጎቴ ድንግልና እንደዋዛ ‹‹በመጥፋቱ›› ከሚቆጩ ‹‹ወግ አጥባቂዎች›› ውስጥ ነበር፡፡ ሰሞኑን እንዳነበብኩት ከሆነ ግን በከባድ ሸክምም ይሁን ‹‹በመደበኛው ሁኔታ›› ከድንግልናቸው የተለያዩ ሴቶች ሳይንስ ‹‹ዳግም ልጃገረድ›› የመሆን እድል ሰጥቷቸዋል፡፡ ነገሩ ቀዶ ህክምና ነው፡፡ ድንግልናን የሚመልስ ቀዶ ህክምና፡፡ እንደሚወራው በአለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች በእልልታ ተቀብለውታል፡፡ ‹‹ሳይንስ ሳይንስ መድሃኒቴ፤ መልሶ ሰጠኝ ልጃገረድነቴን›› እያሉ፡፡ ሰላሳ ደቂቃ በማይፈጅ ቀዶ ህክምና በግዴታም፣ በስህተትም፣ በውዴታም ድንግልናቸውን ያጡ ወይም የሰጡ ሴቶች ታሪካቸውን እንደ አዲስ የሚፅፉበት መልካም እድል ሆኗል፡፡ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዶላር ከፍለው ‹እድሳት›. ከሚያገኙት ሴቶች አብዛኞቹ ከወግ አጥባቂ ማህበረሰብ የመጡ እና ድንግል ሳይሆኑ መሰረግ ውርደት የሆነባቸው ናቸው፡፡ እንግዲህ ለእነዚህ ሴቶች ጉዳዩ ሳይንስ ተጠቅሞ ባህልን የማክበር ነገር ነው፡፡ የቤተሰብን ክብር የመጠበቅ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ አስረኛ ወይ ሃያኛ የጋብቻ በአላቸውን ሲያከብሩ ለባለቤታቸው የሚሰጡት ትልቅ ስጦታ እያደረጉት ነው፡፡ ለምሳሌ አንዷ አሜሪካዊት፤ ‹‹ …አስቡት፤ ከተጋባን 20 አመታችን ነው፡፡ ከዚህ በፊት ያልሰጠሁት ነገር የለም፡፡ ሽቶ ሰጠሁት፡፡ ውድ ሰአት ሰጠሁት፡፡. የቪዲዮ ጌም ሰጠሁት፡፡ አይፎንከ ከ1 እስከ 5 ሰጠሁት፡፡ በየደረጃው ያሉ አይ ፓዶች ሰጠሁት፡፡ ብዙ ብዙ… ነገሮች ሰጠሁት፡፡ ከዚያ ከዚህ በፊት ያልሰጠሁትን ምን ልሰጠው እችላለሁ ብዬ ሳስብ ስለዚህ ነገር ሰማሁና ‹ተሰራሁ›፡፡ ሲያገኘኝ ድንግል አልነበርኩም፡፡ ..እውነቴን ነው የምላችሁ ባሌ እንደዛ ተደስቶም አያውቅ!››ብላለች፡፡ ያለለት ደግሞ ድሮ ‹‹ኦርጅናሌ››ውን በደንቡ መሰረት ወስዶ ‹‹ሞደፊኩን› በስጦታ መልሶ በማግኘቱ ሁለት ጊዜ የአንድን ሴት ‹‹ብር አምባር›› ይሰብራል ማለት ነው፡፡ ስንቱ አንዴ አርሮበታል ያደለው ሁለቴ ይሰብራል! መቼም ጊዜው የትስስር ነው እና ይህ ነገር ዞሮ ዞሮ እኛ ጋር ከገባ (አለመግባቱን አላጣራሁም) ወንዶቻችን ‹‹ድንግል ነሽ?›› የሚለውን ጥያቄያቸውን ማብራራት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፡: ልክ እንደዚህ… እሱ፤ ድንግል ነሽ? እሷ፤ አዎ…! እሱ፤ ኦርጅናል ነው ወይስ ሞደፊክ?
Posted on: Sun, 30 Jun 2013 20:39:05 +0000

Trending Topics



...Rod went to town in
Calling all Dark Skins!!! you know who you are im Talking to YOU
Please share this post on your facebook to help us promote! We

Recently Viewed Topics




© 2015