በወንዶች 5000ሜ. ማጣሪያ - TopicsExpress



          

በወንዶች 5000ሜ. ማጣሪያ ተወዳድረው ወደፍፃሜው ያለፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሆቴል ተነስተው ወደውድድር ቦታ ሲመጡ ወደተሳሳተ አቅጣጫ በሚሄድ ባስ ተሳፍረው በመሄዳቸው ወደስታድየም ለመምጣት በድጋሚ ወደሄቴል ተመልሰው ትክክለኛውን ባስ ለመያዝ ተገደዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደሩት ሀጎስ ገብረሕይወት እና የኔው አላምረው ወደውድድር የገቡት ምንም ሳያሟሙቁ ነበር፡፡ አትሌቶቹ ምንም እንኳ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸንፈው ቢያልፉም በእንደዚህ አይነቱ ስህተት በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ በነበረው ውድድር ላይ ሳይካፈሉ የመቅረት ዕጣ ፈንታ ሊገጥማቸው የነበረ መሆኑ አስደንጋጭ ነገር ነው፡፡ አትሌቶቹ ወደሞስኮ የገቡት ዘግይተው እንደመሆኑ ከሆቴል ወደስታድየም ስለሚወስደው ትክክለኛ ባስ ቀድመው የደረሱት የቡድኑ ኃላፊዎች በደንብ ሊነግሯቸው ይገባ ነበር፡፡ በሁለተኛው ምድብ ከሞ ፋራህ እና ኢሳያህ ኪፕላጋት ጋር የሮጠው ሙክታር ትንሽም ቢሆን የሟሟቅ ዕድሉን ያገኘ ሲሆን ጠንካራ አትሌቶች ከነበሩበት ምድብም አንደኛ በመውጣት ለማለፍ በቅቷል፡፡ #Bizuayehu_wagaw
Posted on: Tue, 13 Aug 2013 15:30:52 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015