በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና - TopicsExpress



          

በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ ከነገ ዛሬ ይቀንሳል ሲባል እንደውም እየባሰበት ያለበት ሁኔታ ውስጥ ነው።በመሰረቱ ችግሩ ከስሩ ካላደረቁ በስተቀር የመቆሚያውም ቀን እንደናፈቀን ይቀራል። በኢትዮጵያና በሳውዲ አረቢያ መካከል ምንም አይነት የስራ ውል የለም እነደ አቶ ዘነበ ከበደ አገላጽ ይህ ቃለ መጠይቅ ከጀርመን የሬዲዮ ጣቢያ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት የተናገሩት ነው።ታዲይ ውልና የጋርዮሽ ስምንንት ሳይኖር እንዴት የስደተኞች ቁጥር አመት ካመት ይጨምራል??? በጅዳ ቆንስላ ውስጥ የሚገኙ ወደ 80 የሚጠጉ እህቶቻችን አሉ።እነዚህ ወገኖቻችን በተለያየ ምክንያት ወደቆንስላው የመጡ ሲሆን አብዛኛዎቹ ካሰሪዎቻቸው ግራ ባላቸው ያለመግባባትና ወደ አገር የሚያሳፍራቸው መንግስት ለመማጸን የተጠጉ ስደተኞች ናቸው።በወቅቱ ወደአገራቸው የሚያሳፍራቸው አካል በማጣት ለተለያዩ ችግር ይጋለጣሉ።አንዳዶቹ ራሳቸውን ይረሳሉ፣ይራባሉ፣ይጠማሉ በዚሁ ጅዳ ቆንስላ ውስጥ በዛሬው እለት አንድ እህታችን ራሷን አንቃ ለሞት ተዳርጋለች።የልጅቷን አሟሟት ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም ። የእህታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ውስጥ ያኑርል።
Posted on: Sun, 23 Jun 2013 19:00:21 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015