ባቡሩ እየመጣ ነው! መነሻውን ሃያት - TopicsExpress



          

ባቡሩ እየመጣ ነው! መነሻውን ሃያት ያደርግና በመገናኛ፣ 22፣ ዑራኤል፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮና ልደታ አድርጐ ጦር ኃይሎች ይደርሳል፡፡ ይህ የመጀመርያው ምዕራፍ የባቡር መስመር ዝርጋታ የ16.3 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ ከሰሜን ወደ ደቡብ የሚጓዘው ባቡር መነሻው ከፒያሣ (ከገነተ ፅጌ አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን) ይሆንና በአዲስ ከተማ፣ አውቶቡስ ተራና ሰባተኛ አድርጐ፣ ከጦርኃይሎች ከሚመጣው መስመር ጋ ይጣመራል፡፡ ከዚያም እስከ መስቀል አደባባይ ከተጓዘበኋላ ወደ ቀኝ ይታጠፍና ቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ አደባባይ ድረስ ይዘልቃል፡፡ ይህ የባቡር መስመር ዝርጋታ የ17.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይዟል፡፡ እያንዳንዱ መስመር 22 ፌርማታዎች ይኖሩታል፡፡ በጠቅላላው ግን 39 ፌርማታዎች ይዘጋጃሉ፡፡ እስከ 15ሺህ ሰዎችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ማጓጓዝ ይችላል፡፡ (ምዕራፍ አንድ) ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 41 ባቡሮች ወደ አገልግሎት ይሠማራሉ፡፡ በየፌርማታዎቹ መካከል በአማካይ እስከ 700 ሜትር ርቀት ይኖራል፡፡ በአንዳንድቦታ እስከ 400፣ እንደጐተራ ማሳለጫ አካባቢ ደግሞ እስከ 1.2 ኪሎ ሜትር ርቀትይኖረዋል፡፡ አንድ ተጠቃሚ ተገቢው ፌርማታ ጋ ለመድረስ ከ300 እስከ 400 ሜትር ብቻ በእግሩ መጓዝ ይጠበቅበታል፡፡ …በመከላከያ ኢንጅነሪንግ የሚገጣጠሙትን ጨምሮ ከውጭ ተገዝተው የሚመጡ ባቡሮችም ይኖራሉ፡፡ በሰዓት 80 ኪሎ ሜትር የመብረር አቅም እንዲኖራቸው ዲዛይን የሚደረጉ ናቸው፡፡ አገልግሎት ሲሰጡ ግን ፍጥነታቸው በሰዓት ከ30 እስከ 40 ኪሎ ሜትር ዝግ እንዲል ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም በአማካይ በየ700 ሜትር ርቀት ፌርማታ ስለሚኖር ነው፡፡ ሁለት ዓይነት የመጓጓዣ የኤሌክትሮኒክስና የወረቀት ትኬቶች ይዘጋጃሉ፡፡ አንድ ተጓዥ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኤሌክትሮኒክ ትኬቱ ከገዛ በኋላ በየጊዜው ሂሣብ እያስሞላ መጠቀም ይችላል፡፡ በተጨማሪም በየቦታው የተዘጋጁ የሂሳብ መሙያ ጣቢያዎችም ይኖራሉ፡፡ ተጠቃሚው ልክ ወደ ባቡሩ ሲገባ፣ በሩ ላይ ወደሚገኘው ትኬት አንባቢ መሣሪያ [SVT READER] ትኬቱን በማስጠጋት እንዲነበብለት ያደርጋል፡፡ በቂ ሂሣብ ካለው እንዲገባ ይፈቀድለታል፡፡ ይህን ሂደት የሚቆጣጠሩ መኮንኖችም በባቡሩ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ተጠቃሚው መውረጃው ጋ ሲደርስ በድጋሚ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቱን በሩ ጋ ወዳለው አንባቢ መሣሪያ በማስጠጋት እንዲነበብና ለተጓዘበት ኪሎ ሜትር ተገቢው ክፍያ እንዲቆረጥ ያደርጋል፡፡ አንባቢ መሣሪያውም ተጠቃሚው የተጓዘበትን ርቀት አስልቶ ሂሣቡን ይቆርጣል፡፡ (አንድ ተሣፋሪ ይህንን ሳያደርግ ከወረደ፣ መሣሪያው እስከ መጨረሻው ፌርማታ ድረስ ያለውን ታሪፍ አስልቶ ይቆርጥበታል፡፡ በዚህ ሂደት የባቡሩ ሠራተኞች (መኮንኖች) የትኬት ማንበቢያ መሣሪያውን በእጃቸው ይዘው ተገቢውን ቁጥጥርና ክትትል ያደርጋሉ፡፡ የወረቀት ትኬቱ በአብዛኛው ከክፍለ ሀገር ለሚመጡና የአጭር ጊዜ ቆይታ ላላቸው የአንድ ጊዜ ተጓዦች የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡ የባቡሩን መነሻና መድረሻ እንዲሁም እያንዳንዱን የሚቆምበትን ፌርማታ ለተሳፋሪዎች በድምጽና በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡ ለዚሁ በተዘጋጀው ስክሪን ላይ እንዲሁም በድምጽ ቀጣይ ፌርማታ የት እንደሆነም ይገልፃል፡፡ በአሁኑ ወቅት የባቡር ኦፕሬተሮች፣ ትኬተሮች፣ የቁጥጥር ባለሙያዎችና የመሳሰሉትን ለማሰልጠንም ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ (ምንጭ፡ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክትሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር በኃይሉ ስንታየሁ ናቸው)Iyere Shikur
Posted on: Fri, 30 Aug 2013 10:15:08 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015