ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? (ከዳኛ - TopicsExpress



          

ተስፋዬ ገብረአብ ማነው? (ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ) ዜግነቱ፣ ወያኔ-ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በዘር በጎሳ፣ በዘር ከፋፍሎን እያናቆረን ዓመታትን አስቆጥሮአል። ያልተጻፉ መርዘኛ መጽሐፎችን እያነባነቡና እየተረኩ ጨዋውን ሕዝብ ለበቀል ማዘጋጀቱን ቀጥሎአል። ሕዝብ እንዳይተማመን፣ ርስበርሱ እየተጨፋጨፈ እንዲለያይ፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ተበታትና እንዳትኖር ጉድጓድ መማሱን ቀጥሎአል። የበደኖ፣ የአርባጉጉ ክስተት እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ የተፈጸመ ድርጊት እንዳልሆነ ቁልጭ ብሎ የታየው ግን ከተስፋዬ “የቡርቃ ዝምታ” መርዛም መጽሐፍ በኋላ ነው። “ነፍጠኛ” በሚል ተቀጽላ በታጀበ ስልታዊ የወያኔ ደህንነቶችና ካድሬዎች ርምጃ ያለቁት የአማራ፣ የጉራጌ እና የሌሎች ዘሮች ቤት ይቁጠረው ብሎ ብቻ ማለፉ ለጊዜው በቂ ነው። ታዲያም ተስፋዬ ደራሲ ነኝ ይላል። በተከታታይም መጻፎችን አውጥቶአል። ደጋፊዎችንም አትርፎአል። ለመሆኑ ተስፋዬ ማነው? እውነት ጋዜጠኛ ወይስ ደራሲ ወይስ ሰላይ? የሚሉ ጥያቄዎች በተወሰኑ ማህበረሰባችን አእምሮ መግባታቸው አይቀሬ ነው። ኢትዮጵያዊ መሆን ያለመሆኑ ላይ ግን ከጥቂቶቹ በስተቀር፣ አብዘኞቻችን አልተጠራጠርንም። ግና ጊዜው ደረሰና የብዙዎች ጥርጣሬ በተለይም የነዚያ የነጻው ፕሬስ አባላት ጩኸት እውን ሆኖ ሊታይ ብቅ አለ። እንዴት? ተስፋዬ ገብረአብ በ1960 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ምድር፣ በደብረዘይት ከተማ ተወለድሁ ባይ ነው። እስከ አሥራ ሁለተኛ ድረስ ከተማረ በኋላ ወደ ሐረር ፖለቲካ አካዳሚ ሂዶ በ1980 ዓ.ም የጦር ሜዳ ጋዜጠኛነት ኮርስ ውስዶ ተመርቆአል። ከዚያም እንደሚለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ሂዶ በመሥራት ላይ እንዳለ በኢህአዴግ ጦር ይማረካል። ወያኔ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በ1983 ዓ.ም ሲቆጣጠር ከሠራዊቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ ገባ። በ1988 ዓ.ም ወደ አሜሪካ፣ ሲያትል ተልኮ የራዲዮ ጋዜጠኛነት ትምህርት ተከታትዬ ተመልሻለሁ እጁን ለሰጠበት አገር ሲል፣ በደራሲ ማስታወሻ ላይ ግን ወደ አሜሪካ ሲያትል የሄድኩት ለረፍት ነበር ይላል። የትኛው እውነት እንደሆነ መገመት የሚቻለው ግን የተስፋዬን ማንነት መገንዘብ ከቻልን በኋላ ነው። ተስፋዬ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ውስጥ በሃላፊነት ሰርቶአል። እፎይታ የተባለ አሳታሚ ድርጅት፣ እና መጽሔት ሥ/አስኪያጅ እንደነበረም ይታወቃል። ከዚህ አልፎ ተርፎም ተስፋዬ ቀንደኛ የወያኔ ደህንነት አባልም የነበረ ለመሆኑ ወደ ፊት የምናይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ተስፋየ በሥራ ላይ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ተስፋዬ ከላይ የገልጽሁትን መጽሐፍ፣ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ”፣ ጨምሮ ወደ ሰባት ……. welkait/wp-content/uploads/2013/10/tesfaye_gebreab_mannew.pdf
Posted on: Thu, 03 Oct 2013 03:36:00 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015