@ቲውተር መጠቀም@ - TopicsExpress



          

@ቲውተር መጠቀም@ ይፈልጋሉ?:----------------------------------------------------- እንግዲያውስ ይህን አጭር ማብራሪያ ያንብቡ በአቡ ዳውድ ኡስማን ቲውተር በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያሉት የማህበራዊ ድህረገፅ አንዱ ነው፡፡በሃገራችን ኢትዬጲያ በርካታ ተጠቃሚዎች ባይኖሩትም በውጪው አለም ግን በሚሊዬን የሚቆጠር ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችንም የቲውተርን ድህረገፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም ከፌስ ቡክ በተጨማሪ ቲውተር መጠቀሙ በርካታ ጥቀሞች የሚያስገኙለት በመሆኑ ሁሉም አጠቃቀሙን ይረዳው ዘንድ እንደሚከተለው በአጭሩ ማብራሪያ ተዘጋጅቶለት ቀርቧል፡፡ 1. ቅድሚያ የቲውተር አድራሻ እንዲኖረን አካውንት መክፈት ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ - ይህን ድህረገፅ twitterይክፈቱ -በመቀጠልም sign up የሚለውን በመጫን የሚጠይቀውን ሙሉ ስም፣ የኢሜል አድራሻ፣የይለፍ ቃል(password)፣ Username መሙላት - የሚጠይቀውን መጠይቅ ሞልተን ማጠናቀቃችንን ካረጋገጥን ቡሃላ Agree to the Twitter Terms of Service የሚለውን መጫን -በመጨረሻም Sign up for Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት ቻልን ማለት ነው፡፡ -አንዳንዴ ለማረጋገጥ በሚል የስልክ ቁጥር እንድናስገባ ሊጠይቀን ይችላል፡፡ ስልክ ቁጥራችን ያለበትን የሃገር ስም በመምረጥ ስልክ ቁጥራችንን እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም የማረጋገጫ ኮድ በስልክ ቁጥራችን ይላክልናል፡፡ እሱን በቲውተር አከውንታችን ላይ በማስገባት የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት እንችላለን ማለት ነው፡፡ 2. የቲውተር አካውንታችን ሙሉ መረጃዎችን እንዲይዝ መሙላት ሌሎች የቲውተር ተጠቃሚ ሰዎች በቀላሉ ከኛ ጋር ለመገናኘት ያስችላቸው ዘንድ ልክ በፌስቡክ ፕሮፋይል እንደምንሞላው ሁሉ በቲውተር ላይም በመሙላት በቀላሉ ከሌሎች ጋር መገናኘት ያስችለናል፡፡ 3. ከሌሎች ሰዎች፣ተቋሞች እና ሚዲያዎች ጋር ለመገናኘት የሚከተለውን ማድረግ - የቲውተር አካውንት መጠቀም ስንጀምር የቲውተር ድህረገፅ የራሱን ጥቆማ ያደርግልናል፡፡ ይህንንም Suggestions. የሚለውን በመጫን የምንፈልገውን መርጠን follow ማድረግ እንችላለን፡፡ - በራሳችን ለመፈለግም Search. የሚለው ቦታ ላይ የምንፈልገውን ሰው፣ድርጅት ወይም ሚዲያ በመፃፍ ፍለጋ ማድረግ እንችላለን፡፡ የፈለግነውን ስናገኝም ምርጫችንን በመጫን follow ማድረግ እንችላለን፡፡ 4. ቲውተር ላይ ፖስት ለማድረግ -በቲውተር ላይ ፖስት ማድረግ የሚቻለው በ 140 ቃላቶች ብቻ የተዋቀረን መልዕክት ነው፡ -ሃሳባችንን ወይም መልዕክታችንን ባጭሩ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ የምንጠቀምበትን አይነት ሳጥን ጋር በመጻፍ Tweet የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን -በፌስቡክ ፖስት ስናደርግ ታግ እንደምናደረገው ሁሉ በቲውተር ላይም “@” የሚለውን ፊደል ከምንፈልገው የሰው ስም ወይም ተቋም ስያሜ ቀድመን በመፃፍ ታግ ማድረግ እንችላለን -በቱውተር ላይም በፎቶ የተሰሩ ነገሮችን ፖስት ማድረግ የሚቻል ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ፖስት እንድናደርግበት በተዘጋጀው ሳጥን ስር በግራ በኩል ADD PHOTO የሚል እናገኛለን፡፡ እሱን በመጫን ከምንፈልግበት ቦታ ፎቶውን በመምረጥ ማስገባት እንችላለን፡፡ ታግ ማድረግ ከፈለግንም ወይንም ከፎቶ በተጨማሪ ፖስት ከምናደርገው ፎቶ ጋር መልዕክት ማስገባት ከፈለግን ፖስት ለማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ላይ በመፃፍ አንድ ላይ TWEET የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን -በቀላሉ መልዕክቶች አንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ ከተፈለገም ሃሽታግ መጠቀም እንችላለን፡፡ የምንፈልገውን መልዕክት ወይም ቃላት ፊት ይህን የመሰላል ምልክት (#) በማስገባት መልዕክቶቻችን በአለም ዙሪያ አንድ ቦታ ተሰባስበው እንዲቀመጡ ማድረግ ይቻላል፡፡ 5. ቲውተርን ላይ የምናገኛቸው ቃላቶች እና አጠቃቀማቸው - Follow፡ ይህ ማለት ልክ በፌስቡክ ፖስት የሚደረጉ ነገሮችን ለመከታተል አድ ፍሬንድ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሲሆን follow የሚለውን በመጫን ብቻ የፈለግነውን ሰው ወይም ተቋም የሚለቃቸውን መረጃዎች እና መልዕክቶች በቀላሉ መከታተል ያስችለናል፡፡ - Following:- ይህ ማለት Follow እያደርግናቸው ያሉ ሰዎችን እና ተቋማትን የማናገኝበት ምርጫ ነው፡፡ - Followers:-ይህ ማለት እኛን Follow እያደረጉ የሚገኙ ሰዎችን ዝርዝር የምናገኝበት ምርጫ ነው፡፡ - Replies.፡- ይህን የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ወይም ቲውት ባደረገው ነገር ላይ ሲሆን ምልክቱም ወደ ግራ የታጠፈ የቀስት ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም ልክ በፌስቡክ ኮሜንት እንደምንለው ነው፡፡ አስተያየት ወይም ምላሽ ለመስጠት Replies. የሚለውን በመጫን ምላሽ ወይም አስተያየት መስጠን እንችላለን፡ - TWEET፡-ይህ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ Post የሚለውን ምርጫ እንደምንጫን ሁሉ በቲውትር ላይም ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ TWEET የሚለውን በመጫን ይሆናል፡፡ - Retweets.፡- ይህንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በኩል መሃል ላይ ሲሆን ምልክቱም ሁለት ቀስቶች ወደላይ እና ወደታች ያሉበት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ሼር ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ አንድ ሰው ፖስት ያደረገውን ሼር ለማድረግ ስንፈልግ Retweet የሚለውን በመጫን ሼር ማድረግ እንችላለን - Favorites.፡ ይህንንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በቀኝ በኩል ሲሆን ምልክቱም የኮከብ ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ላይክ ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ ፖስት የተደረገውን ነገር ላይክ ለማድረግ Favorit የሚለውን በመጫን ላይክ ማድረግ እንችላለን፡፡ - More:- በዚህ ስር ደግሞ ፖስት የተደረገውን ነገር በግል የቲውተር ሜሴጅ ለመላክ፣ በኢሜል ለመላክ እንዲሁም ፖስት ያደረገውን ሰው ብሎክ ለማድረግ የምንጠቀምባቸውን ምርጫዎች የያዘ ነው፡፡ - Messages.፡ ይህ ምርጫ በቲውተር Follow እያደረግነው ከምንገኘው ሰው ጋር በውስጥ በኩል መልዕክት ለመለዋወጥ የምንጠቀምበት ምርጫ ነው፡፡ 6. የፌስቡክ አካውንታችንን እና የቲውተር አካውንታችን አንድ ጊዜ በጋራ እንዴት እንጠቀም ይህን ለማድረግ በቀላሉ የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር አካውንታችን ጋር በማገናኘት በአንድ ፖስት ሁለቱም ጋር ፖስት ማድረግ ያስችለናል፡፡ ይህ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ይኖሩናል ሀ. በፌስቡክ ፖስት የምናደረገውን ነገር በቲውተራችንም ላይ ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡ ይህን ለማድረግም የሚከተለውን Step ይከተሉ፡ -በቅድሚያ በፌስቡክ Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ -በመቀጠልም በSetting ውስጥ የተዘረዘሩት መካከል Followers የሚለውን ይጫኑ -በመቀጠልም Followers የሚለውን ሲከፍቱ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል አምስተኛውን Link my Profile to Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር አድራሻችንን በማስገባት በቀላሉ ከፌስቡክ አካውንታችን ጋር ማገናኘት እንችላለን፡፡ -ከላይ የተጠቀሰውን በቀላሉ ለማግኘት ይህን ሊንክ facebook /twitterበመጫን ማግኘት ይችላሉ ለ. በቲውተር ፖስት የምናደረገው በፌስቡክ አካውንታችን ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡ ይህን ለማድረግ የሚከተለውን Step ይከተሉ፡- -በቲውተር አካውንታችን Setting የሚለው ውስጥ ይግቡ --በመቀጠልም በSetting ውስጥ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ወደታች በመሄድ Apps የሚለውን ይጫኑ -በመቀጠልም Apps የሚለውን ስንከፍት Facebook Connect የሚል ምርጫ እናገኛለን፡፡ እሱን ምርጫ በመጫን የፌስቡክ አካውንታችንን በማስገባት የቲውተር አካውንታችንን ከፌስብከ አካውንታችን ጋር በቀላሉ ማገናኘት እንችላለን ማለት ነው፡፡ - አስፈላጊ ከሆነም ሁለቱንም በማገናኘት በፌስቡክ ፖስት ያደረግነውም በቲተር ፖስት እንዲሆን እንዲሁም በቲውተር ፖስት ያደረግነውም ደግሞ በፌስቡክ ፖስት እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡ - የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር ጋር ማገናኘታችን በዋነኝነት በቲውተር ከ140 ፊደላት በላይ የያዘ መልዕክት ማስተላለፍ ስለማይቻል በፌስቡክ የፈለግነውን መልዕክት ስንፅፍ በቲውተር ላይም ለሚገኙ ሰዎች የፅሁፉን ሙሉ መልዕክት በሊንክ ስለሚያስቀምጥልን በቀላሉ እንዲደርሳቸው ማድረግ ያስችለዋል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት አጠር ያሉ የቲውተር አጠቃቀም መግለጫዎች ማንኛውንም የቲውተር ጀማሪ ተጠቃሚ መጠነኛ ግንዛቤ በአላህ ፈቃድ ያስጨብጣሉ፡፡ አንብበው ሲጨርሱ ሼር በማደረግ ለሌሎች አጠቃቀሙን ያካፍሉ;;
Posted on: Sun, 14 Dec 2014 17:55:53 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015