አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ - TopicsExpress



          

አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 3ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰየሙ፡፡ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አቅራቢነት አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመን በፕሬዝዳንትነት ሰይመዋል፡፡ ተመራጩ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እስካሁን በ2 ጊዜ ምርጫ ማለትም ለ12 ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ ከነበሩት ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የፕሬዝዳትነት ስልጣኑን ተረክበዋል፡፡ ለፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ከ2/3ኛ በላይ የሆነውን ድምጽ ማግኘት ሲኖርባቸው ሙሉ ድምጽ በማግኘታቸው የኢፌዴሪ 3ኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡ በምስራቅ ወለጋ አርጆ ወረዳ አርጆ ከተማ የተወለዱት አምባሳደር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በኢፌዴሪ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊነትና በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ያገለገሉ ሲሆን በፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤነትና በቅርቡ ደግሞ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡
Posted on: Mon, 07 Oct 2013 12:18:18 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015