አበ ቶኪቾ እንዲህ ይለናል ። Abe - TopicsExpress



          

አበ ቶኪቾ እንዲህ ይለናል ። Abe Tokichaw ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዲህ ይላሉ፤ …በመፅሐፌ መደምደሚያ ላይ ለታሪክም ለህዝብም አስቀምጬ ማብቃት የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ፤ አብዛኛው የትግራይ ሊሂቃን ሥልጣን ወይም ሞት ብሎ ሥልጣን ለይ የሙጥኝ እስካለ ድረስ፣ አብዛኛው የአማራ ሊሂቃን በአፄዎች ዘመን የነበረውን የበላይነትን መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የህልም ፖለቲካ እስካልተወ ድረስ፣ ብዙሃኑ የኦሮሞ ሊሂቃን ኦሮሚያን ለብቻ የመውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሀገራችን ከአደጋ ቀጠና የምትወጣ አይመስለኝም፡፡ እኔ ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ እናንት ልሂቃን ሆይ እኒህን ሰውዬ ስሟቸው እና ተባብራችሁ ከአደጋ ነፃ የሆነች ሀገር ስሩልን!!! (በቅንፍም፤ ተስማምታችሁ አደጋውን ካራቃችሁልን፤ እኛ ምስኪኖቹ ውለታ መላሽ ነን…) >>>>>>>>>>>>>------------------------------------------>>>>>>>>>>>>>>>> በመጀመሪያ ያማራ የበላይነት ነበር ብለን እንቀበል ። [ for the sake of argument ] ! አቤ ቶኪቾ የሚባለው ግለሰብ መራራ የዐማራን የበላይነት ለማምጣት ብሎ የፈረጃቸውን ሰወች ያወቃቸው አይመስለኝም ። ካወቃቸውም በመረጃ ቢያስደግፈው ጥሩ ነበር ። መራራ እያወራ ያለው ያማራ ተቃዋሚወች መራራ በተራው ሊያመጣብን የፈለገውን የዘር ፖለቲካ ስለሚቃውሙት ኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፖለቲካ መጥፋት አለበት ብለው ስለሚታገሉ ሰወች ነው ። ይህንም በ ፱፯ [97] ምርጫ ወቅት መራራ ነፍጠኞች መጡብን ብሎ በግልጽ የተናገረው ነው ። በተጨማሪም መራራ የተገንጣይ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን የጠቀሰው እነኝህ ሰወች አስግተውት ሳይሆን ባሁኑ ሰዐት ያለውን የዘር ፖለቲካ አሜን ብለን እንደዐማራጭ እንድንቀበል ስልታዊ በሆነ መንገድ ሲጠራን ነው ። አቶ መራራ ያልገባው ነገር ቢኖር ያማራው ህዝብ ለኢትዮፕያ ብቻየን አላስብም ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች ብሎ የሚያምንበት ደረጃ ላይ እንጅ ያለው በየቦታው የተነሳን ኢትዮጵያን አፈርስብሃለሁ በሚል ማስፈራሪያ የተቋቋመን የጎጠኛ ሃይል የሚያባብልበት ምንም አይነት ምክኒያት የለውም ። ስለዚህ አቶ መራራ አማራ የዘር ፖለቲካ ዴሞክራቲክ ይሆናል ብሎ ስለማያስብ የርሰወን መድረክ የተባለ ድርጅት የሚደግፍበት ምንም አይነት ምክኒያት የለውም ። አቤ ቶኪቾ ይሄን ጽሁፍ ሲጽፍ ያማራ የበላይነት ነበር ። ያማራን የበላይነት ለማምጣት የሚሰሩ ሀይሎች አሉ ብሎ በሚያምን ድርጅት ውስጥ ስለሆነ መሪወቹ እንደመሩት ሲመራ ነው እንጅ ይሄ ጠፍቶት አይመስለኝም ። ፈለገ አስራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው ። Yesemen Kokeb Admas Keadmas Amara Force Eardo Amara አማራው አለቀ Mentewab Mentewab Ethiopia Meyesaw Kassa Keep Ethiopia
Posted on: Tue, 15 Oct 2013 14:49:28 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015