አፍሪካ ከሌላው ዓለም በተሻለ እምቅ - TopicsExpress



          

አፍሪካ ከሌላው ዓለም በተሻለ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ቢኖራትም ለዘመናት ሳትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ኢ/ያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት ሃብታቸው ወደ መጠቀም እያመሩ ነው፡፡ በተለይ የኤሌክትሪክ ሐይል በመጠቀም ረገድ አሁን ገና ቢሆኑም ጅምሮች እየታዩ ናቸው፡፡ ኢ/ያ ከአፍሪካ በአንደኛነተቱ የሚጠቀስ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ሐይል ማመንጫ እየገነባችን፡፡ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ(DRC) ከናይል ወንዝ ተፋሰስ አገራት አንዷ ናት፡፡ DRC ከዓለም ትልቁ የተባለለት የሐይል ማመንጫ ግድብ ልትገነባ ነው፡፡ እስከ አሁን የዓለማችን ትልቁ ግድብ የቻይናው Three Gorges dam (22 500 MW) ነው፡፡ አሁን ይህን ግድብ የሚበልጥ ከውደ DRC ሊገኝ ነው፡፡ DRC የሚትገነባው ግድብ 40ሺ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው ነው፡፡ ይህ በዋናነት በኮንጎ ወንዝ ተፋሰስ የሚገነባ ቢሆንም ዘሮ ዘሮ የናይል ውሃ ነው፡፡ DRC የኢንቴቤ ውል ካልፈረሙ የናይል ተፋሰስ አገራት አንዷ ናት፡፡ ባትፈርምም ግን እየተገበረችው ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት የአፍሪካ አገራትን በሐይል የማስተሳሰር ዓላማ ያነገበ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ያለው ግድብ መሆኑ የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የህዳሴ ግድብም የተፋሰሱ አገራት የሚጠቅም በመሆኑ ነው ከተለያዩ አገራት ድጋፍ እያገኘ ያለው፡፡ ኢ/ያ በአፍሪካ ከDRC ቀጥላ እምቅ የሃይድሮ ፓወር ያላት አገር ናት(she is powerhouse of Africa)፡፡ ከውሃ ብቻ 45ሺ ሜጋ ዋት የማመንጨት ዓቅም አላት፡፡ ይህ በአግባቡ ከተጠቀመችበት ከራሷ አልፎ ሌሎች አገራትም ጭምር ከሐይል እጥረት የሚያላቅቅ ይሆናል፡፡
Posted on: Sun, 07 Jul 2013 15:36:23 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015