ኢልመል ኢስናድ ወ ኢልመል ሪጃል - TopicsExpress



          

ኢልመል ኢስናድ ወ ኢልመል ሪጃል እና የሚሽነሪዎች ለቅሶ Part 1 ለምን ሀዲስ ዶኢፍ ይባላል? ሰሂህ፣ ዶኢፍ፣ ሀሰን ፣ መውዱእ ፣ መርፉእ ፣ መውቁፈ፣ ሙስናድ፣ሙአለቅ፣ ሙንቀቲ፣ሙረሳል፣ ሙተዋቲር፣አሀድ፣ገሪብ፣አ ዚዝ………. ወዘተረፈ የሚሉ ቃላት ከ ሐዲስ ሊቃውንት አንደበት የምንሰማቸው ሳይንሳዊ ቃላት መሆናቸው እንግዲህ የምናነባቸው የሀዲስ መፃህፍት መስካሪ ናቸው፡፡ በአላህ ይሁንብኝ !!!!! የትኛውም ታሪካዊ መንፈሳዊ ሳይንስ ወይም የታሪክ ቁሳዊ ጥናት እና ምርምር ከዚህ መስክ በጥልቀትም ሆነ በስፋት አይበልጥም፡፡ ይህን ሳይንስ ከ አጥንት እና ደም ጋር ለማዋሀድ ከፈለክ ህይወትህን ለመስኩ መሰዋት ማድረግ ይኖርብሀል፡፡ እናም ይህን የሐዲስን መስክ ብርቅዬ ኢስላማዊ ሰይንስ ነው ስልህ ከበቂ በላይ በራስ መተማመን ነው፡፡ እነሆ ይህ ምርጥ እና ድንቅ የሆነውን ሳይንስ ነው እንግዲህ ሚሽነሪዎቸን ያስቆጣቸው፡፡ እንዲ ያስቆጣቸው እና እሪ! ያስባላቸውን ምክንያት በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን 1. መፅሀፍ ቅዱስ በዚህ የሀዲስ መስፈርት ቢፈተሸ መውዱእ(ቅጥፈት)ሊባል ነው፡፡ አረ! መውዱእ እንኳ አይገባውም ሰነድ ያለው መውዱእ እኮ አለ!! ከመውዱእ በታች ደረጃ ቢኖር ኖሮ ያንን ደረጃ ነበር ሚያገኘው ማን? ያንተው መፅሀፍ መፅሀፍ ቅዱስ!!! 2. ይህ ሳይንስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው በ ሙስሊም ሊቃውን ነው፡፡ ቅጥፈት እና ትክክለኛ ዘገባውን እንዲለይም ምክንያት ሆኖታል፡፡ ሚሽነሪው ለሚያነሳው ሀዲሳዊ ጥያቄ በዚህ ሳይንስ ምላሽ በተገቢው መልኩ ስለሚያገኝ አስቆጥቶታል ይህ ጉዳይ እንደ እግር እሳት ከለበለባቸው ሚሽነሪዎች አንዱ Jochen Katz ሲሆን ጥቅምት 8 ፣1998( እንደ ባህር ማዶ) እንዲህ ሲል ፅፏል That is a bogus argument from an Islamic point of view. ሹፍ ይህን የሐዲስን ሳይንስ ነው እንግዲህ ሐሰት ሲል ለማጣጣል የፈለገው ፡፡ ይህም ንግግሩ የሰው መሳቂያ እና መሳለቂያ ከመሆን የዘለለ ትርፍ አላስገኘለትም ነበር፡፡ አንዳንድ ሚሽነሪዎችም የካዘን ንግግር እንደወረደ ኮርጀው ሲያበቁ እንደ ፎቶ ኮፒ ማሽን ሲያባዙት ለማየት ችለናል፡፡ እነዚህ ተራ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ሚያባዙትን ወረቀት እስከዚህም ክብደት አልሰጠሁትም እንዲሁም በቀላሉ ላልፈው አስቤ ነበር ምክንያቱም ሲጀመር ሰው አእምሮ የተሰጠው እንዲመራመርበት ነው እንጂ ያገኘውን በጭፍኑ እንዲያባዛበት አይደለም ፡፡ እናስ የዚህ ፅሁፍ አላማ ምንድነው? ለሚል ጠያቂ ግን ምሰጠው ምላሽ ይህን ሳይንስ ላላወቀው ኢንተሮዳሽን መስጠት ነው፡፡ ይህም አጭር መግቢያ ባህር ሳይኖር ለመዋኘት፣ክንፍ ሳይኖረው ለመብረር ለሚያስብ ሰው ሁሉ ሙከራው አደገኛ እንደሆነ አሳውቆ ከዚህ አደገኛ ሙከራ የሚታደግ ደራሽ መርከብ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ…… እንቀጥል…. ይህ ለ ካዝ ሐሰት ሆኖ የታየ ግን ተአምራዊ የሆነውን የሐዲስን መስክ ታዋቂው ኦሬንታሊስት አለም በሙሉ ድምፅ ሚስማማበት የታሪክ ምሁር Bernard Lewis አጥንቶ ሲያበቃ እንዲህ ይለናል፡፡ ምን ነበር ያልከው? From an early date Muslim scholars recognized the danger of false testimony and hence false doctrine, and developed an elaborate science for criticizing tradition. Traditional science, as it was called, differed in many respects from modern historical source criticism, and modern scholarship has always disagreed with evaluations of traditional scientists about the authenticity and accuracy of ancient narratives. But their careful scrutiny of the chains of transmission and their meticulous collection and preservation of variants in the transmitted narratives give to medieval Arabic historiography professionalism and sophistication without precedent in antiquity and without parallel in the contemporary medieval West. By comparison, the historiography of Latin Christendom seems poor and meager…(1) W Montgomery Watt በበኩሉ it would have been easy to invent sayings of Muhammad. Because the cultural background of the Arabs had been oral the evidence that came to be expected was the chain of names of those who had passed on the anecdote containing the saying . . . The study of Traditions rapidly became a distinct branch of the studies of the general religious movement. It was soon realized that false Traditions were in circulation with sayings that Muhammad could not possibly have uttered. The chains of transmitters were therefore carefully scrutinised to make sure that the persons named could in fact have met one another, that they could be trusted to repeat the story accurately, and that they did not hold any heretical views. This implied extensive biographical studies; and many biographical dictionaries have been preserved giving the basic information about a mans teachers and pupils, the views of later scholars (on his reliability as a transmitter) and the date of his death. This biography-based critique of Traditions helped considerably to form a more or less common mind among many men throughout the caliphate about what was to be accepted and what rejected..(2) የታሪክ ምሁራንን ያስገረመው እንዲሁም ሚሽነሪዎችን አንገት ያስደፋው ይህ ተአምራዊም ታሪካዊም መስክ የምስክርነት መታወቂያ ወይም የታሪካዊነት ማረጋገጫ ያገኘው ከ በርናንድ ልዊስ ወይም ከዋት ብቻ መስሎህ እንዳትስት እንደነ Saadia Gaon(3) እንዲሁም Alfred Guillaume (4) ሌሎችም ምሁራን ከአይሁድ ፅሁፎች ጋር እያወዳደሩ ፕሮፌሽናል ሳይንስ እንደሆነ ደግመው ደጋግመው ጭንቅላቱ ን ለምርምር ለሰጠ ተማሪ አሳውቀዋል ፡፡ የሆነ ሆኖ ምሁራን ፐሮፌሽናል ሲሉ ያንቆለጳጰሱት ይህ የሀዲስ መስክ ምንድ ነው? እኮ ምን ?....... የሐዲስ ትርጉም ምን ይሆን? አዎ! ምን ድነው? ምንነቱ በወጉ ስላልታወቀ ነገር ብነግርህ ትደናገር ወይም ትደናበር ይሆናል በመሆኑም ስለ ሀዲስ ሳይንስ ትንታኔ ውስጥ ዘው ብዬ ከመግባቴ በፊት ቀጥታ ትርጉሙን ብነግርህ ላንተ ትልቅ ውለታ ነው፡፡ ሐዲሰ ማለት በቋንቋ ደረጃ ዘገባ ማለት ነው ፡፡ በሙስሊሙ ዘንድ በነብዩን እንዲሁም በባልደረቦቹን የተዘገበን ዘገባ ለመግለፅ ወካይ ቃል ሆኖ ግልጋሎት ላይ ውሏል፡፡ ይህን ሐዲስ በመዘገብ ዘንድ ሙስሊም ምሁራን ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳደረጉ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ዘገቡ ማለት ግን የዘገቡት ሁሉ ትክክል ነው የሚል ትርጉም ይሰጣል ብለህ ደግሞ እንዳትስት ምክንያቱም ሁሉም ዘጋቢዎች የዘገቡትን እውነት ወይም ሀሰት እንደሆነ እንዳላረጋገጡ ነግረውናል፡፡ ታዋቂው የታሪክ ምሁር በራንድ ልዊስ እንዳለህ ከነብዩ በኋላ በጣም ብዙ ሰዎች ነብዩ እንዲህ ብሏል ሰሃቦች እንዲህ ብለዋል ሲሉ የሐሰት አቧራ ማጨስ ጀመሩ ልክ ከ እየሱስ በኋላ ክርስትያኑ በእየሱስ ላይ መቅጠፍ እንደጀመረው ሲብስ በዝሙት እንደወነጀሉት(5)፡፡ እዚህ ጋር አንድ መነሳት ያለበት ጥያቄ አለ እሱም በክርስትናው አለም እና በሙስሊሙ አለም ያለው ልዩነት ምንድ ነው ሚለው ጥያቄ ሲሆን ምላሹም ክርስትያኑ ስለ እየሱስ አንድ ነገር ከተባለ እየተቀባበለ እንደ ገደል ማሚቱ ሲያስተጋባው ቆየ አሜንም ሲል ተቀብለው፡፡ የእምነቱ ክፍል አድርጎም በጭብጨባ አፀደቀው ፡፡(6) ሙስሊሙ ጋር ግን ይህ አይነት ፈሊጥ አልሰራም ከነብዩ እንዲሁም ከባልደረቦቹ ነው የተሰማው ተብሎ አንድ ዘገባ ከተሰማ ይጣራል ይፈተሸል ፡፡ አእምሮህ እንዴት? እኮ እንዴት ? ብሎ መጠየቁ አይቀርም ይህ ጥያቄ ወደ ሀዲስ ሳይንስ ያስገባናል፡፡ የሐዲስ ሳይንስ ይዘት እና ትንታኔ ይህ ተአምራዊው ስል ምነግርህ ፕሮፌሽናል ሐዲስ የተገነባው ከሁለት ክፍል ነው፡፡ የመጀመሪያው መተን(ቀጥታ ፅሁፉ) ሲሆን ሁለተኛው እና ዋነኛው ኢስናድ(የዘገባ ቅብብሎሽ መስመር) ነው፡፡ እናም እንደ ኢስላም አንድ ሀዲስ ያለ ዘገባ ቅብብሎሽ ቢመጣ መስመር ተቀባይነት የለውም፡፡(7) ሚሽነሪውም ካዝ እንዲያለቅስ ምክንያት የሆነው ይህ ኢስናድ ሚሉት አስለቃሽ ጭስ ሲሆን እንዴት ሊያስለቅሰው እንደቻለ በስተኋላላይ እመለስበታለሁ ….ኦኬ የታላቁ የሐዲስ ሊቅ የኢማም አል ቡኻሪ አስተማሪ አብደላህ ኢብኑ ሙባረክ(d. 181 AH) እንዲህ ሲል ፅፏል ኢስናድ የሐይማኖት(የኢስላም) ክፍል ነው፡፡ ኢስናድ ባይኖር ኖሮ ማንም እንደልቡ በቀጠፈ ነበር(8) ነበር ባይሰበር ፡፡ በኢስላም አንድ ዘገባ መፈተሻ ይሆን ዘንድ ኢስናድ ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ይህም ኢስናድ ሁለት ሰፊ ሀዲስ መፈተሻ ስልቶችን ለመውለድ በቃ፡፡ እነዚህ ሳይንሳዊ መስፈርቶችን እንደወረዱ በወፍራሙ አንብብልኝ፡፡ • ኢልመል ኢስናድ • ኢልመል ሪጃል 1. ኢልመል ኢስናድ፡- ይህ የሳይንስ መስክ ሚያጠናው የ አንድን ዘገባ ቅብብሎሽ መስፈርት ነው ፡፡ ይህንም ሳይንስ በምሳሌ ማየት ካስፈለገ በምሳሌ እንመልከተው፡፡ ተመልከት ሶስት ግለሰቦች ይኖራሉ እንበል እነዚህምን ግለሰቦች X,Y,Z ብለን የእምባሻ ስም እንስጣቸው ፡፡ - - - አንበልና አንድ ዘገባ ከሆነ ምንጭ ይነገራል ይህን ምንጭ( source ) እንበለው ዘገባውም ሲነገር X ይሰማና ለ Y ያቀብለዋል፡፡ Y ዘገባውን ተቀብሎ ሲያበቃ ለ Z ያስተላልፋል፡፡ ይህ የዘገባ ቅብብሎሽ መስመር ኢስናድ ይባላል (Source------X---------Y----------Z) በኢስላም አንድ ዘገባ ከነብዩ መጣ ወይም ከአንድ የነብዩ ባልደረባ መጣ ተብሎ ሲነገር በመጀመሪያ ደረጃ ኢስናዱ ይታያል ፡፡ ማን? ኬት ? አመጣው ተብሎም ይፈተሻል ከዛ በኋላ ነው ሀዲሱ ደረጃ ሚሰጠው፡፡ ተመልከት ለምሳሌ Z ተነስቶ X እንዲህ ቡሏል ስላለ ብቻ እውነት ነው ተብሎ አይታለፍም ከማን አመጣሀው ይባላል Y መጥቀስ ካልቻለ ይህ ዘገባ ሙንቀቲ(የተሰበረ) ዘገባ ይሆናል፡፡ ዘገባውም ዶኢፍ ( ደካማ) የሚል ቻባ ወይም Stamp of approval ያገኛል ፡፡ ሁሉም ኢስላማዊ ዘገባዎች በዚህ መስክ የተዳሰሱ ናቸው፡፡ በተምሳሌትነት አንድ ሶሂህ ዘገባን እናንሳ ስራ ሁሉ በኒያ ነው…(9) የሚለውን ሀዲስ ነብዩ ተናግረዋል ከተባለ ጥያቄው ይህ በየተኛው ኢስናድ ነው የመጣው? የሚል ይሆናል ፡፡ እንደሚታወቀው ሀዲሱ ቡኻሪ በሰሂሃቸው ዘግበውታል፡፡ እስከ ቡኻሪም ድረስ የመጣበት ኢስናድ ሊታወቅ የግድ ነው ፡፡ የሆነ ሆኖ ኢማሙል ቡሀሪ ይህን ሀዲስ በሚከተለው ኢስናድ እንደመጣ ነግረውናል፡፡ ኢማም አል ቡኸሪ-------ሁመይድ አብደላህ ኢብኑ ዙበይር---------ሱፍ ያን----------ያህያ ኢብን ሰኢድ አልአንሳሪይ-----ሙሀመድ ኢብን ኢብራሂም አተሚ---------አልቃማህ ኢብን ወቃስ---------ኡመር ኢብኑል ኸጣብ---------- ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.አ.ወ) ተመልከት ይህ ሀዲስ በዚህ መስመር ነው የመጣው እያንዳንዱ አስተላላፊ ሲዘግብ የነበረው ምንጩን እንዲሁም ኢስናዱን በመጥቀስ ነው፡፡ ያለ ምንጭ ከመጣማ እንዴት ተቀባይነት ይቻረዋል፡፡ በጭራሽ! በፍፁም፡፡ እናም አንድ ሀዲስ ትክክለኛ ነው ለማለት የመጀመሪያው መስፈርት ኢስናድ አለው የሚል ይሆናል፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ኢስናድ የለውም ይህ ታሪካዊ ሀቅ ነው እንግዲህ ካዝን ያስለቀሰው፡፡ ሚያባብለው ሲያጣም ውሽት ሲል ሀዲስን ለማጣጣል ቢፈልግም የሰው መሳቂያእና መሳለቂያ ከመሆን ባሻገር ትርፍን አለተረፈም፡፡ የሆነ ሆኖ የካዝን ነገር ለ ካዝ ልተወውና ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ወንጌሎች ልመልስህ፡፡ ይህ መለኮታው ስትል ምታምንበት ወንጌል ኢስናድ አለው ከማለታችን በፊት ፀሀፊው ይታወቃል የሚለው የመጀመሪያ ጠያቄ ይሆናል ?ተራ ሚሽነሪዎች እና ፎቶ ኮፒ ተከታዮቻቸው ምናልባት አዎ!!! ሊሉን ይችላሉ ይህን ጉዳይ ግን ምሁራን አይቀበሉትም፡፡ እንደነ ፕሮፌሰር በርት ኢህራማን ገለፃ መሰረት ይህ ወንጌል ሲገኝ ማን እንደፃፈው እራሱ አይቀልፅም፡፡ ቀጣዩ ጥያቄ ወንጌሉ ፀሀፊው ማን እንደሆነ ካልገለፀ ማን ማትዮስ ማርቆስ ሉቃስ ወይም ዮሐንስ የሚል የዳቦ ስም ሰጠው? የሚል ሲሆን ያለው ብቸኛ መልሱ ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ናቸው የሚል ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ወንጌሎቹን አጥንተው ሲያበቁ ፀሀፊያቸው እንደማይታወቅ ምሁራን በአራት ነጥብ ደምድመውታል፡፡ የአለም እውነታዎችን ሰብስቧል ተብሎ ሚታመንበት ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህም ሲል እውነቱን ሳይጨምር ሳይቀንስ ይነግርሀል የማትዮስ ወንጌል ፀሀፊ አይታወቅም˝ (10) ˝የማርቆስ ወንጌል ፀሀፊ አይታወቅም̋ (11) ̋የሉቃስ ወንጌል ፀሀፊ አይታወቅም˝ (12) ˝የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ አይታወቅም˝(13) ይህ መለኮታዊ ተብዬ ወንጌል በማን እንደተፃፈ እንዲሁም በማን እንደተላለፈ ሳይታወቅ እንዴት ትክክለኝነቱ ነው ሊባል ይችላል?፡፡ አልፎ ተርፎ ኦርጅናል ማመሳከሪያው ጠፍቷል፡፡ ፕሮፌሰር በርት ኢርሀማን እንደሚነግረን ከሆነም የኦርጅናሉ ኮፒ የኮፒውም ኮፒ ጠፍቷል በወፍራሙም እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ ˝In any event, none of [the original manuscripts of the books of the Bible] now survive. What do survive are copies made over the course of centuries, or more accurately, copies of the copies of the copies, some 5,366 of them in the Greek language alone̋(14) በመሆኑም ኢስናድ አልባ ፅሁፍ ነው ማለት ነው፡፡ የያዝከው መፅሀፍ እና ይህን ጉድ ለ አንድ ኢለመንተሪ የሐዲስ ተማሪ ብትነግረው ጊዜ ሳይወስድበት መፅሀፍህ መውዱእ (ቅጥፈት) ነው ይልሀል፡፡ በሌላ አባባል በመፅሀፍህ ላይ ብይን ለመስጠት የግድ የሀዲስ ጠበብት መሆን አያስፈልግም፡፡ የሆነ ሆኖ አንድ ሀዲስ የተለለፈበትን ሂደት አስመልክቶ በተለያዩ ደረጃዎች ይመደባል፡፡ ይህ ጉዳይ እጅግ በጣም ጥልቅ ስለሆነ አልገባበትም፡፡ 2. ኢልመል ሪጃል ፡- እንዳልኩህ በኢስላም አንድ ዘገባ ያለ ኢስናድ ከመጣ እጣው ቁሻሻ ማጠራቀሚያ ከመሆን የዘለለ አይሆንም ፡፡ በኢስናድ ካልመጣ ተቀባይነት የለውም የሚለው ካሴት ሲገለበጥ ግን በኢስናድ ቢመጣ ተቀባይነት አለው የሚልን መልእክትን አላዘለም፡፡ ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፡፡ እንዴት ላለ ጠያቂ ጥያቄው ወደ ሁለተኛው ሳይንስ ይመራዋል እሱም ኢልመል ሪጃል ወደ ሚለው ፕሮፌሽናል ሳይንስ ፡፡ ይህ ሳይንስ የሚያጠናው በኢስናድ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ማንነት እና ሙሉ የህይወት ታሪካቸውን ነው ፡፡ ከላይ የጠቀስኩትን ምሳሌ ልድገምልህ ፡፡ ተመልከት (Source------X---------Y----------Z) ይህ ከሆነ ኢስናዱ በኢስናዱ ውስጥ የተሳተፉት ስብእናዎች በሙሉ ይጠናሉ፡፡ ለምሳሌ በዘገባ ቅብብሎሽ መስመር ውስጥ ካሉት ስብእናዎች ውስጥ አንዱ X ነው፡፡ ኢልመል ሪጃል ሚያጠናው X ማነው፡፡ X - የተባለው ስብእና ከትውልዱ እስከ እድገቱ ፣ ስነምግባሩም ከሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ይጠናል፣ የማስታወስ ችሎታው፣ ለጊዜያዊ ጥቅም ሲል ዋሽቶ ወይም አታሎ ያውቃል ፣ ሰዎች ስለ ማንነቱ ምን ይላሉ እና መሰል ነገሮች በጥንቃቄ ይጠናሉ፡፡ ተጠንተውም ሲያበቁ አስተላለፈ የተባለው ሀዲስ በመስኩ ምሁራን ብይን ሰጥበታል፡፡ በዘገባ ቅብብሎሽ መስመር የተሳተፈ ስእብእና ሁሉ በዚህ ሳይንስ ከመፈተሸ አይተርፍም፡፡ ለምሳሌ አንድ ታሪክ መጥቀስ ይቻላል ያውም የታላቁ የሀዲስ ሊቅ የ ኢማም አል ቡኻሪ ፡ ይህ ሰው ሀዲስ ለመፈለግ አህጉራትን አቆራርጦ ሀዲስ አለበት ወደ ተባለ መንደር ይሄዳል፡፡ ያ ሀዲስ ያውቃል የተባለው ግለሰብ ጋር እንደደረሰ ማንነቱን ከጠየቀ እና እሱነቱን ካረጋገጠ ቡሀላ አንድ ነገር ይከሰታል ፡፡ ይህ ሀዲስ ያውቃል የተባለው ግለሰብ አህያ ነበረችው ለሆነ ስራ ይፈልጋትና አህያዋን ይጠራታል፡፡ አህያዋም ልትመጣለት አልቻለችም፡፡ ይህን ተያያይዞ ይህ ግለሰብ ቤቱ ውስጥ በመግባት ባዶ ሠሀን ያመጣና ምግብ እንዳለው አስመስሎ አጠገቡ ያስቀምጠዋል፡፡ አህያዋም በጣም ስለራባት ምግብ ያለው መስሏት ስትመጣ ይህ ሰው አህያዋን ይይዛታል፡፡ ኢማም አል ቡኻሪ የዚህ ግለሰብን ስራ አይተው እንዳበቁ ሀዲስ ሳይቀበሉት ጥለውት ሄዱ፡፡ ለምን አህያዋን ስላታለት፡፡ የነብዩን ንግግር ቢያታልልስ ምን ዋስትና አለ!!!፡፡ ሹፍ ቡኻሪ አህጉራትን ለሃዲስ ሲሉ አቆራርጠው መተው ሲያበቁ ሀዲስ ይዟል ተብሎ በሚታወቀው ስብእና ላይ ባዩት ባህሪ አማካኝነት ሀዲሱን ጥለውት ሄዱ፡፡ ጥንቃቄ ይልሀል ይህ ነው፡፡ በመሆኑም በዘገባ ቅብብሎሽ መስመር ያለ አንድ የሀዲስ አስተላላፊ አታላይ ከሆነ አሊያም የማስታወስ ችሎታው ደካማ ከሆነ ወይም ተአማኒነት ከሌለው ወይም ከማን ሀዲስ እንዳመጣ ካላወቀ አንድ ሀዲስ ተቀባነት አይኖረውም ዶኢፍ ስለሚሆን ውድቅ ይደረጋል ፡፡ ምሳሌ እንመልከት ዝሙተኛ በውግራት መገደል አለበት የሚል የቁርአን አንቀፅ ወርዶ ነበር ግና ባሁኑ ቁርአን ላይ እንዳይካተት ተደርጓል የሚለው አንዱ የሚሽነሪዎች ክስ ነው ﻋﻦ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﻗﺎﻟﺖ ﻟﻘﺪ ﻧﺰﻟﺖ ﺁﻳﺔ ﺍﻟﺮﺟﻢ ﻭﺭﺿﺎﻋﺔ ﺍﻟﻜﺒﻴﺮ ﻋﺸﺮﺍ ﻭﻟﻘﺪ ﻛﺎﻥ ﻓﻲ ﺻﺤﻴﻔﺔ ﺗﺤﺖ ﺳﺮﻳﺮﻱ ﻓﻠﻤﺎ ﻣﺎﺕ ) 15 ( ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻭﺗﺸﺎﻏﻠﻨﺎ ﺑﻤﻮﺗﻪ ﺩﺧﻞ ﺩﺍﺟﻦ ﻓﺄﻛﻠﻬﺎ አረበኛው ሀዲስ ይህን ይመስላል ይህን ሀዲስ ይዘው ሲያበቁ ሚሽነሪዎች ዝሙተኛ በውግራት የሚናገረው የቁርአን አንቀፅ ጠፍቷል ሲሉ ሲያስተጋቡ አይተህ ይሆናል (ይህ ዘገባ የታሪክ ዘጋቢዎች በተለያየ መፅሀፎቻቸው ላይ ዘግበውታል)፡፡ ይህ ሀዲስ ደረጃ ኢስናድ አለው ለሚለው ጥያቄ መልሱ አዎ አለው የሚል ነው፡ መልሱ!!! ቀጣዩ የኢልመል ሪጃል ውጤቱ ምን ሆን የሚል ሲሆን የጥንትም የሁኑም ምሁራን ለዚህ መልስ አላቸው፡፡ እሱም በዘገባ ቅብብሎሽ መስመር ውስጥ የተላለፈው አንዱ ግለሰብ ሙሀመድ ኢብን ኢስሀቅ ይባላል ይህ ግለሰብ ሀዲሱን ኬት እንዳመጣው አያውቅም(16) ስለዚህ የሐዲሱ ዶኢፍ እና ውድቅ ነው ለመረጃነት ሊበቃ አይችልም፡፡ የሱራ አህዛብ አንቀጽ ጠፍቷል ርዝመቱ የሱራ አልበቅራ ያክላል ግና ዚር እንዳለው እየተቀራ ያለው አንቀፅ 73 ወይም 72 ነው ተብሎ የተዘገበው ሀዲስም ተመሳሳይ እጣ ፋንታ ይገጥመዋል(17)፡፡ ሀዲሱ ሚሽከረከረው የዚድ ኢብን አቢ የዚድ በተባለው ስብእና ላይ ሲሆን የዚህ ሰው ሀዲስ ተቀባይነት የለውም ምክንያቱም ልክ እንደ ሙሀመድ ኢብን ኢስሀቅ የኢልመል ሪጃል መስፈርት ሊያሟላ ባለመቻሉ የሆነ ሆኖ የቁርአን አንቀፆች እንደጠፉ ሚናገሩ ሀዲሶች አሉ የሚለውን ጉዳይ ወደ ፊት የቁርአን አንቀፆች ወይስ የአዲስ ኪዳን የማን ነው የጠፉት በሚል ርእስ በጥልቀት አላህ ካለ እመለስበታለው ኢንሻአላህ !! ይህ በምሳሌነት ስለ ቁርአን ከሚሰነዘሩ ትችቶች የቀረበ ሲሆን ለምሳሌነት ብቻ ነው በአጭሩ የነካካሁት ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ስመልስህ መፅሀፍ ቅዱስን ራሱ ኢስናድ ባይኖረውም ማርቆስ ፃፈው የተባለውን እንዲሁም ዮሐንስ ፃፈው የተባለውን ወንጌልን ፀሀፊዎቹ ባይታወቁም የማርቆስ ወንጌል ፀሀፊ እና የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ እያልን በዚህ በኢልመል ሪጃል መስፈርት እያነፃፀርን ሁለቱን ፀሀፊዎች እንመዝናቸው፡፡ የቂጣው በአል የእየሱስ ስቅለት በመጀመሪያ አንባቢ ግር እንዳይለው ስለ ቂጣው ፋሲካ በአል መግቢያ ለመስጠት ልገደድ ነው፡፡ ይህ በ አይሁዶች ዘንድ ልክ እንደ ኢድ ትልቅ በአል ተደርጎ ሚወሰድ ሲሆን ምንጩን ያደረገው ኦሪት ዘፃእት 7-12 ፡፡ ታሪኩ በአጭሩ ፈረኦን የእስራኤል ህዝቦችን ነፃ ስላላደረገ ከ እግዚአብሄር አስር መቅሰፍት ይፈራረቁበታል፡፡ አስረኛው መቅሰፍት በእጅጉ የከፋ ሲሆን እሱም በኩር ሆኖ የተወለደ ልጅ እና እንስሳት ሞት ነው፡፡ ፈረኦን ባጠፋው የህፃናት እና እንስሳት ሞት ምክንያቱ ባይገባኝም ግና ምን ታረገዋለህ ተወሰነ አሜን ብለህ ተቀበል፡፡ ይህን ተያይዞ እግዚአብሄር ሙሴን በእስራኤላውያን ቤት ላይ ደም ምልክት እንዲያደርግ ያዘዋል ምክንያቱም እግዚአብሄር በዛ ሲያልፍ ደሙን ያየውና የኢስራኤላውያን ቤት መሆኑ ተረድቶ ያልፋቸዋል፡፡ ደም የሌለበት ቤት ግን ካየ የግብፃውያን ቤት መሆኑን አውቆ እዛ ውስጥ ያሉትን እንስሳት ሆነ የበኩር ወንድ ልጆችን ይፈጃቸዋል፡፡ አሁንም እዚህ ጋር እግዚአብሄር የእስራኤላውያንን እና የግብፃውያንን ቤት ለመለየት ደም መጠቀሙ በእጅጉ ይደንቃል አምላክነቱንም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል ይሁን ብቻ ብዬ ልለፈው፡፡ እግዚአብሄር የደም ምልክት አይቶ ሲያበቃ እስራኤላውያንን ስላለፋቸው( pass over them)… ባአሉ በእንግሊዘኛው pass over ለመባል ችሏል፡፡ መፅሀፍ ቅዱስም እንደሚሚነግረን ይህን አስረኛውን የመቅሰፍት ቀን (ፈጣሪ ምልክት የተጠቀመበትን ቀን) ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እግዚአብሄር ይህን ቀን ቋሚ በአል አድርገው ለዘልአለም እንዲይዙት ያዛቸዋል ይህ በአል ነው የቂጣ ባእል የተባለው የሆነ ሆኖ ይህን በአል ተያይዞ የማርቆስ ወንጌል ፀሀፊ እና የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ የፃፉትን ታሪክ ለ እየቅል በለው ፡፡ ቀጣዩም ጥያቄ እንዴት ? የሚል ሲሆን በሚከተለው መልኩ ይቀርባል፡፡ እንደ አይሁዶች ቀን አቆጣጠር መሰረት አዲስ ቀን ሚጀምረው በመሸ ጊዜ ነው (በዚህም ወሳኝ ምክንያት ነው አይሁዶች ሰንበትን ቀን አርብ ማታ ማክበር ሚጀምሩት) ፡፡ በመሆኑም የቂጣ በአል ምግብ ሚዘጋጀው ቀን ሲሆን ሚበላው ደግሞ ማታ ነው አዲሱ ቀን ሲጀምር…… ይህ እውነታ ወደ እየሱስ ስቀለት ታሪክ ይመልሰናል እንደ ማርቆስ ወንጌል 14፡ 12 ደቀመዛሙርቱ እየሱስ ጋር ይመጡና የፋሲካ ምግብ እንዲዘጋጅለት እየሱስን ይጠይቁታል፡፡ እየሱስም ይፈቅድላቸው(14፡14-17) እና ምግቡን ያዘጋጃሉ፡፡ እንደ መሸም አዲስ ቀን ስለሚገባ በአሉን አብረው ማክበር ይጀምራሉ መመገብም ይጀምራሉ፡፡ (14፡22-24). ከዚህ በኋላ ጌቴሴማኒ ወደ ተባለ ቦታ ሄዱ እዛም ሶስቴ ፀልዮ እንዳበቃ ወደ ፈተና ይገባል፡፡ ማታውን ታስሮ ያነጋል(14፡53-72) ፡፡ ከፈተናዎችም በኋላ እየሱስ በጊዜው ፀረ ሽብር ህግ ተወንጅሎ(የአይሁድ ንጉስ ነኝ ብለሃል ተብሎ) በንጋታው 3፡00 ጧት ይሰቀላል፡፡ ይህ የማርቆስ ወንጌሉ እየሱስ ሲሆን የዮሐንስ ወንጌሉ እየሱስ ደግሞ ዮሐ 19፡14 በሚከተለው መልኩ ሰፍሯል፡፡ ቀኑ የፋሲካ በአል መዘጋጃ ጊዜውም ከቀኑ ስድስት ሰአት ያህል ነበር ፡፡ጲላጦስም አይሁድን እነሆ ንጉሳችሁ አላቸው እነሱም አስወግደው አስወግደው ስቀለው እያሉ ጮሁ ፡፡ጲላጦስም ንጉሳችሁን ልስቀለው አለ ፡፡ የካሃናት አለቆችም ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉስ የለንም ብለው መለሱለት በመጨረሻም ጲላጦስ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው(19፡14-16) ተመልከት በማርቆስ ወንጌል መሰረት እየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የፋሲካን በአል እንዲያዘጋጁ አዟቸው ሲያበቃ ቀኑን አዘጋጅተው ማታውን አብረው አሳልፈዋል፡፡ ማለትም በፋሲካ በአል በዘጋጃ ወቅት እየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብሮ ነበር ፡፡ ሲመሽም የፋሲካን ወይም የቂጣን በአል አብሮ አሳልፏል ለሊት ከፀለየ በኋላ ነው የተያዘው ፡፡ ሲነጋም ተሰቀለ፡፡ በጥሞና ካነበብከው እንደ ዮሐንስ ወንጌል ዘገባ እየሱስ የተሰቀለው ማርቆስ ወንጌል በዘገበው ቀን አይደለም፡፡ ዮሐንስ 18፡28 ምሳሌ ይሰጠናል ለምን አይሁድ ወደ ጲላጦስ ቤት እንዳልገቡ፡፡ ምክንያቱም ፋሲጋንመብላት እንዲችሉ ቀኑን ለለማርከስ ነበር፡፡ (በማርቆስነ ወንጌል ዘገባ መሰረት እነዚህ ሰዎች ፋሲጋን በልተው ነበር እየሱስ ላይ ሲወነጅሉ የታዩት)፡፡ እናስ? እናማ እደ ዮሐንስ ወንጌል ዘገባ መሰረት እየሱስ ደቀመዝሙሩን ፋሲካን እንዲያዘጋጁ አላዘዛቸውም ሲደመር ፋሲካን አብሮ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አልበላም፡፡ ይህ ደሜ ነው ይህ ስጋዬ ነው ሲል የተቆረሰን ቂጣ አልሰጣቸውም፡፡ እንደ ዮሐንስ ወንጌል ቂጣው በሚበላበት ሰአት እየሱስ ቀብር ውስጥ ነበር፡፡ እንደ ማርቆስ ወንጌል ግን እየሱስ አብሮ ቂጣ በልቶ ነበር፡፡ በመሆኑም የማርቆስ ወንጌሉ ፀሀፊ እና የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ የፃፉት የተለያዩ እየሱሶችን ታሪክ ነው ማለት ነው፡፡ ፀሀፊዎቹ ይህን ያፃፋቸው መንፈስ ቅዱስ ነው የሚለኝ ቀላጅ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም ቸርች አደለም ያለነው ጥናት ላይ ነን፡፡ ወደ ኢልመል ሪጃል ሳይንስ ስመልስህ ሁለቱም ፀሀፊዎች ተቀባይነት የላቸውም ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስም ይሁን በምናምን የተያየ ታሪክ ዘግበዋል፡፡ ከሁለት አንዱም ውሸታም ነው፡፡ እና ከሰነድ አኳያ ብቻ ሳይሆን ከዘጋቢዎቹ ማንነት አንፃር ዘገባው መውዱእ ነው፡፡ ……………. ይቀጥላል የሆነ ሆኖ እኛ ሙስሊሞች አንድን ዘገባ ስለፈለግነው ወይም ስላልፈለግነው አይደለም ዶኢፍ ወይም መውዱእ ምንለው በደመነፍስ መንፈስ ቅዱስም ተገለፀልን በሚል ( የማይዋጥ) ሽፋን አደለም ፡፡ አንድን ታሪክ ምንቀበለው ፕሮፌሽናል በሆነው የሀዲስ ሳይንስ ነው፡፡ ይህ መሆኑ ሲገባው እና መፅሀፍ ቅዱስ ከዚህ ሳይንስ አኳያ ቢፈተሸ መውዱእ መሆኑን በመረዳቱ ካዝ ቢያለቅስ አእምሮውን ካለማሰራቱ የመነጨ ከመሆን የዘለለ ትርጉም የለውም!!!1 W Montgomery Watt ምን ነበር ያልከው? it would have been easy to invent sayings of Muhammad. Because the cultural background of the Arabs had been oral the evidence that came to be expected was the chain of names of those who had passed on the anecdote containing the saying . . . The study of Traditions rapidly became a distinct branch of the studies of the general religious movement. It was soon realized that false Traditions were in circulation with sayings that Muhammad could not possibly have uttered. The chains of transmitters were therefore carefully scrutinised to make sure that the persons named could in fact have met one another, that they could be trusted to repeat the story accurately, and that they did not hold any heretical views. This implied extensive biographical studies; and many biographical dictionaries have been preserved giving the basic information about a mans teachers and pupils, the views of later scholars (on his reliability as a transmitter) and the date of his death. This biography-based critique of Traditions helped considerably to form a more or less common mind among many men throughout the caliphate about what was to be accepted and what rejected.. Reference sources 1. Bernard Lewis, Islam In History, 1993, Open Court Publishing, pp.104-105. 2. W Montgomery Watt, What Is Islam?, 1968, Longman, Green and Co. Ltd., pp. 124-125. 3. Henry Malter, Saadia Gaon: His Life And Works, 1921, The Jewish Publication Society of America, Philadelphia, pp. 39-40. 4. Alfred Guillaume, The Legacy Of Islam, 1931, Oxford, p. ix. 5. The Gospel of Philiph 63. 32-64.5, In Nag-Hammadi library,New York, 1977, p. 138 6. የቁርአን እና የመፅሀፍ ቅዱስ አጠባበቅ ክፍል - 3፣ ቃልአሚን ኢበነልኢስላም 7. Suhaib Hasan, An Introduction To The Science Of Hadîth, 1995, Darussalam Publishers, Riyadh, Saudi Arabia, p. 11. 8. Ibid 9. Sahih Al Bukhari h.no. 1 10. The New Encyclopedia Britannica vol 14 pp826 11. The New Encyclopedia Britannica vol 14 pp 827 12. The New Encyclopedia Britannica vol 14 pp 824 13. The New Encyclopedia Britannica vol 14 pp 828 14. The Orthodox Corruption of Scripture, Bart Ehrman, pp. 27 15. Sunan Ibn Majah, Hadith 1944 16. Shaykh Muhammad Taqi Usmani in Takmala Fath Al-Mulhim 1/69 pub. Darul Ahya Al-Turath Al-Arabi, Beirut. 17. Shakh shu’aib ,Clasification of musnad pp. 441 , Al risala publisher, Beirut
Posted on: Sat, 13 Sep 2014 12:08:10 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015