ኢሳያስ አፈወሪቂ ለእረፍት ወደ - TopicsExpress



          

ኢሳያስ አፈወሪቂ ለእረፍት ወደ ፖርትሱዳን አርከዊት ሪዞልት ሆቴል ይበራሉ:: አሜሪካ በኤርትራ የመንግስት ለውጥ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች ነው:: #Eritrea #Ethiopia #PFDJ #TPLF አሜሪካ የአቶ ኢሳያስ አፍወርቂን መታመም ተከትሎ ዜጎቿን የፖለቲካ ችግሮች በኤርትራ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ወደ ሃገሪቱ እንዳይገቡ ካስጠነቀቀች በኋላ እና አስመራ እና አከባቢው ላይ ያሉም በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መናገሯን ተከትሎ በአስመራ የመንግስት ለውጥ እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የደህንነት መዋቅር ሰዎች በኢትዮጵያ በሱዳን እና በእርትራ መታየታቸው ለዚሁ ጉዳይ መጠናከሪያ ሆኗል:: ኢሳያስ አፈወርቂ ለማገገም በነገው እለት ፖርት ሱዳን ወደሚገኘው ሲንካት ከተማ አቅራቢያ በአርከዊት ሪዞልት ሆቴል የእረፍት ጊዜ እንዲያሳልፉ አልበሽር አስፈላጊውን እንዳዘጋጁላቸው ምንጮች ተናግረዋል::አቶ ኢሳያስ የጤንነታቸው ጉአይ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱ ያሳሰበው የሻእቢያ ቡድን በስልጣን ሽኩቻ እየጦዘ ሲሆን የራሳቸው እያረረባቸው የሰው የሚያማስለው የወያኔው ጁንታ አናቶች የተለያዩ የኤርትራ ባለስልጣናትን እና ዲፕሎማቶችን በመንግስት ለውጡ ዙሪያ በስልክ እና በግንባር እያነጋገረ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::#Minilik_Salsawi
Posted on: Sat, 23 Nov 2013 13:23:21 +0000

Recently Viewed Topics




© 2015