ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን - TopicsExpress



          

ኢትዬጲያዊያን ሙስሊሞች አሁን በሃገራችን ያለንበት ተጨባጭ ይህን ይመስላል:: ይህን ለማስተካከል ባለመቻላችን አላህ ፊት ምን ይሆን ምላሻችን??? 1.በሃገሪቱ ብቸኛ የሙስሊሞች ወካይ አካል የኢትዬጲያ እስልምና ጉዳዬች ጠ/ምክር ቤት ወይም መጅሊስ በትክክለኛ ሙስሊሞች መመራት ካቆመ አስርት አመታትን አስቆጠረ፡፡ 2.የሙስሊሙ መሪ ይመረጥ ሲባል ለመንግስት ባላቸው ታማኝነት በቀበሌ ግለሰቦች እንዲመረጡ ተደረገ 3.በኢትዬጲያ ብቸኛው ሁሉን አቀፍ ተቋም የሆነው አወልያ በመንግስት አስገዳጅነት ከሙስሊሙ ተነጥቆ ለህገ ወጡ መጅሊስ እንዲሰጥ ተደረገ 4.በአወልያ ሲረዱ እና ሲማሩ የነበሩ የቲሞች እና የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎች ከግቢው ተባረው መና ቀሩ 5.በመላው ሃገሪቱ የነበሩ የተለያዩ ኢስላማዊ ድርጅቶች እና ማህበራት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲዘጉ ተደረገ፡፡ 6.መንግስት እኔ ትክክለኛውን ኢስላም አውቅላቹሃለው በማለት አህባሽ የተባለውን አንጃ ካልተቀበላችሁ ተብለን ተገደድን 7.አህባሽ ቀድሞ የነበረ ቢሆንም በግዳጅ አቂዳችንን እንዲበርዝ ሽርክ እና ቢድአን እንዲያስፋፋ ድጋፍ እየተደረገለት ነው 8.አባቶቻችን ብዙ ደማቸውን አፍስሰው በመስዋትነት የገነቡትን መስጂዶቻችንን በመንግስት አስገዳጅነት ከሙስሊሙ በመንጠቅ ለአህባሽ መራሹ መጅሊስ አሳልፎ እየተሰጠብን ነው፡፡የመስጂዱን የስልጣን ጉዳይ ሳይሆን መስጂዱን ከተረከቡት ቡሃላ ብልሹ የሆነውን አቂዳቸውን እና የጥመት አስተምህሯቸውን በመስጂዳችን በነፃት ለማስተማር መብቃታቸው አይቀሬ ነው 9.በመስጂዶቻችን ለረጅም አመታት በኢማምነት ሲመሩን የነበሩትን ኡለሞቻችንን እና መሻይኮቻችን በኩፍር እና በቢድአ በተጨማለቁ የአህባሽ እምነት አራማጅ ግለሰቦች በመንግስት እንዲተኩ ተደረገ፡፡ እየተደረገም ነው፡፡ 10.በአህባሽ እና በቢድአ አራማጆች ተከትለን አንሰግድም በሚል ሁለተኛ ጀምአ ለመስገድ ሲሞከር በመንግስት ሁለተኛ ጀምአ መስገድ ሃራም ተደርጎ ሙስሊሞች እየታሰሩ ነው፡፡ 11.በመስጂዶቻችን የዳዕዋ እና ኢስላማዊ ትምህርቶችን እንዳንማማር ተከለከልን 12.ዳኢዎች እስልምናን ለማስተማር ከፈለጉ ከአህበሽ መራሹ መጅሊስ መታወቂያ ካላወጡ በየትኛውም መስጂድም ሆነ ቦታ ማስተማር አይችሉም ተባለ 13.ማንኛውም ኢስላማዊ ትምህርት በመፅሃፍም ሆነ በኦዲዬቪዋል ለማሳተም ከተፈለገ የአህባሻዊ መጅሊሶችን ፈቃድ እና ይሁንታ ማግኘት አለበት ተባለ 14.ሁሉም ኢስላማዊ የህትመት ውጤቶች የሆኑ ጋዜጦች እና መፅሄቶች በሃገራችን እርም ተደረጉ 15.በመላው ሃገሪቱ ታላላቅ ቂርአት ቦታዎች እና ዛውያዎች በመንግስት እንዲዘጉ እና እንዲፈርሱ ተደረጉ 16.በሺዎች የሚቆጠሩ ደረሶች ከሚቀሩባቸው የቂርአት ቦታዎች ኡስታዛቸውን ለአልሸባብ ወጣት እየመለመልክ ነው በሚል እንዲታሰሩ ተደርጎ ደረሶቹንም እንዱበተኑ እና ወደ ሃገራቸው እንዲሄዱ በታጣቂዎች ተደርጓል 17.በሃገሪቱ የሚገኙ ኢስላማዊ መድረሳዎች እንዲታሸጉ ተደረገ ህፃናት በልጅነታቸው ቁርአን የሚቀሩ ከሆነ ሲያድጉ አክራሪነት ስለሚጠናወታቸው ከ 18 አመት በታች ቁርአን እንዳይቀሩ ይደረግ ተባለ 18.በየመስጂዱ የነበሩ ኢስላማዊ ቤተ መፅሃፍቶች እንዲታሸጉ አልያም በውስጣቸው ያሉ የተውሂድ ኪታቦች እንዲሁም በስም በሚታወቁ ታላላቅ ኡለሞች የተፃፉ መፅሃፍቶችን የዋሃቢያ ናቸው በሚል እንዲቃጠሉ እና እንዲወገዱ ተደረገ 19.ፂም ማሳደግ እና ሱሪ ማሳጠር የነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና መሆኑ እየታወቀ የአክራሪዎች እና የአሸባሪዎች ነው በሚል እየታሰርን፣ እየተደበደብን እና እየተሰቃየን እንገኛለን 20.ሙስሊም ተማሪዎች አላህ (ሱ.ወ) ግዴታ ያደረገባቸውን የግዴታ ሰላት በጀምአ እንዳይሰግዱ ተከለከሉ፡፡ 21. ሙስሊም ሴት እህቶቻችን በት/ቤቶች እና በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሂጃባቸውን ካላወለቁ መማር እንደማይችሉ ተነገራቸው፡፡ በየቦታው ሂጃባቸውን በመጠበቃቸው ብቻ እያመናጨቁዋቸው፣ሂጃባቸውን እየገፈፉ አንቺ የአረብ አመንዛሪ እየተባሉ እየተሰደቡ እና እየተዋረዱ ይገኛሉ 22.በመስጂድ ውስጥም ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ቂርአት ተሰብስቦ መቅራት በተለያዩ ቦታዎች ተከለከለ፡፡ 23.በመላው ሃገሪቱ ለኢስላም ብዙ ሲለፉ እና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ኡለሞች፣ኡስታዞች እና ወንድሞች በየእስር ቤቱ በአሸባሪ የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸው ወህኒ ወረዱ 24.በመስጂዶቻችን ወታደሮች ከነጫማቸው በመግባት መስጂዳችንን በማርከስ በሙስሊሞች ደም አጨቀዩት 25.ኢስላማዊ የሰደቃ እና የዳዕዋ ዝግጅቶች ሃራም ናቸው በሚል በመንግስት እንዲታገዱ ተደረገ 26.ኢስላማዊ ትምህርቶችን መስጫ ፓምፍሌቶችን ማሰራራጨትም ሆነ መበተን ሽብር ነው በሚል ተከለከለ 27.በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ስራውን የፈለገ ስራውን ይስራ ያልፈለገ ደግሞ ስራውን ይልቀቅ በሚል ሰላት እንዲያቆሙ አልያም ማታ ቤታቸው ሲገቡ ሰብስበው እንዲሰግዱ፣ኢስላማዊ መገለጫዎችን ፂም ማሳደግ እና አለባበሳቸውንም ኢስላማዊ ማድረግ ክልክል በጥብቅ ተከለከሉ 28. ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ ስርአት እንዳይኖረን ተደረግን፡፡ 29.ይህ ሁሉ በደል ሲደረስ ለምን ብሎ የጠየቀ በሙሉ አሸባሪ በሚል በየእስር ቤቱ እና በየወህኒ ቤቱ እንዲሰቃዩ ተደረገ:: 30.በሁሉም ከተማ ላይ ያሉ እስር ቤቶች ቢፈተሹ ሙስሊምብቻ በመሆናቸው ተወንጅለው በታሰሩ ንፁን ተሞልተው ይገኛሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት በኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ከሚገኘው በደል እና ግፍ በጥቂቱ ሲሆን ይህ ሁላ በደል እና ግፍ ሲፈጸም እየተመለከትን ግን ምንም ማድረግ አለመቻላችን ልብ ይሰብራል፡፡ አንድን መጥፎ ነገር የተመለከተ በእጁ ለማስቆም ይሞክር እልያም በምላሱ በመናገር ለማስቆም ይሞክር አልያም ያንን ድርጊት በልቡ ይጥላው፡፡ ይህ በልብ ብቻ መጥላቱ ግን ደካማ ኢማን መሆኑን ነብዩ(ሰ.ዐ›ወ) በሃዲሳቸው አስተምረውናል፡፡ እስልምና በሂወት እያለን ይህ ሁላ ሲደፈር ማየት ምነኛ ሞት ነው ፡፡ ቀደምት ሰሃቦች ይህን ጉድ ቢያዩ ምን ይሉ ነበር????? አላህ በወንጀላችን አይፈትንን፡፡ በሃይማኖታችን ላይም የማንችለውን ፈተና አያሸክመን፡ በጠላቶቻችንም ላይ ድልም እንድንቀናጅ ሁልጊዜም እርዳታው አይለየን!!! አሚን!! #ABU DAWD OSMAN
Posted on: Thu, 14 Nov 2013 17:31:57 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015