ኢትዮጵያ ግን የማን ናት? ሰሞኑን ቢቢሲ - TopicsExpress



          

ኢትዮጵያ ግን የማን ናት? ሰሞኑን ቢቢሲ እንዴት ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በየመን እና ሳውድ አረቢያ በስደት በየበረሃዉ እንደሚንገላቱ፣እንድሚደፈሩ፣በእሳት እንደሚጠበሱ፣ እንደሚገደሉ፣ እንደቃ እንደሚሸጡ ሲከፋም እንደሚሞቱ አንድ ዶክመንታር አቅርቦ ነበር፤ በሌላ በኩል የኛዉ ኢቲቪ ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲወች በኢትዮጵያ መንግስት 75 ከመቶ ወጭ ተሸፍኖላቸው በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ስለተመረቁ ዔርትራዉያን ተማሪወች ዜና በማሳየት ተጠምዶ ሰንብቷል፤ እኛ እራሳችን እኮ የወጭ መጋራት (cost sharing) ከፍለን ነው የምንማረው :: መመረቁንስ ይመረቁ ሥራ ላይስ እንዴት ነው ኢትዮጵያዉያን ተመርቀው ሥራ አጥተው ከሀገር እንዲሰደዱ እና ኮብል ድንጋይ እንዲጠርቡ እየተደረገ ለዔርትራዉያኑ ቅድሚያ ይሰጣል ወይ? ነገሩ መጀመሪያም የደህንነት መስሪያ ቤቱ ነበር ሲንከባከባቸው የከረመው መቸም ከዛው ሰፈር ለሥራ ሳይፈልጋቸው የቀረ አይመስለኝም :: ወይ አንች ሀገር !!! እህህ ነው እንጅ ሌላ ምን ይባላል? ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች እማ ነጥብ አልመጣላችሁም እየተባሉ ከ 10 ኛ ክፍል ያቁአርጡ፣ለስደት እና ለመከራም ይዳረጉ፣ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀዉም ድንጋይ ይጥረቡ ዔርትራዉያኑ ደግሞ በኛዉ ገንዘብ በኛዉ ዩኒቨርስቲ ተምረው እኛዉ እራሳችን ይሰልሉን:: በኛዉ ገንዘብ፣ በኛዉ መሃንዲስ በኛዉ ቅብጥርሴ ምናምን አይደል ባለራዩስ አባይ ይገደባል ሲሉን የነበረው? የኢትዮጵያ ህዝብም እንደዛው ይገደባል:: እማማ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ማን ነበር እንደዚህ ያለው? ለማንኛዉም የኢቲቪን ዜና እና የቢቢሲን ዶክመንታሪ ከስር ይመልከቱ:: youtube/watch?v=1lUSrWHHCw4 ethiotube.net/video/26954/Must-Watch-BBC-News--Ethiopian-migrants-tell-of-torture-and-rape-in-Yemen--July-2013
Posted on: Wed, 24 Jul 2013 05:36:18 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015