ኢትዮጵያና ኤርትራ በሱዳን በኩል - TopicsExpress



          

ኢትዮጵያና ኤርትራ በሱዳን በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር እያካሄዱ እንዳሉ ተሰማ፡፡ Sudan mediating indirect talks between Ethiopia and Eritrea | ኢትዮጵያና ኤርትራ በሱዳን በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር እያካሄዱ እንዳሉ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሽር ሀሙስ ዕለት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጋር በመሆን መግለጻቸው ተሰማ፡፡ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አንዳንድ ጥረቶች እያደረግን ነው” ያሉት አልበሽር፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበሩ ጉዳይ፣ በእጅ አዙር በሚያደርጉት ግጭት (Proxy war) ዙሪያና በሌሎችም ተዛማች ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ ለማስቻል ህቡዕ የሆን የሶስተኛ ወገን ድርድር በሱዳን በኩል እንደጀመሩ ገልጸዋል፡፡ “ሱዳን ከሁለቱም ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን ከዚህ ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር በተጨማሪ በቅርቡ የሁለቱንም ሀገራት መሪዎች ካርቱም ላይ ጠርተን እንዲወያዩ እናደርጋለን” ሲሉ አልበሽር መናገራቸውም ታውቋል፡፡ Sudan mediating indirect talks between Ethiopia and Eritrea – DireTube Latest Ethiopian News diretube Ethiopia and Eritrea are in secret talks mediated by Khartoum with a view to end the historic conflict between the two nations.Sudan’s President Omar al-Bashir revealed Thursday that he had initiated indirect talks between the
Posted on: Mon, 09 Dec 2013 16:15:15 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015