ኢትዮጵያዊው የጎዳና ተዳዳሪ በአሜሪካ - TopicsExpress



          

ኢትዮጵያዊው የጎዳና ተዳዳሪ በአሜሪካ የተሳካለት ኳስ ተጨዋች ሆነ በጎዳና ህይወት አሰቃቂ ገጽታን ችሎ ለብዙ ዓመታት የኖረው ኢትዮጵያዊ ግርማ በማደጎ ወደ አሜሪካ ተጉዞ ታዋቂ የኳስ ተጨዋች ሆነ፡፡ ቤተሰቡንም ሆነ ስሙን የማያውቀው ግርማ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት የጎዳና ህይወትን የሙጥኝ በማለት ከለጋ ዕድሜው ጀምሮ ህይውቱን ለማቆየት መትጋት ጀመረ፡፡ ግርማ በጎዳና ላይ በሚሰራቸው ስራዎች የሚያገኘውን ገቢ የዕለት ጉርሱን ከመሸፈን ጎን ለጎን ለትምህርት በመጠቀም እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ ለመማር ችሏል፡፡ ቤንጃሚንና ቤተሰቦቹ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ግርማን በማደጎ ልጅነት ወደ አሜሪካ ይዘውት ተጓዙ፡፡ አሁን ግርማ በሚማርበት ኮንቬናንት ትምህርት ቤት በሚገኝ የእግር ኳስ ክለብ ኮከብ ተጨዋች ሆኗል፡፡ ግርማ ወደፊት ትልቅ ተጨዋች ሆኖ በሀገሩ የሚገኙ ጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመርዳት ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል፡፡ ኤን ቢሲ 29 እንዳስነበበው፡፡ የግርማን ቪድዮ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ source ERTA
Posted on: Fri, 27 Sep 2013 10:31:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015