ኢናሊላሂ ወዒና ኢለይና ራጂኡን በኮፈሌ - TopicsExpress



          

ኢናሊላሂ ወዒና ኢለይና ራጂኡን በኮፈሌ ከተማ በቶቶላም አካባቢ የተገደሉት ሙስሊሞች ቁጥር ከ6 በላይ ማሻቀቡ ተሰማ:; በምዕራብ አርሲ በኮፈሌ ከተማ ልዩ ስሙ ቶተላሞ አካባቢ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ መንግሰት ሆን ብሎ በፈፀመው ትንኮሳ በተፈጠረ አለመግባባት ቀድሞውንም በአካባቢው ሁከት በመፍጠር ለግድያ የተዘጋጁት የፌደራል ፖሊሶች በከተማው ሙስሊሞች ላይ ጥይት በመተኮስ አስካሁን ባለው መረጃ ከ6 ሙስሊሞች በላይ መገደላቸው ተሰምቷል፡፤ ከተገደሉት ውስጥ አንድ ትልቅ ሼህ እና አንድ ህፃን ልጅ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን የተቀሩት 4ቱ ወጣቶች መሆናቸው ተዘግቧል፡፤ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ የተፈጠረው አለመግባባት ህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ትንኮሳውን ለማክሸፍ እየሞከረ ቢገንም የመንግስት ወታደሮች ግን በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ንፁሃን ሙስሊሞችን በጥይት እያረገፉ ይገኛሉ፡፤ በተፈጠረው ችግርም አስካሁን ከ 100 በላይ ሙስሊሞች መታሰራቸው ተዘግቧል፡፤ መንግስት ሃሙስ ማታ የሃይል እርምጃ እንደሚወስድ በሰተው መግለጫ መሰረት በመላው ሃገሪቱ ህዝበ ሙስሊሙን በአስር እና ድብደባ እያሸበረ ሲሆን እነሆ በኮፈሌ ከተማም ንፁሃን ሙስሊሞችን በጥይት አርግፏል፡፤ የተፈጠራ አለመግባባበትም የተገደሉት ሰዎች አስክሬን ወደ ሻሸመኔ ጀነራል ሆስፒታል መወሰዱን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ የተገደሉትን ንፁህን ሙስሊሞችም አላህ የሸሂድነትን ማዕረግ ያጎናፅፋቸው!!! ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!! አላሁ አከበር!!! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ for more information like this page https://facebook/abudawdosman
Posted on: Sat, 03 Aug 2013 16:49:08 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015