ኢድ ነው ብዬ BY Malcolm king (M.K.) ግማሽ ሃዘን - TopicsExpress



          

ኢድ ነው ብዬ BY Malcolm king (M.K.) ግማሽ ሃዘን ግማሽ ደስታ፤ ቀኑ እንዳያልፍ በእርጋታ፤ በኣሩሲ በኮፈሌ እናት ስታለቅስ ተደፍታ፤ በዛች ቅጥፈት በዛች ፋታ፤ ሙስሊሞች ላይ ስበው ቃታ፤ በኣቡጀዲ ተሸፍኖ ጀናዛውን ሳይ በተርታ፤ አይኔ ኣልቅሶ ኣፍንጫዬ በተመታ፤ ተቸግራ ኣሳድጋ ወላጅ ለፍታ፤ ህጻን ልጇን ሳጠግብ ኣይታ፤ ሚስት ከባሏ ለዘላለም ተለይታ፤ ደም በጠማው የቀን ሸፍታ፤ ሃዘን በዝቶ ነግሶ ዋይታ፤ እቤቴ ወስጥ ደምቆ ፌሽታ፤ ኢድ ነው ብዬ እንዴት ላክብር፤ ሙስሊሙ ህዝብ ኣጥቶ ክብር፤ ኣሸባሪ በሚል ፈሊጥ ሙሉ ኣገሩ ሲሸበር፤ እንደኣውሬ በመታደን በየማረሚያ ሲታጎር፤ ቀን ከሌሊት በኤሌክትሪክ ሲሆን ቶርቸር፤ ኣፉ ደርቆ በውሃ ጥም ሲኮማተር፤ ጾሞ ውሎ በሰኣቱ እንዳያፈጥር፤ ኣይኑ ታስሮ በጨለማ ሲደናበር፤ እኔ ቤቴ ተቀምጬ ምንም ሳላፍር፤ ኢድ ነው ብዬ እንዴት ላክብር፤ ግማሽ ጎኔ ሰላም ሆኖ ሌላኛው ጎኔ ሲታሰር፤ ግማሽ ልቤ ተደስቶ ቀሪው በቁጭት ሲሻክር፤ ግማሽ ፊቴ ፈካ ብሎ ሌላው በሃዘን ሲጠቁር፤ ግማሽ ጉንጬ ሞላ ብሎ ቀሪው በእንባ ሲሸረሸር፤ በኣጠቃላይ የግፍ ቀንበር ከሙስሊሙ ላይ እስኪባረር፤ ሃዘን ላይ ነኝ ፍትህ ጠፍቶ በዚች ምድር፤ ሙሉ ደስታ ኣላገኝም ሙሉ መብቴ እስኪከበር።
Posted on: Wed, 07 Aug 2013 20:50:41 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015