እውን ዩኒቨርሲትዎቻችን ከፖለቲካና ከ - TopicsExpress



          

እውን ዩኒቨርሲትዎቻችን ከፖለቲካና ከ ሀይማኖት የጸዱ ናቸው? By; Ih Raj መንግስት ላለፉት ዓመታት በሀገሪቱ ውስጥ እያቆጠቆጠ የመጣውን የዳዕዋ እንቅስቃሴ ለመግታት የተለያዩ ስልቶችን ሲቀይስ ከርሟል። ከነዚህም ውስጥ ሀገሪቱን እያተራመሰ የሚገኝበትን የአህባሽ አስተምህሮ ከሊባኖስ በማስመጣት የኢስላማዊ ተቋማት ነጠቃን እያጧጧፈ ቢሆንም የነገ የሀገር ተረካቢዎችና የለውጥ ሃዋሪያ የሆኑ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግን በጣም ዘግናኝና ጉዳቱም እጅግ የከፋ ነው። መንግስት ወቀሳውን ከሚያቀርብባቸው ነገሮች ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ማራመጃ መድረክና የእምነት ተቋማት እየሆኑ ነው የሚለው ይገኝበታል። በመሰረቱ ስርዓቱ እንጂ ተማሪው ወይም አስተማሪው የግድ secular መሆን ስለማይጠበቅባቸው የመማር ማስተማሩን ሂደት ሳያውኩና የሌላውን መብት ሳይጋፉ የእምነቶቻቸውን ድንጋጌዎች ቢተገብሩ በኔ እይታ ችግር ያለው አይመስለኝም። ከወረቀት ያልዘለለው ህገ መንግስትም ይሄንን የማድረግ ሙሉ መብት ሰቷቸዋልና። በዛሬው ጽሁፌ ስለ መብት ጉዳይ ልሟገት ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎቻችንን ወደ ፖለቲካ መድረክነት የቀየራቸውና የዕምነት ተቋም ያደረጋቸው ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ፈልጌ ነው። እስቲ እራሴ በምማርበት ዩኒቨርሲቲ የታዘብኩትን ነገር ላስቃኝችሁና ፍርዱን ለናንተ ልተው። Ih Raj ነኝ ትንሽ ጊዜ ሰታችሁ አንብቡት ከተሳሳትኩም አርሙኝ!! እኔ በምማርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መምህር፤ተማሪ ወይም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርም ሆነ አጋዥ ሰራተኛ ያልሆኑ አራት ሰዎችን በግቢው ውስጥ በየቦታው ማለትም (የተማሪዎች ስብሰባ ላይ፡ ካፌ አካባቢ፡ የበዓላት ቀን ወዘተ) ማየት የተለመደ የዕለት ተዕለት ተግባር ነው። እነዚህ አራት ሰዎች አደራጆች በመባል የሚታወቁ ሲሆን አውራው ፓርቲ ያቀፋቸውን አራት ድርጅቶች (ህወሃት፡ ብአዴን፡ ኦህዴድ፡ ደኢህዴን) ይወክላሉ። የነዚህ ሰዎች ስራ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መከታተል፡ ለአባልነት መመልመልና መዋጮ ማሰባሰብንም ያጠቃልላል። የዩኒቨርሲቲው የሴኔት ስብሰባ ላይ ሳይቀር ተሳታፊዎች ናቸው። ዩኒቨርሲቲው የሞባይል ካርድ ከመሙላት ጀምሮ የትራንስፖርት ወጪያቸውንም ይሸፍናል። ስልጣናቸው ገደብ የለውም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውስጥም በመግባት ውሳኔዎችን ያጸድቃሉ ሲያሻቸውም ይሽራሉ........... ታዲያ እነዚህን ካድሬዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ በማምጣት በስልጣን ያንበሸበሻቸው ሙስሊሙ ነው እንዴ?? የመማር ማስተማር ሂደቱን በተመለከተ የታዘብኩትን በቀጣይ ጽሁፌ አካፍላችኋለሁ። ድል ለዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!!!
Posted on: Tue, 29 Oct 2013 15:59:46 +0000

Trending Topics



770899">PSALM 23 IN PIDGIN ENGLISH 1. The Lord na mai Shepherd, I dey
Pain Relief is just one of the most noticeable benefits you will

Recently Viewed Topics




© 2015