የማይደርስ የለ........ የባህር ዳር - TopicsExpress



          

የማይደርስ የለ........ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ባህር ዳር ዪኒቨርሲቲን ፣ ትምህርት ሚኒስቴርን እና የባህር ዳር ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመክሰስ ለሀምሌ 2/2005 መቀጠራቸው የሚታወስ ነው ሰላት በጀምዓም ሆነ በግል አቁሙ ፤ ሂጃብ/ኒቃብ አውሉቁ ተብለው ይህም አልበቃ ብሎ ከፍተኛ ግፍ እና በደል የተፈጸመባቸው ውድ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተለያዩ ሰላማዊ የመደራደሪያ ሃሳቦችን በመያዝ ሚመለከታቸውን አካላት ሁሉ ቢያናግሩም አትጋቢ መላሽ ማግኝት ይቅር እና ቅንጣት ታክል ትኩረት ሊሰጧቸው ያለፈቀዱትን አካላት ለመክሰስ ተገደዋል። የሀገር ተረካቢ የሆኑትን ተማሪዎች ችግር አዳምቶ ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳነት ‘’........ሰላትም ሆነ ሂጃብ የኔ ጉዳይ አይደለም......... ሀይማኖቴን ያለ ወደ ቤቱ መሄድ ይችላል...... ሀይማኖታችሁን እቤታችሁ ስትሄዱ ትደርሱበታላችሁ....’’ ሲል የተማሪዎችን ቅስም የሚሰብር ነግግር ተናገረ። ተማሪዎቹም ‘’.......የቅርቢቱም ሕይወት ጥቅም በመጨረሻይቱ (አንጻር) ጥቂት እንጂ አይደለም።' የሚለውን የአላህን ቃል በማስታወስ ዲኔን/ሀይማኖቴን በለው ጓዛቸውን ይዘው ከ12 ዓመት በላይ የለፉበትን ትምህርታቸውን ጥለውት ወጡ። እነዚህ መብታችውን እና ግዴታችውን ጠንቅቀው የሚያውቁት ውድ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወጥትው ቁጭ አላሉም፤ ጉዳያቸውን ይዘው ወድ ትምህርት ሚኒስትር፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር፤ አስታራቂ የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ሳይቀር ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ለዲናቸው፤ ለመብታቸው ላይ እታች ይሉ ጅመር። ተማሪዎቹ መፍቴ እናገኛለን ብለው የጎብኟቸው የመንግስት አካላት (ትምህርት ሚኒስትር እና የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር) ከመፍትሄ ይልቅ አንዴ ስብሰባ ላይ ናቸው፡ አንዴ ለስራ ጉዳይ ወጥተዋል እያሉ እልህ አስጨራሽ በሆነ መልኩ ሲያንከራቱቷቸው ከቆዩ በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳነት ያልተለየ መልስ ሰጧቸው። ይህም ብቻ አይድለም በፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር ውስጥ ያናገራችውም አካል ፡ በባህር ዳር ዪኒቨርሲቲ እየተተገበረ ያለው ህገ-ደንብ ኢትዮጲያ ውስጥ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አረዷቸው ። የሃገር ሽማግሌዎችም ጋር ቢሄዱም እርቅ ሊያገኙ ያልቻሉት እነዚህ በሳል የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ይዘዉት ለመሄድ ተገደዱ፤ በጠበቆቻቸውም አማካኝነት ከባለፈው ጥር ወር ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ ምክንያት የሆነውን ህገ ደንብ እንዲሽሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ፣ ለባህር ዳር ዪኒቨርስቲና ለዪኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ደብዳቤ መላካቸውን አስታወቁ። የተማሪዎቹ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉና ዶክተር ያዕቆብ ሀይለማርያም ደብዳቤውን የላኩት ተማሪዎች በህብረት መስገድ እና በትምህርት ቤት ውስጥ ኒቃብ መልበስን የሚከለክለው ህገ ደንብ እንዲሻር በህግ ከመጠየቃቸው በፊት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነበር፡፡ እንግዲ ከዚህ ሁሉ ፈተና እና እንግልት በኋላ ነው የባህር ዳር ዩኒቨርሲትይ ሙስሊም ተማሪዎች በፍርድ ቤት ለፊታችን ማክሰኞ ሀምሌ 2/2005 እለት የተቀጠሩት። የማይደርስ የለ ሀምሌ 2/2005 ደርሰ! እኛም በመላው ኢቲዮጲያ የምንገኝ ሙስሊሞች ፤ በተለይም አብረን ካልቆምን የዚህ ህገ ደንብ ሰለባ መሆናችን የማይቀርል በየዩኒቨርስቲው የምንገኝ ሙስሊም ተማሪዎች ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን ጎን በዱዓ ፤ በሃሳብ ፤ እንዲሁም አሰፈላጊ ሆኖ በተገኝው ነገር ሁሉ ሙሉ ድጋፍ ለናደርግላቸው ገዴታችን መሆኑን ለናሳስብ እንወዳለን። “ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው።” (አት-ተውባ 9፤ 71) Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ፨ EMUS ፨ https://facebook/EthiopianMuslimUniversityStudentsEmus
Posted on: Sun, 07 Jul 2013 19:28:25 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015