የእናትነት ልክ የት ድረስ ነው? (አሌክስ - TopicsExpress



          

የእናትነት ልክ የት ድረስ ነው? (አሌክስ አብረሃም) ( እንደተረት ....የህዝብ ናት) ልጁ ሚስቱና ባልቴት እናቱ አልስማማ አሉት! ጭቅጭቃቸው መረረው እናም ክፉ ሚስቱ ጋር ተመካከረ እና ባልቴትና አይነስውር እናቱን ጫካ ሊጥላት ተስማማ!! እናቱን አንከብክቦ አዝሎ ጥቅጥቅ ወዳለ ጫካ ገባ.....ወደጫካው ውስጥ ሲሄድ እናት ልጇ ጀርባ ላይ ሁና ቅጠል እየበጠሰች በየመንገዱ ትጥላለች... በዚህ ሁኔታ እጅግ አስፈሪውና ማንም መመለስ የማይችልበት የጫካው ክፍል ጥሏት ተመለሰ !! ድንገት ከኋላቸው ተደብቆ ሁኔታውን እየተከተለ ሲመለከት የነበረ አዳኝ ወደተጣለችው እናት ቀረበና ‹‹ ልጅሽ ጥሎሽ ሄደ ሲያመጣሽ ከኋላችሁ ሁኘ አያችሁ ነበር ለምንድን ነበር ግን ቅጠል እየበጠሸ በየመንገዱ ስትጥይ የነበረው ?›› አላት እናት እንዲህ አለች ‹‹ልጄ እኔን ጥሎ ሲመለስ መንገዱ ጠፍቶበት አውሬ እንዳይበላብኝ ብየ ነው›› !!
Posted on: Thu, 25 Jul 2013 08:11:51 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015