የክፍል ስራ (አሌክስ አብረሃም ) አንዲት - TopicsExpress



          

የክፍል ስራ (አሌክስ አብረሃም ) አንዲት ጩጨ አለች እዚህ አፏን በደንብ ሳትፈታ ነገር የምታፍታታ ወቸ ጉድ .....የጠየቀችኝን ልጠይቃችሁ እስኪ ከ 10 የሚታረም ነው !! እደግመዋለሁ ይታረማል !! አንድ ከበደ የሚባል ሰውየ ሰራተኞቹን ‹‹ቤት ጥረጉ ›› አላቸውና ቁሞ ሲያስጠርግ በዛ የሚያልፍ ሰው ‹‹ጋሽ ከበደ ሰራተኞቹን ምን እያስደረካቸው ነው? ›› ብሎ ጠየቀው ከበደ ‹‹ቤት እያስጠረኳቸው ›› ብሎ መለሰ ከዛ ቤቱ ሲጠረግ አቧራው ስለተነሳ ከበደ ‹‹መጀመሪያ ውሃ አርከፍክፉበት ›› ብሎ ሰራተኞቹን አዘዘ... ሰራተኞቹ ሲያርከፈክፉ ሌላ መንገደኛ መጣና ‹‹ከቤ ሰራተኞቹን ምን እያስደረካቸው ነው? ›› ብሎ ጠየቀው ....ከበደ ምን ብሎ ይመልስ .....? (ማሳሰቢያ ...‹ውሃ እንዲያርከፈክፉ አዝዣቸው እያርከፈከፉ ነው› የሚል መልስ አንቀበልም!! ከበደ ሰራተኞቹን ሲጠርጉ ‹እያስጠረኳቸው › ካለ ሲያርከፈክፉ ምን ....እያስደረኳቸው ነው ይላል ?.....ጉዳችሁ ሊታይ ነው ዛሬ ሂሂሂሂሂ ከ 10 ነው እንዳትረሱ .......)
Posted on: Thu, 29 Aug 2013 12:49:34 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015