"ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ!" - TopicsExpress



          

"ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ!" ትዝብት በEfrem Tafesse..... ቃል ኪዳን!!! ከሞት በቀር የማይሻርና የማይለወጥ መሀላ ማለት ነው:: በግዋደኝነትም ሆነ በጋብቻ ውስጥ በቃል ኪዳን የተመሰረተ ፍቅር የተባረከና የፀና ነው:: ዛሬ ዛሬ ለሰንቱ ቃል ገብተን, የስንቱን ቃል በላን? እውነቱ ግን ይሄ አይደለም! ቃል ኪዳን ገቡ ማለት በራስዎ ማሉ ማለት ነው! ፍቅረኛሞች እና ባለ ትዳሮች ቃል ኪዳናቸውን ቢጠብቁ /ቢፈፅሙ/ እንደሚባረኩ ሁሉ, ባይፈፅሙ/ቢያፈርሱ/ ሊረገሙበት እንደሚችሉ መፅሀፍ ቅዱስም ቁርፀንም በግልፅ ያስቀመጡት እውነታ ነው! ከዚህም የተነሳ መፅሀፍ ቅዱስ ደስታ በተሰማህ ግዜ ቃል እንዳትገቡ ያዛል B/C ከስሜት የመነጨ ሊሆን ሰለሚችል እና ስለማንፈፅመው ተረጋግተን/አስበንበት/ ቃል መግባት እንዳለብን ያስተምራል! ያንም ያስቀመጠው ባንፈፅመው እግ/ር አምላክ/አላህ/ ሰለሚቀጣን ማለት ነው! ዛሬ ላይ ቃል ኪዳን ለ1 ቀን ለሰርግ ማድመቂያ እና መስፈርቱ ከሚግዋደል ተብሎ በቸልተኝነት ሲገባ እና ሳይፈፅሙ ሲቀር መስተዋላቸው አብሮን ያረጀ እና የፈጀ እውነታ ነው:: ታዲያ ቃል ኪዳንን ማፍረስ እርግማን, ጉስቁልናና ጥፋትን ያስከትላል! ትዕግስትን በማጣት እና ይቅርታን ባለማድረግ እንክዋን ቃል ኪዳናችንን ብናፈርስ ለከባድ ጉዳት እና ቅጣት እንደሚዳርገን እንደ ባዘቶ የጠራ የመፅሀፉ እውነታ ነው! አሁን ላይ ከሚስተዋሉት ቃል ኪዳን በሁለቱ ፍቅረኛሞች ብቻ የሚደረግ መሆኑ ነው! ይሄ አካሄድ ግን የተሳሳተ እንደሆነ ስጠቁማችሁ ግን ይህንን እውነታ ይዤ ነው:: ቃል ኪዳን የሚፈፀመው ግን ምስክሮች ባሉበትና ብዙም ሆነ ጥቂት ሰው በተገኘበት ቦታ መሆን አለበት! ከነዚህም ውስጥ በቤተ ክርስቲያን አባቶች ፊት እና በመዕመናን ፊት መሆን አለበት:: ቃል ኪዳን በግል እና በተናጠል አይፈፀምም! ጋብቻንና የፍቅር ግዋደኝነትን የሚያክል ነገር ቀርቶ ማንኛውም ውልስ እንክዋን በምስክር ፊት ካልተፈፀመ ዋስትናው አጠያያቂ ነው ህጋዊ አይደለምና! ይህን ሁሉ ስናደርግ ታዲያ ምስክሮች እነ ማን እንደሆኑ ልንገርዎ......? 1ኛ ምስክር እግ/ር 2ኛ ምስክር ቤተ ክርስቲያን/ምዕመናን 3ኛ ራሳቸው ተጣማሪዎቹ ናቸው:: ቃል ኪዳን የሚፀናው 1ዱ እስኪያጠፉ ብቻ ሳይሆን ከሞት በቀር ማንም ሊለይ የሚችል ነገር የለም ማለት ነው! ቃል ኪዳን አይደክምም አያረጅም B/C የቃል ኪዳኑ መሰረት እግ/ር ሰለሆነ:: ታዲያ ቃል ኪዳን ስንገባ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ መፈፀም እንዳለብዎ አይሰማዎትም??? ሰላም
Posted on: Wed, 09 Oct 2013 14:10:50 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015