ድምፃችን ይሰማ #EthioMuslims #USCIRF የኮሚሽነር - TopicsExpress



          

ድምፃችን ይሰማ #EthioMuslims #USCIRF የኮሚሽነር ዙህዲ ጃሲር የጉዞ ማስታወሻ (መነበብ ያለበት) ሰኞ መስከረም 6/2006 በኢትዮጲያ ውስጥ የፀረ-ፅንፈኝነት ትግል ከነፃነት ጋር ሲጋጭ ከሶማሊያ ህግ-አልባነት እስከ ኤርትራና ሱዳን የጭቆና ሥርዓት እና የሲቪል መብቶች ረገጣ የተነሣ የአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ ያልተረጋጋ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጲያ ጉዳይ ግን ከዚህ የተለዬ ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ ሁኔታ እየተቀየረ ይመስላል ይላሉ ኮሚሽነሩ፡፡ ኮሚሽነር ዙህዲ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከታህሳስ 15 እስከ 19 ድረስ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን (USCIRF) ተወካዮችን እየመራሁ አዲስ አበባ ነበርኩ ይላሉ፡፡ በጉብኝታችንም ይላሉ ኮ/ር ዙህዲ ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማለትም ከአሜሪካ አምባሳደር እስከ የኢትዮጲያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ የኃይማኖት መሪዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም የኃይማኖቶች-ህብረት ተወካዮችን አግኝተዋል፡፡ ጉዞ ከመጀመራችን በፊት በተለይም ከሃምሌ 2011 ጀምሮ በኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ላይ የተፈፀሙ የህግ ጥሰቶችን ሪፖርቶች አይተናል ይላሉ ኮሚሽነሩ፡፡ ያ ወቅት ማለት ይላሉ ዙህዲ (ሀምሌ 2003 የአህባሽ ግዳጅ ጠመቃ በሀረር በይፋ የተጀመረበትን ወቅት ማለታቸው ነው) የኢትዮጲያ መንግሥት ኢስላም በኢትዮጲያ ውስጥ እንዴት መከወን እንዳለበት ለመቀየር ለመጀመሪያ ጊዜ የፈለገበት እና ይህን አዲሱን ፖሊሲ የተቃወሙትን ሁሉ መቅጣት የጀመረበት ወቅት ነበር በማለት ያስታውሳሉ፡፡ የእኛም የምርመራ ግኝቶች በኃይማኖት ነፃነት እና የሚያመጡትን አሉታዊ ተፅዕኖ ማለትም የሰብዓዊ መብቶች እና የወደፊት ደህንነት ጉዳዮች ሁሉ አረጋግጠውልናል፡፡ እስከ ሃምሌ 2011 ድረስ፣ የኢትዮጲያ መንግሥት ሙስሊሞችን ጨምሮ የህዝቦቹን የኃይማኖት ነፃነት ያከብር ነበር፡፡ የህገ-መንግሥቱ አንቀፅ 27 ለኃይማኖች ነፃነትና ‹‹የመንግሥት ከኃይማኖት መለያየት››ን ዋስትና ይሠጣል በማለት ኮ/ሩ የህጉን ባዶነት ያስታውሳሉ፡፡ ኮሚሽነሩ ይህን ህግ ለመጣስ አራት ነገሮች ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ በማለት ዘርዝረዋል፡፡ አንደኛው፣ በጎረቤት ሶማሊያና ሱዳን የታየው የአሸባሪዎች የደህንነት ስጋት ማስከተሉ፣ ሁለተኛው፣ በድንበር አካባቢዎች ላይ የሳውዲ አራቢያ አስተሳሰብ እንደ ስጋት መታየቱ፣ ሦስተኛው የኢትዮጲያ ፖሊሲዎች የሲቪል ማህበራትን እንቅስቃሴ ስለሚጨቁኑ ነው፡፡ መንግሥት ለሰብዓዊ መብቶች፣ ለዴሞክራሲ የግንዛቤ ማስጨበጫና ግጭት አፈታት ጉዳዮች ለሚረደግ የውጭ እርዳታ ላይ በጣለው ከባድ ማዕቀብ ምክንያት ብዙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የህልውናቸው አጣብቂኝ ምርጫ ውስጥ ገብቷል፡፡ በመሆኑም ያላቸው አማራጭ ነፃነታቸውን አሳልፈው በመስጠት እና እንቅስቃሴያቸውን በመግታት ከመንግሥት ጋር ‹‹መሥራት›› ወይም ድርጅታቸውን መዝጋት ብቻ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ በኢትዮጲያ ውስጥ የኃይማኖትን ነፃነት የሚታዘብ ወይም የኃይማኖቶች-ህብረትን ትብብርና በኃይማኖቶች መካከል የሚፈጠሩትን ግጭቶች ለመፍታት እንቅስቃሴዎች የሚያካሂዱ ነፃና ገለልተኛ ቡድኖች/ ሲቪል ማህበራት የሉም፡፡ በመጨረሻም፣ የኢትዮጲያ መንግሥት የኃይማኖት ጭቆናን ለኃይማኖታዊ ስጋቶቹ እንደ አፀፋ ቅጣት መጠቀሙ ናቸው ብለዋል፡፡ ኮሚሽነሩ በመቀጠል ከሃምሌ 2011 ጀምሮ የኢትዮጲያ መንግሥት የጥቂት ሙስሊሞችን አስተሳሰብ ለመዋጋት በመወሰኑ ሳቢያ የሁሉንም ሙስሊሞች ነፃነት እየጨቆነ ነው ይላል፡፡ ስለዚህ የአህባሽ አንጃ አስተማሪዎችን ከሊባሎስ በማስመጣት የኢትዮጲያ የእስልምና አስተማሪዎችንና ኢማሞችን በኃይል ማስገደድ የአህባሾቹን አስተምህሮ እንዲቀበሉ እና እንዲያንፀባርቁ ተደርጓል ብሏል፡፡ መንግሥትም የተቃወሙትን ሁሉ ማጥፋት፣ ኢማሞችን ማባረርና መድረሳዎችንና ት/ቤቶች የመዝጋት እርምጃዎችን ሁሉ ወስዷል፡፡ ይህ ሁሉ የመብት ረገጣ የተካሄደው በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት (መጅሊስ) በኩልም ነው በማለት ትዝብታቸውን ለግሰዋል፡፡ የአህባሽ ጠመቃው ሲጀመር ይላሉ ኮሚሽነሩ የመጅሊሱ ባለሥልጣናት በህዝበ-ሙስሊሙ ሳይመረጡ በመንግሥት ተመልምለው የተቀመጡ ሲሆኑ በዚህም የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ሲያስመቱ እና ዕውቅና የተቸረውን ድምፅ ሲያራቁቱ ነበር፡፡ በዛው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ የአህባሽን አስተሳሰብ ለማስረፅ የተደረገው ጥረት ከመስጅዶችን ውጪ የተቃውሞ ሰልፎችን አቀጣጥሏል ይላሉ ኮሚሽነሩ፡፡ በ2012 ፀደይ ላይ 17 ሙስሊም ምሁራን አባላት ያሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ህዝበ-ሙስሊሙን ከመንግሥት ጋር ለማደራደር የኃይማኖት ነፃነት ዋስትናዎች እንዲያከብሩ ማለትም የአህባሽ የግዳጅ ጠመቃ እንዲቆም፣ የተዘጉ ት/ቤቶች እንዲከፈቱ እና የተባረሩ ኢማሞችና አስተዳዳሪዎች እንዲመለሱ በማለት ተመስርቶ ነበር፡፡ ኮሚቴው በተጨማሪ አዲስ ነፃና ፍትሃዊ የመጅሊስ ምርጫ እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር ይላሉ ኮሚሽነር ዙህዲ፡፡ በሃምሌ መጨረሻ ላይ ድርድሩ ሳይሳካ ቀርቶ፤ የተቃውሞ ሰልፎች በእጅጉ ተስፋፍተው እንዲሁም መንግሥት የቤት ለቤት ፍተሻ ማጧጧፍ ጀምሮ ነበር፡፡ በዚህም መንግሥት የኮሚቴ አባላቱን ጨምሮ 1ሺ ሰልፈኞችን አስሯል በማለት አክለዋል፡፡ በጥቅምት ወር ላይ መንግሥት ዘጠኝ የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ 29 ሰልፈኞችን በሽብር ተግባር እና እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት ሙከራ ከሷቸዋል፣ እስካሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ እንዚህ ሰዎች አሸባሪዎች ስለመሆናቸው ምንም ዓይነት ማስረጃ አልተገኘም እያሉ ኮሚሽነሩ የመንግሥት የግፍ ተግባር አጋልጠዋል፡፡ ኮሚሽነሩ የ28ቱን እስረኞች ጠበቆች አግኝተናቸው ነበር፤ ጠበቆቹም ደንበኞቻቸው ቶርቸር እንደተደረጉ እና ታሳሪዎቹን አግንኝተው ማማከር እንዳልቻሉ ነግረውኛል ይላሉ፡፡ መንግሥት እኛንም ከእስረኞቹ ጋር በቀጥታ እንዳንገናኝ ከልክሎናል ይላሉ ኮ/ር ዙህዲ፡፡ የሚገርመው ይላሉ ኮ/ር ዙህዲ የመንግሥት ባለሥልጣናት በአህባሽ የጠመቃ ሥልጠና ላይ ምንም ሚና እንደሌላቸው አድርገው ይክዳሉ፣ አንድን እምነት በሌሎች ላይ የመጫኑን ጉዳይ ያስተባብላሉ፣ ‹‹ቀይ መስመሩ››( ቃሉን ለመተርጎምም ፍቃደኛ አይደሉም) እስካልተነካ ድረስ በኃይማኖት ጉዳዮች እንደማይገቡ ይገዘታሉ፤ በመሆኑም ለአህባሽ የጠመቃ ሥልጣናው መጅሊሱን ብቻ ተጠያቂ ያደርጋሉ ምንም እንኳን የመጅሊሱ ባለሥልጣናት ከመነሻው በመንግሥት የተቀመጡ እና ለመንግሥት ብቻ ታዛዦችና አገልጋዮች ቢሆኑም፡፡ ከአዲሶቹ የመጂሊስ ባለሥልጣናት ጋር ባደረግነው ስብሰባም ይላሉ ኮ/ር ዙህዲ የመንግሥትና የኃይማኖት መለያየትን በመደገፍ የመንግሥትን የንግግር ቃላት ሲያስተጋቡ ነበር በተጨማሪም ሠልፈኞቹን ‹‹ሽብርተኞች›› እያሉ ስም በመለጠፍ ምንም እንኳን የተወሰኑት አባላቶችም ዱሮ ሰልፉን የተቀላቀሉ ቢኖርም በማለት ሆድ አደሮችን ታዝበዋቸዋል፡፡ የመጅሊሱ ም/ፕሬዜዳንትነት ለገዥው ፓርቲ ቅርብ ሰው ለሆነው ግለሰብ ተጠብቆ እንዲቀጥል መደረጉን ታዝበናል፡፡ እንዲሁም የመጅሊሱ ፕሬዚዳንት ቀደም ሲል በከፍተኛ የመንግሥት ቦታዎች ላይ ያገለገለ መሆኑን ታዝበናል፡፡ በመጨረሻም፣ የመጅሊሱ ባለሥልጣናት በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ምንም ልዩነት አይኖርም ተቃዋሚዎቹም ወደ እኛ ‹‹ይመጣሉ›› በማለት እንዲሁ በጭፍኑ ይናገራሉ፡፡ ይህ ባጠቃለይ ሲታይ ምን ማለት ነው? ምንም እንኳን የኢትዮጲያ መንግሥት ከሶማሊያና ከሱዳን የኃይማኖት ፅንፈኝነትን ቢፈራም የኃይማኖትን ፅንፈኝነት መዋጋት የሚቻለው በኃይማኖት ጭቆና ሳይሆን በኃይማኖታዊ ነፃነት ነው፡፡ ይህም ማለት የሃሳቦችን የውጤት ምህዳር በማራቆት ሳይሆን የኃይማኖትን ጨምሮ ሁሉንም ሃሳቦች የሚያካትት ምህዳር በመፍጠር ነው፡፡ ይህም የህዝቦችን የጋራ ስሜቶች በማመን፣ እንዲሁም የመንግሥትን ጭቅና ብቻ ሳይሆን የኃይማኖት ፅንፈኝነትና በራስና በቤተሰብ ላይ የሚደረግን አምባገነናዊ ቁጥጥርም እንደሚቃወሙ በማመን ነው፡፡ በእርግጥ በዓለም ላይ ብዙ ጥናቶች እንዲሚያረጋግጡት የኃይማኖት ነፃነት ባለበት ሁሉ መረጋጋት፣ መግባባትና መከባበር አለ በተቃራኒው የኃይማኖት ነፃነት በተነፈገበት ሁኔታ እነዚህ ሁሉ ይናፍቃሉ፡፡ ስለዚህ አክራሪዎች የሚያሸንፉበት ብቸኛው መንገድ ቢኖር መንግሥታት ፅንፈኞችን በመዋጋት ስም፣ በተከታታይ የህዝባቸውን ነፃነት ሲጋፉ ነው፡፡ በኢትዮጲያም ውስጥ ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ ነፃነትን ማጎናፀፍ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲባል ሳይሆን ለሀገር ሰላምና ደህንት ሲባል ለፅንፈኝነት ፍቱን መድሃኒት ስለሆነ ነው በማለት ኮሚሽነር ዙህዲ ልምዳቸውንና ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡ ሚ/ር ዙህዲ ጃሲር በአሜሪካ ዓለማቀፍ የኃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን ውስጥ ኮሚሽነር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ እኛም እውነታውን ለዓለም ህዝብ ስላቀረቡልን ኮሞሽነሩን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ስም ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡ አላሁ አክበር! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና አዲሱ ገጻችንን ላይክ ያድረጉ! https:// facebook / DimtsachinYisema 2 ሙሉ ፅሁፉን ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡፡ journal.georgeto wn.edu/2013/03/ 11/ counter-extremis m-with-freedom- in- ethiopia-by- m-zuhdi-jasser/ #.UT7MpRVriQA.fa cebook
Posted on: Mon, 16 Sep 2013 11:09:20 +0000

Trending Topics



"min-height:30px;">
CWMAD - CAN WE MAKE A DIFFERENCE???? we all are here to make a
Kuwaiti embassies to issue visit visas KUWAIT: In collaboration
Just heard from Stefan Arngrim, that we lost Don Matheson
JW Pet Company Mini Hol-ee Football Dog Toy, Colors
Political System in Islam. Islam and
Asking for prayer....our community, Barbers Hill...two families,

Recently Viewed Topics




© 2015