ድምፃችን ይሰማ #Ethiopia #EthioMuslims #DY - TopicsExpress



          

ድምፃችን ይሰማ #Ethiopia #EthioMuslims #DY #RadioDY ዛሬ በስካይፒ ያግኙን! የሚሰማዎትን ይንገሩን! ጁምአ ሐምሌ 26/2005 ለሬዲዮ ድምጻችን ይሰማ ይናገሩ! ሬዲዮ ድምጻችን ይሰማ ዛሬ አስተያየታችሁን በስካይፒ ይሰበስባል፡፡ ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ መንግስት ትናንት ምሽት ስላወጣው መግለጫ፣ ስለ ጁምአ ተቃውሞ መሰረዝና መሰል ጉዳዮች ያላችሁን አስተያየት ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 11፡ 00 ሰዓት ድረስ በስካይፒ ተገኝተው ይንገሩን፡፡ የስካይፒ አድራሻችን Radio.Dy ነው፡፡ የስካይፒ ላይ ጥሪውን የሚያስተናግደው የኮምፒውተር ፕሮግራም በመሆኑ አስተያየትዎን ወይንም ጥያቄዎን የኮምፒዩተር ፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንዳበቃ በቀጥታ በአጭሩ ያስተላልፉ፡፡ በመሆኑም የምትደውሉ ሁሉ በስካይፒ ላይ ተጨማሪ ውይይት እና ጥያቄና መልስ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ለማስታወስ ያህል ሬዲዮ ድምጻችን ይሰማ በ 19 ሜትር ባንድ 15150፣ 15155፣ 15160፣ 15165፣ 15170፣ 15175 እና 15180 ኪሎ ኼርዝ (KHZ) አጭር ሞገድ የሚተላለፍ ሲሆን አርስዎ በማድመጥ እንዲሁም በመላ ሃገሪቱ እንዲደመጥም መረጃውን በማስተላለፍ የድርሻዎን እንዲወጡ እናስታውሳለን፡፡ አላሁ አክበር!
Posted on: Fri, 02 Aug 2013 07:37:40 +0000

Trending Topics



ass="stbody" style="min-height:30px;">
Viega 56081 PureFlow 1-1/2-Inch Standard PEX Press Jaw 6g6knnm
DO YOU KNOW THAT THE PHILIPPINES IS OWNED BY A SINGLE
Hasil latihan bebas IV motoGP, Brno, Republik Ceko: 1.
Sam Spade was busy so I pulled on my trench coat patted my

Recently Viewed Topics




© 2015