ድምፃችን ይሰማ! #Ethiopia #EthioMuslims - TopicsExpress



          

ድምፃችን ይሰማ! #Ethiopia #EthioMuslims #DY #JumaDemonstration #EthioMuslimWorldWideProtest ፈጽሞ የማይቀርበት ጁምአ እውን ሊሆን አንድ ቀን ብቻ ቀረው! ረቡእ ሐምሌ 17/2005 የታሪካዊው ጁምአ መርሐግብር! ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሁሉ ታሪኩን የሚያድስበት እለት! ልክ ከሁለት አመት በፊት በዚህ ወቅት ነበር የመንግስታዊው ሃይማኖት በሃይል የመጫን ነጋሪት መጎሰም የጀመረው፡፡ ከሀረር ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ የተሰማው ጉድ ልዩ ነበር፡፡ ‹‹አዲሱ ሃይማኖት ከመንግስት ለህዝቡ የተመረጠ ነው፤ ከዚህ ውጪ ውልፍት ማለት አክራሪነትን ማበረታታትና አሸባሪነትም ጭምር ነው›› የሚል አዋጅም ታወጀ፡፡ ባለፈው አመት ልክ በዚህ ወቅት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር የመንግስትን እርምጃ በመቃወም የተንቀሳቀሱበት ወቅት ነበር፡፡ ሕዝቡ ለስምንት ወራት ያህል ያደረገውን ትግል በማፋፋም የመጨረሻ ምእራፍ ላይ በደረሰበት ወቅት መንግስት ባሰበውና ባቀደው መሰረት አዲሱን ሃይማኖት አንቀበልም ያሉትን ሙስሊሞች በጥይት መቁላት ጀመረ፡፡ በአወሊያ፣ በአንዋር፣ በደሴ፣ በተባረክ፣ በባዩሽ እና በሌሎችም መስጂዶች ሙስሊሞች በጥይት፣ በድብደባ፣ በአስለቃሽ ጭስ ከመሬት ወደቁ፡፡ መንግስት መሪዎቻችንን በግፍ ወደ ወህኒ ገፋቸው፡፡ እኛ ደግሞ ይህ የመንግስት የሽብር ተግባር በተፈጸመ ልክ በአመቱ በሌላ አገራዊ ሳይሆን አሕጉራዊ ተቃውሞ ለመታደም ሰዓታት ቀርተውናል፡፡ መንግስት ያንን ሁሉ አስከፊ እርምጃ የአገሪቱ ሙስሊም ዜጎች ላይ የወሰደው ዛሬ ልንታደምበት የተዘጋጀነው ተቃውሞ እውን እንዳይሆን፣ በበደል ብዛት አፋችን እንዲለጎም፣ በመንግስት የሽብር እወጃ ተሸማቀን ከጓዳ እንድንሸሸግ፣ የፍትህ መጓደል እንዳያስጨንቀን፣ የእምነት መብት መጣስ ምን ገዶን እንድንል፣ ኢስላማዊ አንድነታችን ትርጉም አልባ እንዲሆን ነበር፡፡ ግን አልሆነም አልሀምዱሊላህ! ዛሬም በደል በነገሰበት አገር ፍትህ የምንል ዜጎች ነን! በፍርሃት አፋችን አልተለጎመም! በሴራ አንድነታችን አልተፈታም! መሪዎቻችንን እስር ቤት ጥለን ቤታችን አልተሸሸግንም! አልሀምዱሊላህ! ቃል ኪዳናችንንም እየሞላን መጥተናል፤ ትውልዱንም አኩርተናል! በመጪው ጁምአም ይህን ታሪካችንን እናድሳለን፡፡ በመጪው ጁምአ ታሪካችንን የምናድሰው በልዩ ዝግጅት እና ትእይንት ነው፡፡ በአገር ውስጥ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአገር አቀፍ ደረጃ ከምናደርገው ተቃውሞ ውጪ ድምጻችን ህብር ሰርቶ በአህጉረ አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካ ይሰማል፡፡ ጥያቄያችን አንድ ሆኖ፣ በአካል አንድ ቦታ ባንሆንም በመንፈስ ግን አንድ ላይ ሆነን፣ የሕግ መጣስ፣ የፍትህ መጓደል፣ የዜጎች ክብር መናቅ አስተሳስሮን ‹‹ድምጻችን ይሰማ!››፣ ‹‹ፍትህ አይጓደል!›› ብለን ስለ ሕግ የበላይነት ልንሟገት ተዘጋጅተናል፡፡ በዚህ ታሪካዊ ተቃውሞ ሙስሊሙ ሁሉ ከእነ ቤተሰቡ በመገኘት ታሪኩን እንደሚያድስና ዙልምን አጥብቆ እንደሚቃወም ዳግም ያረጋግጣል፡፡ * በአገር ውስጥ በአዲስ አበባ በፒያሳው ኑር መስጂድ የተቃውሞው ስነ-ስርአት የሚካሄድ ሲሆን በክልሎች ደግሞ ዘወትር ተቃውሞ በሚደረግባቸው መስጂዶች ይካሄዳል፡፡ * ከአገር ውጪ በወጡት የጊዜ ሰሌዳዎችና መሰባሰቢያ ቦታዎች ዝርዝር መሠረት ተቃውሞዎቹና የኢፍጣር መርሀ ግብሮቹ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ በአገር ውስጥ በዕለቱ አትመንና አዘጋጅተን የምናመጣቸው መፈክሮች ተከታዮቹን መልእክት የያዙ ሊሆኑ ይገባል፡፡ 1. የመጅሊሱ አመራሮች አይወክሉንም! 2. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከዳር እስከ ዳር ተነስተናል! 3. ተቋሞቻችንን አሕባሾች አይወርሷቸውም! 4. የተነጠቁ መስጂዶቻችን ለሕዝብ ይመለሱ! 5. የተባረሩ ኢማሞች ይመለሱ! የጁምአ ሰላት እንደተጠናቀቀም እጅ ለእጅ ተያይዘንና ባለንበት ቦታ በመቆም በድምጽ ልንላቸው የሚገቡ መፈክሮችን ማሰማት እንጀምራለን፡፡ በድምጽ የምናሰማቸው መፈክሮች ደግሞ ተከታዮቹ ናቸው፡፡ 1. ‹‹አላሁ አክበር!›› ለ 3 ደቂቃ 2. ‹‹ድምፃችን… ይሰማ!›› ለ 3 ደቂቃ 3. ‹‹ጣልቃ ገብነት ይቁም!›› ለ 3 ደቂቃ 4. ‹‹ጥያቄዎቹ ይመለሱ!›› ለ 3 ደቂቃ 5. ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!›› ለ 3 ደቂቃ 6. ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!›› ለ 3 ደቂቃ 7. ‹‹ሕገ መንግስቱ ይከበር!›› ለ 3 ደቂቃ 8. ‹‹ድራማው ይብቃ!›› ለ 3 ደቂቃ 9. ‹‹ኢማሞቻችን ይመለሱ!›› ለ 3 ደቂቃ 10. ‹‹መጅሊሶች አይወክሉንም!›› ለ 3 ደቂቃ 11. ‹‹የመንግስት ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ!›› ለ 3 ደቂቃ በመጨረሻም ካለንበት ቦታ ሳንንቀሳቀስ እጆቻችንን ወደ አላህ በመዘርጋት ዱዓ በማድረግ ወደየመጣንበት እንመለሳለን- ኢንሻ አላህ፡፡ * ማስታወሻ - በተቃውሞአችን እለት በመስጂድ ግቢ ውስጥ ያለንም ሆነ ከግቢው ውጪ የምንገኝ ባለንበት ቦታ ረግተን በመቆም ተቃውሞአችንን ማከናወን ይኖርብናል፡፡ ከቦታ ቦታ መነቀሳቀስን በማስቀረት ባለንበት ቦታ ሰብሰብ በማለት ተቃውሞ እናደርጋለን፡፡ ይህም በመሀላችን ሰርገው በመግባት ሁከትን ለሚሹ የትንኮሳ ክፍተቶችን ለመዝጋትና ወጥነት ያለው አብይ ተቃውሞ ለማድረግ ይረዳናል፡፡ የተቃውሞ መርሐግብሩን እንዳጠናቀቅንም ተነጥለን ከመመለስ በጋራ ሰብሰብ ብለን ወደመጣንበት መመለስ እንዳለብንም ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ አላሁ አክበር! Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ይሄን ሊንክ ጠቅ አድርገው ይከተሉና አዲሱ ገጻችንን ላይክ ያድረጉ! https://facebook/ DimtsachinYisema2
Posted on: Thu, 25 Jul 2013 04:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015