ድሮ facebook ላየ የምገባው ቆንጆ ቆነጆ - TopicsExpress



          

ድሮ facebook ላየ የምገባው ቆንጆ ቆነጆ ሴቶች ጋር ለመተዋወቅ፤ የሚለጥፉትን ፎቶዎች ለማየት እና ለማድነቅ (ወይኔ ላይኮቼ እና ሼሮቼ……….መልሱልኝ….)ፉገራ እና ቀልድ ወሬዎችን ለማየት እና ለማንበብ ነበረ…..እናም መሰላቸት እና በራሴ መበሳጨት ጀምሬ ነበር……..ከሆነ ጊዜ ነኋላ ግን ጥሩ ጥሩ የሚባሉ የ facebook ከያኒዎች እና ገጾች መጡ……ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ የ facebook ግድግዳዬን በጸሃፊዎች፤ በዜና አቅራቢዎች እና በኪነጥበብ ነገሮች የሞላሁት……..የሚገርመኝ አሁን አሁን መጀመሪያ facebook ስከፍት መንበብ የምፈልገው አለም እንዴት አደረች፤ እነ Alex Abreham ምን ጻፉ፤ እኔ ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር - Hiwot Emishaw ምን ነቆሩ፤ እነ ጠይም በረንዳ: ዘ ዮሐንስ ሞላ/ Chocolate Porch: Yohanes Molla’s ምን አሉ ምንስ ገጠሙ ሆኗል…………………….. እናም አሌክስ የሚባል ሰው ሳስብ ምንም ነገር ሳልጽፍ የሱን ጽሁፎች ብቻ ለማንበብ facebook አካዉንቴን ብጠቀመው ደስ ይለኛል። በቃ facebook ከማይረባ ፎቶ መለጠፊያነት ፤እንቶ ፈንቶ ጽሁፍ ከማቅረቢያነት ይልቅ የነ አለክስ ታሪክ የነ ዮሐንስ ወሬና ግጥም የነ ህይወት ነቆራ ማንበቢያ አትሮንስ ስለሆነልኝ ለ #MarkZuckerberg ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው። የነብዩ ሰለሞን ‹‹ያማል ›› ግጥም በጣም እወደዋለሁ (በጣም እወደዋለሁ አይገልጸውም.....ግን ቀጥራኝ ስለቀረች አይደለም.....ሃሃ) እናም ይሄንንም ግጥም ከሱ ተርታ መድቤዋለሁ......ሙቱ!!! እስኪ Alex Abreham እያመሰገናችሁ ኮምኩሟት!!!!!!!!!!!! ስማኝማ አንተ ሰው .... የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ አልነበረ ያልከው ከመቅረት የባሰ አመጣጥ እንዳለ አንተ መቸ አወከው አይዞን ወዳጀ ያው እንዳንተ ደጃፍ ኦና ሁኗል ደጀ አሁን ናፍቀኸኛል ..... እጠብቅው የለኝ ትጠብቀው የለህ እንገናኝና ‹አረቄ› እየጠጣን ግጥም እንፃፍለት ለድህነታችን ጥበቃን ላሳጣን !! እናቱን ድህነት !! እናቱን ጥበቃ !! በቃ!!
Posted on: Wed, 28 Aug 2013 08:22:32 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015