ግብጽ በሙባረክ ዘመነ መንገስት - TopicsExpress



          

ግብጽ በሙባረክ ዘመነ መንገስት በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ድርጊት ይቅርታ ልትጠይቅ ግብጽ Egypt should cooperate with Ethiopia as sign of apology for Mubarak’s era deeds| See at .... diretu.be/748226 | ግብጽ በሙባረክ ዘመነ መንገስት በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ድርጊት ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባታል - የግብጽ የቀድሞው የፓርላማ አባል፡፡ አብዱላሂ ሀራሪ የተባሉ አንድ የቀድሞ የግብጽ ፓርላማ አባል ግብጽ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ዘመነ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለተወሰዱ አላስፈላዲ ውሳኔውች እና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ይቅርታ ልትጠየቅ ይገባታል ብለዋል፡፡ አብዱላሂ አክለውም በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚደረገው የአል ሲሲ የአዲስ አበባ ጉብኝት ኢትዮጵያ እና ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ የፈጠሩትን አለመግባባት በንግግር እና በመተባበር ለመፍታት በር የሚከፍት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ የቀድሞው የፓርላማ አባሉ ግብጽ ኢትዮጵያን ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል ከማለታቸው ውጪ በሆሲኒ ሙባረክ ዘመን በኢትዮጵያ ላይ ተፈጸመ ስላሉት አላስፈላጊ ድርጊት ማብራሪያ ያልሰጡ ቢሆንም በወቅቱ ግብጽ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ላይ የመግደል ሙከራ እስከማድረግ የደረሰ እንቅስቃሴ ማድረጓን እየተጋለጡ ያሉ መረጃዎች መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
Posted on: Sat, 14 Jun 2014 13:00:01 +0000

Trending Topics



Recently Viewed Topics




© 2015